ቁማርተኛው - ፓስካል
ሳንቲምን ወደ ላይ ብታፈናጥር፣ ሳንቲሙ ሰው ባለበት አልያም አንበሳ ገጽ ባለበት ይገለበጣል፡፡ እድሉም ሃምሳ ሃምሳ ነው፤ ሳንቲሙ ችግር ያለበት ወይም ጠማማ ካልሆነ በቀር። ሰው መረጥክ አንበሳ፤ ውጤቱ ላይ እኩል እድል ነው ያለህ:: የእግዚአብሔር ሃለወትስ? እግዚአብሔር ይኑር ወይም አይኑር እርግጠኛ ካልሆንክስ? በዚህ ሃሳብ መቋመር አለብህ? እግዚአብሔር የለም ብለህ ሕይወትህን እንዳሻህ ትመራለህ ወይስ በእግዚአብሔር መኖር አምነህ እንደሱ ፍቃድ ትኖራለህ? ብሌስ ፓስካል (1623-62) የተባለ ክርስቲያን ይህን ሃሳብ ተመራምሮበት ነበር፡፡
ፓስካል የአየር ግፊት መለኪያ የሆነውን ባሮ ሜትርን እና ሜካኒካል ካልኩሌተርን ፈልስፏል፡፡ ልክ እንደ ሳይንቲስትነቱ እና ፈላስፋነቱ ሁሉ፣ ፓስካል ግሩም የሂሳብ ሊቅ ነው፡፡ ከሂሳብ እሳቤዎቹ ውስጥም ይበልጥ የሚታወቀው በይሁንታ (probability) ሃተታዎቹ ነው፡፡ ፓስካል ፈላስፋ ብለን ከምንጠራው ይልቅ የስነ-መለኮት ጠቢብ ብንለው ይወዳል።
እናም ፓስካል በአመንክንዮ አስደግፎ በአምላክ መኖር ማመን እንዳለብን ያስረዳናል። ለእሱ በእግዚአብሔር ማመን የልብ ጉዳይ እንጂ የምክንያት ጉዳይ አይደለም፤ ምንም አይነት ማስረጃም ሊቀርብለት እንደማይችል ያስባል፡፡ እግዜርንም ማወቂያው መንገድ ልብ እንጂ ጭንቅላት አይደለም ይለናል።
እናም እግዜር አለ ወይም የለም በሚሉ ጥርጣሬዎች ሙግት ላይ የትኛው ጋ መቆም እንዳለብን የሚያሳይ አንድ ቁመራ ያሳየናል፡፡ ይህም ቁመራ ልክ እንደ ሳንቲሙ ሁሉ በእድል ላይ ይመሰረታል። አሪፍ ቆማሪ ከሆንክ፣ ሁሌም ቢሆን ከመቋመርህ በፊት ያሉህን እድሎች ትመረምራለህ፤ የሚያከስርህ ከሆነ አትገባበትም፡፡ እና በአምላክ መኖር ላይ እንዴት እንቋመር?
በአምላክ መኖር እርግጠኛ አይደለህም ብለን እናስብ፤ አሁን አማራጮች አሉህ።
ሕይወትህን አምላክ እንደሌለ እርግጠኛ ሆነህ መኖር ትችላለህ፤ እናም ልክ ከሆንክ እድሜ ልክህን ኃጢአት ሰራሁ አልስራሁ ሳትል እና ሳትጨነቅ ትኖራለህ፤ ቤተክርስቲያንም ሄደህ የሶስት ሰዓት ርዝማኔ ያለው ቅዳሴ ላይ የምታጠፋው ጊዜ አይኖርም፡፡ ሆኖም ይሄኛው ምርጫህ ልክ ካልሆነና በአምላክ ሳታምን ከሞትክ፣ ገነት የመግባት እድልህን ከማበላሸት በተጨማሪ ዘላለማዊ በሆነ እሳት ውስጥ ትማገዳለህ፡፡ በዚህ ምርጫህም የሚኖረው የመጨረሻ መጥፎ ነገር ሲዖል መግባት ይሆናል።
በሁለተኛው ምርጫህ፤ አምላክ እንዳለ አምነህ መኖር ትችላለህ። ትጸልያለህ፣ ቤተ-ክርስቲያን ትሄዳለህ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ታነባለህ ወዘተ። እናም እድልህ ሆኖ አምላክ ከኖረ ዘላለማዊ የሆነ ሕይወትን ትሸለማለህ። ነገር ግን ባይሳካልህ እና አምላክ ባይኖር፣ የምትቃጠልበትም ሆነ ቅጣት የምትቀበልበት ሁናቴ አይኖርም፡፡ ከሞትክም ተሳስቼ ነበር ለማለት የሚሆን ጊዜ እንኳ አይኖርህም᎓᎓ ፓስካል ይህን ሃሳቡን እንዲህ ይለዋል “ካሸነፍክ ሁሉንም ታገኛለህ ፤ ከተሸነፍክ ሁሉንም ታጣለህ፡፡''
ፓስካል በአምላክ መኖር ካመንክ እነዚያን ጣፋጭ ኃጢአቶችን እንደምታጣቸው አልጠፋውም፡፡ ሆኖም ደስታን በሃብት እና በዝና ብቻ ማነው ይገኛል ያለው ታማኝ፣ ቅን፣ ትሁት አመስጋኝ፣ ለጋስ፣ መልካም ባልንጀራ እና እውነት በመናገር ውስጥም ደስታ ይገኛል፡፡
እናም የፓስካልን ቁመራ ስናጠቃልለው፤ በአንድ በኩል ያሉት ዘላለማዊ ሕይወት ወይም ገነትን ያገኛሉ፤ በሌላኛው በኩል ያሉት ደግሞ ዘላለማዊ ቅጣት ወይም ሲኦልን ያገኛሉ፡፡ የትኛው ይሻላል? የትኛውንስ ትመርጣለህ?
ፓስካልም፤ “ፈጣሪ የለም ብዬ ሲኦል ከምገባ፣ አለ ብዬ ባይኖር ይሻላል” ይለናል።
እናም ጥሩ ምክንያታዊ እና ጥሩ ቆማሪ ከሆንክ ምርጫህ አምላክ አለ ይሆናል ባይኖርም ምንም አትሆንም፤ ከኖረም ዘላለማዊ ሽልማት ይጠብቅሃል።
ሆኖም ይህ የፓስካል ቁመራ ልክ ነው? ምናልባትም ምርጫህን በአምላክ መኖር ላይ አደረግክ እንበል፤ ሆኖም ውስጥህ ባያምንበት ምን ይፈጠራል? አሁንም ገነት ትገባለህ? ገነትን ለመውረስ ምን ያህል እምነት በአምላክህ ላይ ሊኖርህ ይገባል? ፓስካል ይህን ሲመልስ፣ አንዴ በአምላክ መኖር ካመንክ በኋላ ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመግባት መሞከር ይኖርብሃል። ቤተ-ክርስቲያን ሂድ፣ ጸልይ፣ አትስረቅ፣ አትዋሽ፣ ጠበል ተጠመቅ፣ የኃይማኖት አባቶች የሚሉህን ተከተል ወዘተ...። እናም እውነተኛዋን መንገድ ፍለጋ ስትኳትን፣ እምነትህ እየጠነከረ ይመጣል፤ ወደ አምላክህም ትቀርባለህ። ይህም ዘላለማዊ ሽልማትን የማግኛ እና ከቅጣት የመሸሺያ መንገድ ነው፡፡
ሁሉም ሰው በፓስካል እሳቤ ይስማማል ማለት አንችልም፤ ከፓስካል ቁመራ ካሉት ችግሮች አንዱ አምላክ ቢኖርም ምናልባትም አንተ የእሱ ሰው ላትሆን ትችላለህ። የሚኖረው አምላክስ የማን ነው? የክርስቲያን፣ የሙስሊም፣ የአይሁድ፣ የቡድሂስቶች ወይስ የማን? እንዲያውም የተሳሰተ አምላክን ስታመልክ ከርመህ ዘላለማዊ ሕይወትን ስጠኝ ብትለው፣ ይበልጥ የሚናደድብህ አምላክ ቢሆንስ? ወይም ደሞ ቢኖር እንኳ ሰዎች እንደሚሉት ስለተሳሳትክ ብቻ ሲኦል ውስጥ የሚዶልህ አምላክ ላይሆን ይችላል፡፡ የፓስካል ቁመራ መነሾ የእርሱ አምላክ ልክ እንዲሆን ከመመኘት ይነሳል፤ ሆኖም ለዚህ መልስ አይሰጠንም፡፡ አምነህም ልክ ባልሆነ አምላክ ካመንክ ሲኦል ትገባለህ፤ ወይም ያንተ አምላክ ውሸትን የሚጠላ ከሆነ እና አንድ ቀን ስቶህ ብትዋሽ ሲኦል ትገባለህ፡፡ ፓስካል እንዳሰበው ቁመራው ቀላል አይደለም፡፡
መፅሀፍ- የፍልስፍና ማዕድ
ደራሲ - ሰለሞን
@zephilosophy