አምስተኛዉ እጅግ መሠረታዊ የጋራ ችግሮች እያሉብን መከፋፈላችንን ይመለከታል። ከብልፅግና አዉሮፕላን ውጭ ያለን ሰዎች በዋጋ ግሽበቱ ምክንያት መኖር ቸግሮናል። ባለፈዉ ሳምንት ብቻ ነዳጅ በሊትር 11 ብር ገደማ ጨምሯል። ይህ ችግር አማራ-ኦሮሞ፣ ትግራዋይ-ሲዳማ፣ ሶማሌ-አፋር፣ ወላይታ-ጋሞ ወይም ሙስሊም-ክርስቲያን ብሎ ሳይለይ ሁላችንንም ይጎዳል። የሰላም መደፍረሱም በተመሳሳይ የሁላችንን ህይወት ይነካል። ለስድስት ዓመታት የቀጠለዉ የወንድማማች ጦርነት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻችንን፣ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በልቷል። ሀብታችንም በትሪሊዬኖች ባልተገባ ጦርነት ወድሟል። በተለያዩ ቦታዎች በኮሪደር ስም አያሌ ዜጎች ያለምንም ካሳ ከይዞታቸዉ ተፈናቅሏል። የቀይ ባህር ዓሳ በየግዜዉ ችጋርን ለመሸሽ የሚሰደዱ ልጆቻችንን ይመገባል። በእዉነቱ ከሆነ እነዚህ ጉዳዮች -እነፋናን ባያሳስቡም- ሁላችንንም ያለልዩነት ሊያንገበግቡን ይገባል። ይሁንና በትናንሽ አጀንዳዎች ስንጨቃጨቅ ይታያል። ለምን እንደዚህ ይሆናል? ሊያስተባብሩን የሚገቡ ትላልቅ የጋራ አጀንዳዎችና ችግሮች እያሉን ምን ይከፋፍለናል? አሰቀድመዉ አንደነገሩን ፖለቲካ ቁማር ከሆነ እንደህዝብና እንደሀገር እንዳንበላ ራሳችንን ፈትሸን ማረም ይኖርብናል!
©ታየ ደዳዓ
@Showapress
©ታየ ደዳዓ
@Showapress