በፆም ወቅት ጁኑብ መሆን
~
1- መብላት መጠጣት በሚፈቀድበት የሌሊቱ ክፍል ላይ ሐላል ግንኙነት የተፈቀደ መሆኑ ግልፅ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ أُحِلَّ لَكُمۡ لَیۡلَةَ ٱلصِّیَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَاۤئكُمۡۚ }
"በፆም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለናንተ ተፈቀደላችሁ።" [አልበቀረህ: 187]
2- በሌሊቱ ክፍል ጁኑብ ሆኖ ሳለ ሳይታጠብ የፈጅር ወቅት ቢገባ ፆሙ ላይ ችግር የለውም። እናታችን ዓኢሻህ - ረዲየላሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦
كَانَ رسول الله صلى الله عليه وسلم يُدْرِكُهُ الفَجْرُ وَهُوَ جُنُبٌ مِنْ أَهْلِهِ، ثُمَّ يَغْتَسِلُ وَيَصُومُ.
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከባለቤታቸው ጀናብተኛ ሆነው የፈጅር ወቅት ይደርስባቸው ነበር። ከዚያ ታጥበው ፆማቸውን ይቀጥላሉ።" [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም]
3- በቀኑ ክፍለ ጊዜ ተኝቶ ኢሕቲላም በመሆኑ ጀናባ የገጠመው ሰው ፆሙ ላይ ተፅእኖ የለውም። ምክንያቱም እንቅልፍ ላይ ያለ ሰው እስከሚነቃ ድረስ ተጠያቂነት የለበትምና። በኢስላም ማንም ቢሆን ከአቅሙ ውጭ በሆነ በማይችለው ነገር አይጠየቅም። አላህ እንዲህ ይላል፦
{لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا}
"አላህ ነፍስን የችሎታዋን እንጂ አያስገድዳትም።" [አልበቀራህ: 286]
ነብዩም ﷺ መፆም ያሰበ ሆኖ ሳለ ጀናባ ሆኖ እንደሚነጋበት ለነገራቸው ሰው እሳቸውንም እንደሚገጥማቸውና ፆሙ ላይ ችግር እንደሌለበት ነግረውታል። [ሙስሊም ዘግበውታል።]
4- በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ ባለ መንገድ ራሱን በማርካት (ኢስቲምናእ በማድረግ) ጁኑብ የሆነ ሰው አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ ፆሙ ተበላሽቷል። ፆሙ እንደማይበላሽ የገለፁ ቢኖሩም ራስን ከውዝግብ ማራቅ የተወደደ ነው።
5- በቀኑ ክፍለ ጊዜ ቀጥታ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ፆሙ ይበላሻል። ከዚያም ባሻገር ለጥፋቱ ጥብቅ ማካካሻ ይጠበቅበታል።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor