አንድነት በተውሂድ ነው


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል የተለያዩ ግጥሞች እና ሙሀደራዎች የሚተላለፍበት ቻናል ነው

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🌿 *በጌታህ ታገዝ... አትሳነፍ!!*

🔗 ከአቡሁረይራ በተዘገበ ሀዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፤

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ : ”احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ وَاسْتَعِنْ بِاللهِ وَلَا تَعْجَزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَرٌّ فَلَا تَقُلْ لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا وَكَذَا قُلْ قَدَّرَ اللهُ وَمَا شَاءَ اللهُ فَعَلَ، فَإِنَّ لَوْ تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَان“ رَوَاهُ مُسْلِم
ٌ
«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አትሰላች፤ መጥፎ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ፤ ‘ይህን ነገር እንዲህ ወይም እንዲያ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል


አላህ መልካም ስራን ያግራልን!




Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: Abduselam Ibnu Hassen
أربع ركائز للتاجر المسلم.
=============
قال النبي(ﷺ):-
«أربعٌ إذا كنَّ فيك فلا عليك ما فاتك من الدنيا ، صدْقُ الحديثِ ، و حفْظُ الأمانةِ ، و حُسْنُ الخُلقِ ، وعفَّةُ مَطْعَمٍ»
المصدر: صحيح الجامع:(873 )
للمحدث الألباني: خلاصة حكم المحدث : صحيح
.
-----------------------

አራት የሙስሊም ነጋዴ ካፒታሎች
====================

↪️የሒዲሡ መልእክትወደ አማርኛ ሲመለስ
አራት ነገሮች በውስጥህ ካሉ በዱንያ ላይ ምንም ነገር ቢያመልጥህ ደንታ አይኑርህ፦
① በምታወራ ጊዜ እውነትን መናገር፣
② አማናን መጠበቅ(የፈጣሪን እና የፍጡርን አደራ በአግባቡ መወጣት)፣
③ መልካም ስነ ምግባር (ከፈጣሪና ከፍጡ ጋር ግንኙነትን ማሳመር)
④ በአመጋገብ መጠንቀቅ (ኢምንት እንኳን ሐራም ነገር ወደ ሆድ እንዳይገባ መጠንቀቅ፣ ሐላል በመከስብ ላይ መዋደቅ)።
(ሶሒሑ አልጃሚዑ: 873)

ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድ ሐፊዞሁላህ እነዚህን ነገሮች (አራት የሙስሊም ነጋዴ ዋና ሀብቶች (ካፒታሎች) በማለት ገልፀዋቸዋል
➡️ነጋዴዎች ሲባል የአኼራ ንግድ ላይ የተሰማሩትን ነው።

ሱብሐነላህ! እኛ የት ነው ያለነው?
እስኪ ቆም ብለን እናስብ!!


ብዙዎቻችን ነፃ የሆንን ይመስለናል እንጂ ታስረናል
~
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እስር ቤት ውስጥ ሳሉ እንዲህ ይሉ ነበር፦
المحبوس، من حُبِسَ قلبه عن ربه.
"እስረኛ ማለት ልቡ ከጌታው የታሰረ ነው።" [አልዋቢሉ ሶዪብ፡ 48]

ወደ ጌታው እንዳይቀርብ፣ ትእዛዛቱን እንዳይፈፅም፣ ከክልከላዎቹ እንዳይርቅ በሸይጧን፣ በነፍሲያ፣ በክፉ ጓደኛ የተፈተነና የተሸነፈ ሰው እስረኛ እንጂ ነፃ አይደለም። አዎ ዛሬ ብዙዎቻችን በስልካችን ታስረናል። በሸይጧን ታስረናል። በነፍሲያ ታስረናል። በወዳጅ ታስረናል። በቲቪ ታስረናል። በገንዘባችን ታስረናል። በዱንያዊ ቁሶች ወደ አላህ መቃረብን ከመነፈግ በላይ እስራት አለ? ቁርኣን መቼ ነው የቀራነው? ዚክርስ ትዝ ይለናል? ምላስን መቆጣጠርስ አለ? ሶላታችን ጣእም አለው? ለተቸገረ እጃችን ይፈታል? ገንዘባችን ለአልባሌ ጉዳይ አይወጣም? ለዲናችን አስተዋፅዖ አለን? እኮ እስከመቼ?! አላህ ልብ ይስጠን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor




"ክርስትና"ን የበረዘው ዻውሎስ እና ኢስላምን ሊበርዝ ተነስቶ የነበረው ዓብዱሏህ ኢብኑ ሰበእ


የስላሴ አስተምህሮ መቼ ተነሳ ?!


መጤ ነገሮችን መታገል ግዴታችን ነው!

ከኢርሻድ ደርስ የተቆረጠ



https://t.me/Muhammedsirage








Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




﴿وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ﴾
قال معاذ رضي الله عنه:

العمل الصالح: الذي فيه أربعة أشياء:

العلم، والنية، والصبر، والإخلاص.

📖| البغوي: ١/٢


Forward from: Fuad Mohammed
‏عاجل :

‏رؤية هلال شهر رمضان في سدير..
‏وغداً السبت أول أيام رمضان بالسعودية .
ነገ የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ነው

ምስጋና ለታላቁ አሏህ ይገባል

https://t.me/Muhammedsirage


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ፆም የማያበላሹ ነገሮች
~ ~~
1- የህክምና መርፌ መወጋት፣
2- ምግብ መቅመስ (ከተዋጠ ፆም ያጠፋል)፣
3- የአይን ጠብታ፣ ኩል መኳል፣ የጆሮ ጠብታ፣
4- አካልን ለማቀዝቀዝ መታጠብ፣
5- ሽቶ ወይም በኹር ማሽተት፣
6- መፋቂያ በማንኛውም ሰዓት መጠቀም፣
7- ዋገምት ወይም ሒጀማ (ሚዛን በሚደፋ አቋም ፆም አያበላሽም)
8- ማስታወክ (ሚዛን በሚደፋ አቋም ፆም አያበላሽም። ለምሳሌ ያክል የኢብኑ ሒዛምን ፈትሑል ዐላም ኪታብ ትንታኔ ከገፅ 4/348 - 350 መመልከት ይቻላል።)
9- ለምርመራ ደም መስጠት፣
10- በፊንጢጣ የሚገባ መድሃኒት፣
11- ዝንብ፣ አቧራ ፣ ... ድንገት መግባት፣
12- ምራቅን መዋጥ፣
13- የአስም ህመምተኞች በአፍንጫ የሚጠቀሙት Sprayer

እነዚህ ነገሮች በሙሉ ፆም አያበላሹም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ከዐርሹ በላይ" መፅሀፍ ገበያ ላይ ወጥቷል። አልሐምዱ ሊላህ ቢኒዕመቲሂ ተቲሙ ሷሊሓት።

መገኛ፦ አተውባ መክተባ (አንዋር መስጂድ አጠገብ)
=
https://t.me/IbnuMunewor


ተዉሂድ በአደባባይ

በዉዱ ወንድማችን ሳዳት ከማል

አሏህ ሆይ ወንድማችንን ባለበት ጠብቅልን

በጉራጌ ዞን በአክሊል ወረዳ
ተዉሂድ በአደባባይ

t.me/abu_reyyis_arreyyis/5307
t.me/abu_reyyis_arreyyis/5307





20 last posts shown.