ቅናት አያረጅም!
~
የአዛንና የሶላት ሰዓት አጭር ነው። በጥላቻ ስትሞላ ግን 5ቱ ደቂቃ አምስት ሰዓት ይሆንብሃል። ሰፈራችን ላይ የሱብሕ አዛን 11፡25 አካባቢ ተደረገ። ሶላቱ ደግሞ ሩብ ጉዳይ አካባቢ። ሁሉም ቢደመር 20 ደቂቃ አይሞላም። ከማዶ የሚሰማው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ግን እስካሁን አልተቋረጠም። ይሄ የየሰፈሩ እውነታ ነው። ግን የራስ እንትን አይገማም።
የዚች ሃገር ትልቁ ችግር ቅናት ነው። ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚገፋው አስተማሪ ከክልከላው ጀርባ ያደፈጠው ምክንያቱ ምቀኝነት ነው። ሌላው እንዲሁ ሽፋን ነው። የራሱን ማስለበስ ሲያቅተው ሌሎች ላይ ይዘምታል። "ለሙስሊሞች ሒጃብ ከተፈቀደ እኛም ነጠላ እንለብሳለን" የሚለው የምቀኛ ሰፈር ልጆች መፈክርም የታወቀ በሽታ ነው፣ ቅናት። "ለሙስሊሞቹ መስገጃ ከተፈቀደ ለኛም መፀለያ ይፈቀድልን" የሚለው የምቀኝነት ልክፍትም የተለመደና ዝነኛ ህመም ነው።
ምቀኝነት እየተጋተ ያደገ አካል አድጎ አርጅቶ፣ በምርኩዝ እየሄደ፣ የሌሎችን ሃገራት ሁኔታ እያየ እንኳ አይለወጥም። እንዲያውም እየባሰበት ይሄዳል። ወደው አይደለም "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም" የሚሉት። በቅናት የገረጣ ፊት በቅባት አይወዛም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor