የኔ ጌታ | ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
የኔ ጌታ
ሰምቼ አድምጬ ልቀመጥ በእርጋታ
መንፈሴን አበርታ/2/
ፈጥኖ ይስማማና ሐሳብህ ከሀሳቤ
ስጋት መከራዬ ይነቀል ከልቤ
ጭንቀትን ይነቅላል እርጋታን ይተክላል
ቃልህ ስልጣን አለው ያፈርሳል ይሰራል
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
ችግሬ ታላቅ ነው አይበል ከንፈሬ
ታላቅነትህን ለንገር ለችግሬ
ጠላቴ ፊት ስቆም ፊትህ ተንበርክኬ
የድል ነው ዘመኔ የድል ነው ታሪኬ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
ዝናብ ታመጣለህ ባይኖርም ደመና
በረከትን ልጥገብ እሺ ልበልና
ያደረክላትን ልንገራት ልነብሴ
ልጠማ ጧት ማታ ልስማ በመንፈሴ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
በፊትህ ምንድን ነው የሴረኞች ሴራ
ቃልህ ጉልበት አለው ይንዳል ተራራ
በእርሱ መዶሻነት በደሌ ሲመታ
ጫጫታው ያልፍና ይሰፍናል ጸጥታ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አያፍረኝ አይፈራኝ ቃልህ መስታወቴ
ሁሌ ይነግረኛል ስለማንነቴ
ወዴት እንደወደኩ ወዴትስ እንዳለው
ሽንገላን በማያውቅ በቃልህ አውቃለው
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
የኔ ጌታ
ሰምቼ አድምጬ ልቀመጥ በእርጋታ
መንፈሴን አበርታ/2/
አዝ
ፈጥኖ ይስማማና ሐሳብህ ከሀሳቤ
ስጋት መከራዬ ይነቀል ከልቤ
ጭንቀትን ይነቅላል እርጋታን ይተክላል
ቃልህ ስልጣን አለው ያፈርሳል ይሰራል
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ
ችግሬ ታላቅ ነው አይበል ከንፈሬ
ታላቅነትህን ለንገር ለችግሬ
ጠላቴ ፊት ስቆም ፊትህ ተንበርክኬ
የድል ነው ዘመኔ የድል ነው ታሪኬ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ
ዝናብ ታመጣለህ ባይኖርም ደመና
በረከትን ልጥገብ እሺ ልበልና
ያደረክላትን ልንገራት ልነብሴ
ልጠማ ጧት ማታ ልስማ በመንፈሴ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ
በፊትህ ምንድን ነው የሴረኞች ሴራ
ቃልህ ጉልበት አለው ይንዳል ተራራ
በእርሱ መዶሻነት በደሌ ሲመታ
ጫጫታው ያልፍና ይሰፍናል ጸጥታ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ
አያፍረኝ አይፈራኝ ቃልህ መስታወቴ
ሁሌ ይነግረኛል ስለማንነቴ
ወዴት እንደወደኩ ወዴትስ እንዳለው
ሽንገላን በማያውቅ በቃልህ አውቃለው
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All