«ደረቅ ሴት በፍፁም እንዳታገባ!!»
------------------------------
👉መጀመሪያ ትዳርን ስታስብ
«እንጨት ነች ወይስ ቅጠል ብለህ ጠይቅ» ወንድም አለም ትዳር Join የሚባል የቴሌግራም ቻናል እንዳይመስልህ እሽ⁉️
📌 ያለፈ ታሪክ ያላት ሴት ይቅር ብለህ ልታገባት ትችላለህ!!
📌 መጥፎ ባህሪ ያላት ልጅ ትስተካከላለች ብለህ ልታገባት ትችላለህ!!
📌ምናልባት ባለማወቅ በተሳሳተ ግንዛቤ ቤተሰቦቿን ማህበረሰቧን ባትወድም እገራታለሁ ብለህ ልታገባት ትችላለህ!!
🥊ከሀገራችን ተጨባጭ አንፃር ዲኗ ላይ ደካማ ሁና ትስተካከላለች ትማራለች ብለህ ልታገባት ትችላለህ!!
........❌ነገር ግን በፍፁም አደራ የምልህ"ደረቅ መንቻካ» ሴት ወደ ህይወትህ ላይ ጭራሽ ማስገባት የለብህም።
👉ዶክተር ኢብራሂመል-ፈቂ ሲናገር.. ደረቅ እና ለዘብተኝነት ውርደት ሚመስላቸው እንስቶች ትዳር የሚፈርሰው በነሱ ጦስ ነው ምክንያቱም ለድርቀታቸው ሲሉ የትዳር ህይወታቸውን መስዋት ያረጋሉ ይላል።
ድርቅናን ለማፍረስ ከባድ ትግል ይጠይቃል ምናልባትም ከሷ በሆላ ሁሉንም ሴቶች በሷ ልክ ልትቀርፅ ትችላለህ‼️
...... ለዛም ነው የመናዊው ፀሀፊ የመፀሀፉን ርዕስ፦
( النساء العاندات لا يصلحن لزواج)
«ደረቅ ሴቶች ለትዳር አይሆኑም» ብሎ የሰየመው.....
👉ትዳር መተናነስን ይፈልጋል ።
👉ነገሮች ይስተካከሉ እንጂ ብዙ ችግር የለውም ማለትን ይፈልጋል ።
👉በጣም አይቶ ማለፍን ይፈልጋል ።
👉ደረቅ ሴት ደግሞ ሲበዛ ራስ ወዳድ ናት ለኢጎዋ ስትል ምንም ታረጋለች ።
👉ሀሳቧን አለመቀየሯ ለሷ ጀግንነት ይመስላታል።
👉በምክኒያት ልታሳምናት አትችልም ምክኒያቱም..ምክኒያታዊ አይደለችም ። 👉ተሳስተሻል እንድትባል አትፈልግም። 👉መሳሳት ለሷ ሞት ነው ።
👉ፍታኝ ለማለት ትቸኩላለች።
👉ከሱጋ መለያየት የቤተሰብ የሞራል አደጋ መሆኑን እያወቀች ግን እሱ ቢቀርባት ምንም እንደማይፈጠር ለማስመሰል ትተጋለች ።
👉ለድርቅናዋ እስከጥግ መስዋትነት ትከፍላለች።
.......እዚህ ጋር አረቦች ትዝ አሉኝ....‼️
📌አረቦች ሊያገቧት የፈለጓትን ሴት ሚቀርባት ሰው ጋ ይሄዱና በአሽሙር الخشب او الورقة ይላሉ እንጨት ናት ቅጠል ማለታቸው ነው ።
👉 ይህ ማለት ትንጭ እንጨት እንጨት ካለች ህይወት ነውና ደጋግሞ ያስብበታል ማለት ነው ።
«ስሚ ልንገርሽ»
📌አትተብች ወላሒ ባልሽ ባልሽ ነው በቃ‼️
📌ሁሉ ነገርሽ ለሱ ግልፅ መሆን አለበት!?
📌ብትተናነሺለትስ ዝቅ ብትይለትስ!? 📌📌ያልፈለግሽውን አርጊ ብሎሽ ብታረጊለትስ?
📌ከሱ ውጭ ሂወት አለሽ ???
👉ይህን አይነቱ የሴትነት ባህሪ ዛሬ ላይ እጅግ ከኛ ርቆ እያጣነው ከመጣን ከጥቂቶች ውጭ ዘመናት አለፉት ።
... ......ስንቶች ሴቶች ናቸው ባላቸውን በአስተሳሰብ ለመብለጥ ወይም ካንተ እሻላለሁ የሚለውን ለማሳያት ሚጥሩት በአሏህ??
......ስንቶቹ ናቸው ባሏ ይፈራታል እንዲባሉ ሚፈልጉ ሴቶች ታዲያ የዚህች አይነቷ ሴት ነች ከብት ??
..... እናማ ወንድሜ ያ ፀሀፊ ልክ ነው «ወላሒ ደረቅ እንስቶች ለትዳር አይሆኑም»። ገና ስታወራት እንኳን ዝምብላ «ጀሸእ» ኩራት ወይም ኢጎ ወጥሯት ለምን እንዲህ አደረገ ብላ በማይጠቅም ነገር ኢግኖር ካበዛች እንዴት ከሷጋ ልትዘልቅ ነው⁉️
🥊ድርቅና በውስጡ ኩራትን፣ ማን አለብኝነትን፣ማን ስለሆነ ነው እና ግትር መሆንን ያካታል።
ለዘብተኝነት የሴት ልጅ ሸማ ልበሷ ነው ቻይነት ያልተሰጣት ሴት ህይወቷን በራሷ ታፈርሰዋለች ።
👉ግትር ሴት ተጠንቀቂ ተስተካከይ‼️
.....Nur
http://t.me/nuredinal_arebihttp://t.me/nuredinal_arebi