ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ኢጎ
በህይወት ስቃይ ና ችግሮች ውስጥ ስንሆን በችግሮቻችን የበለጠ አቅመቢስነት የሚሰማን እንሆናለን፡፡ በዚህም ከእነዚያ ችግሮች ለማምለጥና ያንን ለማካካስ ራሳችንን ከፍ አድርጎ ማየት እናዳብራለን፡፡ ይህ ራስን ከፍ አድርጎ ማየት ከእነዚህ በአንዱ መንገድ ይሰራል፡፡
1. እኔ በጣም አሪፍ ነኝ ሌሎቻችሁ ግን ደባሪዎች ናችሁ ስለዚህ የተለየ እንክብካቤ ያስፈልገኛል፡፡
2. እኔ የምረባ አይደለሁም ሌሎቻችሁ
ግን አሪፎች ስለሆናችሁ የተለየ እንክብካቤ ያስፈልገኛል የሚሉ ናቸው፡፡
እነዚህ ሀሳቦች በውጪ ሲታዩ ተቃራኒ አስተሳሰብ፣ ውስጡ ግን ተመሳሳይ ራስ ወዳድነት ያለባቸው ናቸው፡፡ በእርግጥ ራሳቸውን ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች በሁለቱ መካከል ሲዋዥቁ ይታያሉ፡፡ ወይ እነርሱ ከአለም ሁሉ በላይ ናቸው አለዚያም ደግሞ አለም ሁሉ ከእነርሱ በላይ ነው፡፡ ይህም መዋዠቅ የሚከሰተው የሆነ ቀን ወይም ያለባቸውን ሱስ እያስታገሱ ባሉባት ቅጽበት ይሆናል፡፡
ብዙ ሰዎች ከንቱ በሆነው ለራሳቸው በሚሰጡት ከፍተኛ ክብር የተነሳ በራሳቸው ፍቅር የወደቁ እንዲሁም በጣም ለፍላፊ በመሆናቸው ከሌላው ሰው በቀላሉ መለየት ይችላሉ።በቀላሉ መለየት የማይችሉት ለራሳቸው ከፍተኛ ክብር የሚሰጡ ሆነው ነገር ግን ዝቅተኛ እንደሆኑና ለአለም የማይጠቅሙ እንደሆኑ የሚሰማቸውን ነው፡፡
በሕይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አንተን ለመጉዳት የሚደረግና ያለማቋረጥ ተጠቂ የሚያደርግህ አድርጎ መተርጎም ልክ ተቃራኒውን እንደማድረግ ያህል ራስ ወዳድነት ነው፡፡ አንደኛው ምንም አይነት ችግር የሌለበት ሆኖ አንደኛው ደግሞ ሊቀረፍ የማይችል ችግር አለበት የሚል እምነት ማዳበር የዚያኑ ያህል በከፍተኛ ደረጃ ከንቱ የሆነ ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ነገር ይፈልጋል፡፡ እውነታው በሕይወት ውስጥ የግል ችግር የሚባል ነገር አለመኖሩ ነው፡፡ የሆነ ችግር ካለብህ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችም ከዚህ ቀደም የዚያ አይነት ችግር ነበረባቸው ወይም አሁን አለባቸው አለበለዚያም ወደፊት ይኖርባቸዋል፡፡ የዚያ ችግር ተጠቂዎች ምናልባትም አንተ የምታውቃቸው ሰዎች ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ይህ መሆኑ ግን ችግሩን አያሳንሰውም ወይም የሚጎዳ የመሆኑን መጠን አይቀንሰውም፡፡ ይህ ማለት በአንዳንድ ሁኔታዎች ተጠቂ ላትሆን ትችላለህ ማለትም ሳይሆን ይህ ማለት አንተ የተለየህ አይደለህም ማለት ነው፡፡
በአብዛኛው ችግሮችን ለመፍታት የመጀመሪያውና በጣም አስፈላጊ የሆነው እርምጃ፣ አንተና የአንተ ችግሮች በችግሮቹ ከባድነት ወይም በሚያስከትሉት ስቃይ ተጠቃሚዎች አለመሆናችሁን መረዳት ነው፡፡
ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ችግር
አንድ ጊዜ ሰዎች በዙሪያቸው የሚከናወነው ሁሉ ራስን ትልቅ አድርጎ የሚያሳይ እንደሆነ ያለማቋረጥ እንዲገምቱ የሚያደርግ አስተሳሰብ ካዳበሩ፣ እነርሱን ከዚያ ውስጥ ሰብሮ ማውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ እነርሱን ለማስረዳት የሚደረግ ሙከራ ሁሉ ለእነርሱ የእነርሱን ታላቅነት፣ ምን ያህል ጎበዝ፣ ተሰጥኦ ያላቸው፣ መልከ መልካሞችና ስኬታማ መሆናቸውን መሸከም ባለመቻል የሚመጣ ጥቃት ተደርጎ ይታያል፡፡
ራሳቸውን ከፍ ያሉ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች፣ በሕይወት ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ሁሉ ለእነርሱ ታላቅነት ወይ አድናቆት ወይ ጥቃት የተሰሩ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ የሆነ ጥሩ ነገር ካጋጠማቸው እነርሱ በሰሩት አሪፍ ነገር ምክንያት ነው፡፡ መጥፎ ነገር ካጋጠማቸው የሆነ ሰው ቀንቶ ሊጎዳቸው ሞክሮ ነው፡፡ ራስን ከፍ አድርጎ ማየት ዘላቂነት የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች የእነርሱን የበላይነት ስሜት በሚያጠናክር በየትኛውም ነገር ራሳቸውን ያሞኛሉ፡፡ ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍልም፣ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች አካላዊና ስሜታዊ ጉዳት የሚያስከትል ቢሆንም የአእምሮ እይታቸውን ይከላከላሉ፡፡
ለራሳቸው ከንቱ የሆነ ከፍተኛ ግምት የሚሰጡ ሰዎች ለራሳቸው ችግሮች በግልፅና በታማኝነት እውቅና መስጠት ስለማይችሉ ህይወታቸውን ዘላቂ ወይም ትርጉም ባለው ሁኔታ ማሻሻል አይችሉም፡፡ እንደዚህ ያሉ ከፍተኛ ክህደት እያሳደዱና ታላላቅ የክህደት ደረጃዎች እያከማቹ ለመኖር የተተው ናቸው፡፡
ግን በመጨረሻ እውነቱ ይወጣና የተቀበሩት ችግሮች ሁሉ እንደገና ራሳቸውን ግልፅ ሲያደረጉ ከባድ የህይወት ምስቅልቅል ውስጥ ይገባሉ።
📚- The subtle art of not giving a f*ck
✍️ - Mark manson
@Zephilosophy