Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
=>አባቶቻችን ይህንን ቅዱስ "ኃያል መነኮስ" ይሉታል:: በ20 ዓመቱ ወደ በርሃ ገብቶ ለ70 ዓመታት በበርሃ ሲጋደል 90 ዓመት ሞልቶታል:: ሰይጣንን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከአካባቢው አርቆታል::+ሰይጣንም እርሱን መጣል ስላልቻለ ቢያንስ ከጾሙ: ጸሎቱና ስግደቱ ትንሽ ቢቀንስልኝ ብሎ አዲስ የፈተና ስልትን ፈጠረ:: ቀርቦም በገሃድ "አብራኮስ አንተ ደክመሃል:: ግንኮ ገና 50 ዓመት እድሜ አለህ" አለው::
+ቅዱሱ ግን ሰይጣንን "አሳዘንከኝ! እኔኮ ገና 100 ዓመት ያለኝ መስሎኝ ነው በጥቂቱ የምጋደለው:: እንዲያ ከሆነማ ከነበረኝ ጾም: ጸሎትና ስግደት በእጥፉ እጨምራለሁ" ቢለው ሰይጣን አፍሮ ተመልሷል:: ቅዱስ አብራኮስ ግን በዚያው ዘመን: በ90 ዓመቱ ዐርፏል::
=>አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ታሕሳስ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መቃርስ ገዳማዊ
2.አባ አብራኮስ ገዳማዊ
3.ብጽዕት ሐና (የእመቤታችን እናት)
4.አባ በጽንፍርዮስ ሰማዕት
5.አባ ሚካኤል ዘቀልሞን
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
5.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
6."13ቱ" ግኁሳን አበው
=>+"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41)
>
https://t.me/zikirekdusn