Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በየትኛውም ብሄር ውስጥ ያሉ ሙስሊም ብሄርተኞች ወይም የብሄር ፖለቲከኞች እንዳለ መናጆ ብቻ ናቸው፣ የራሳቸው አስተማማኝ ቁመና የላቸውም። የዝና ማማ ላይ የሚገኙትም በዚህ ረገድ የተለዩ አይደሉም።
በብሄራቸው ውስጥ ከሌሎች የበለጠ ወይም የጎላ መስዋእትነት ቢከፍሉ እንኳ ስኬታቸው ገደብ አለው፡፡ ይህንን እራሳቸውም ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዚያም ነው በብሄር አጋሮቻቸው በኩል ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲሰነዘር በብሄር ተኮር ጉዳዮች ላይ እንደሚያደርጉት መረር አድርገው የማይነቅፉት። አክሱም፣ ጎንደርና ወለጋ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ናቸው። ደፍረውና ገፍተው ጠንከር አድርገው "ለምን?" ያሉ ለታ እንደ ብሄራቸው ለትግራይ፣ ለአማራ ወይም ለኦሮሞ ህዝብ አንድነት የማይጨነቁ፣ የትግል ቅደም ተከተል ያልገባቸው፣ አለፍ ሲልም ፅንፈኞች ተደርገው ይሳላሉ። የከሸፉ እንደሆኑ ተደርገው ይዘመትባቸዋል። በዚህ የተነሳ ለእምነት ያን ያህል ክብር በሌለው ቆሻሻ የዘር ፖለቲካ ውስጥ በዝምታቸው እንደተከበሩ መኖር ነው የሚፈልጉት። እምነት ተኮር በደሎችን ቢነቅፉ እንኳ ፖለቲካዊ ትርፍ በሚያስገኝ መልኩ ተቀናቃኝን ለማሳጣት የታለመ እንጂ በአብዛኛው ሐቀኝነት የሚታይበት አይደለም። ሐቀኛ ማለት በሌሎች የሚፈፀሙ በደሎችን በቀጥታ እያወገዘ በደሉ "የኔ" በሚላቸው አካላት ሲሆን ሰበብ የማይደረድር ነው። ለፖለቲካ ትርፍ ቁስላችንን እያከኩ ሌሎች ላይ መዝመትማ፣ ... ለዚህ ለዚህማ ከትኛውም ብሄርተኛ በላይ ለቅኝ ግዛት መጥቶ የነበረው ጣልያን ለሙስሊሞች የተሻለ ብዙ ውለታ ውሏል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor