የመንግሥትና የግል ሠራተኞች ከደመወዛቸው ለአደጋ ሥጋት ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ‼️
👉ባንክና ኢንሹራንስን ጨምሮ በበርካታ 👉አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ይፈጸማል።
የሚጠበቅባቸውን ክፍያ በወቅቱ ገቢየማያደርጉ ወለድና ቅጣት ይከፍላሉ።
የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካል ሆኖ እንዲቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ የመንግሥትና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ሠራተኞች ከሚከፈላቸው የተጣራ የወር ደመወዝ ላይ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስገድድ ድንጋጌ ተካተተ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤት አባላት በረቂቁ ላይ ለስምንት ደቂቃ ያህል ከተወያዩበት በኋላ፣ ለምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል፡፡
በረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ ላይ በቅድመ አደጋ፣ በአደጋና በድኅረ አደጋ ወቅቶች ለሚወሰዱ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ፣ ምላሽና መልሶ ማቋቋም የሚሆን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ መቋቋሙ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ ተገማችና የአደጋ ሥጋት ምላሽ የፈንድ ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በአገር በቀል አቅም ዜጎች፣ ማኅበረሰብና ተቋማት እርስ በርስ በመደጋገፍ የአደጋ ሥጋትን የመከላከል፣ የማቅለል፣ የዝግጁነት፣ የምላሽ፣ የማገገምና በተሻለ ሁኔታ መልሶ ማቋቋም ላይ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል ትልም የያዘ ስለመሆኑ ተብራርቷል፡፡
ፈንዱ ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ ከሚቆረጥለት ገቢ በተጨማሪ ባንኮች፣ አነስተኛና ጥቃቅን የፋይናንስ ድርጅቶች ከሚሰጡት የብድር መጠን ላይ፣ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለሚሰጡት አገልግሎት ከሚሰበስቡት የፕሪሚየም (ዓረቦን) ክፍያና ከማንኛውም የአክሲዮን ዲቪደንድ ድርሻ እንደሚሰበሰብ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ከበረራ ትኬት ሽያጭ፣ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ለድምፅና ለዳታ አገልግሎት ከሚያስከፍሉት የአየር ሰዓት ዋጋ፣ ከፓስፖርትና ከቪዛ አገልግሎት ክፍያ፣ የነዳጅ ሽያጭ አቅራቢ ድርጅት ከሚያገኘው ገቢ፣ ማንኛውም የንግድ ፈቃድ በሚወጣበትና በሚታደስበት ጊዜ በቁርጥ የሚታሰብ እንደሆነም በረቂቁ ተካቷል፡፡
#ሪፖርተር
====================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2shttps://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2shttps://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2