አሁንን የመኖር ሀይል
በመጀመሪያ አሁን የጊዜ አካል አይደለም። ጊዜ እንዲኖር ያለፈው ወይም የወደፊቱ መኖር አለበት። አሁን የጊዜ አካል ሳይሆን ዘላለማዊ (eternal) ነው። ልብ ብላቹ ካሰባችሁት ጊዜ ያለው አእምሮአችን ውስጥ ነው፤ ምክንያቱም ምናስባቸው ሀሳቦች በጊዜ ውስጥ ማለትም በባለፈው እና በወደፊቱ ጊዜ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እስኪ ምታስቧቸው ሀሳቦች ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ለማተኮር ሞክሩ፤ ከዚያ አእምሮአችሁ በባለፈው(past) እና በወደፊቱ(future) ላይ ተጠምዶ ታገኙታላቹ።
ስለ አሁን(present) ማሰብ አትችሉም። አሁን ላይ ማሰብ ሳይሆን መኖር (አእምሮ አልባ መሆን) ነው ምትችሉት። እስኪ ስለአሁን ለማሰብ ሞክሩ ምን ሀሳብ ወደ አእምሮአችሁ መጣ? በርግጠኝነት ምንም ማሰብ አልቻላችሁም፤ ስለዚህ ሀሳብ የሚያርፍበት ጊዜ ይፈልጋል ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ምንም የማያስብ ስራፈት ትሆናላችሁ ማለት አይደለም። አሁን ላይ መኖር ስትጀምሩ ከአእምሮአችሁ በላይ መሆን ትጀምራላችሁ። ስለዚህ አእምሮአችሁን ምን ማሰብ እንዳለበት የምትወስኑት እናንተ መሆን ትጀምራላችሁ ማለት ነዉ። ነገር ግን አእምሮ ካለናንተ ፍቃድ በራሱ ማሰብ ያቆማል። አእምሮአችሁ እናንተ ሳትፈልጉ በሀሳብ የሚጠመድ ከሆነ ግን አሁን ላይ እየኖራችሁ አይደለም ማለት ነው።
አሁን ላይ ለመኖር ተደጋጋሚ የተመስጦ (meditation) ልምምድ ያስፈልጋችኃል፤ ምክንያቱም ከአእምሮአችሁ ካልተላቀቃችሁ አሁንን መኖር አትችሉም። ተመስጦ (meditation) ማለት ደግሞ ምንም ሳይሆን እራሳችንን ከአእምሮ ቁጥጥር የምናላቅቅበት መንገድ ማለት ነው። ከአእምሮአችሁ ስትላቀቁ ህይወትን ከዳር ቆማችሁ እንደ ተመልካች መታዘብ ትችላላችሁ።
ህይወትን በሙላት መኖር ከፈለጋችሁ ከኢጎ (ከአእምሮ ቁጥጥር) መላቀቅ ይኖርባችኃል። ኢጎ ከሌሎች የተሻላችሁ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ እና ሌሎችን እንድትጨቁኑ ይነግራችኃል። አለማችን ላይ የምናየው ጦርነት፣ ክፉት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ፅንፍ የወጣ ሀይማኖትን ተገን ያደረገ የሰዎች ጭፍጨፋ በሙሉ የኢጎ ውጤቶች ናቸው። ሁላችንም ውስጥ አይነቱ ይለያይ እንጂ የሆነ አይነት ኢጎ አለ። ኢጎ አሁንን እንዳንኖር የሚገዳደረን ቀንደኛ ጠላታችን ነው።
ሁላችንም ኢጎን አሽቀንጥረን መጣል ይኖርብናል። አለበለዚያ ሰዎች በሰላም የሚኖሩባት የተዋበች ምድር ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን ከኢጎ መላቀቅ እንደምናስበው ቀላል አይደለም። ከህፃንነታችን ጀምሮ የሆነ የኢጎ ማንነት ስንገነባ ኖረናል። ኢጎአችን ትክክለኛ ማንነታችን እስኪመስለን ድረስ ከስብዕናችን ጋር ተጣብቋል። አንዳዶቻችን የብሔር ማንነትን፣ ሀይማኖትን፣ ግለሰባዊ አስተሳሰብን፣ የበላይነት ስሜትን፣ የቆዳ ቀለምን እና የመሳሰሉትን እንደ ተፈጥሮአዊ ማንነት በመቁጠር ከሌሎች ጋር እስከ መጋጨት እና መተላለቅ የሚያደርሱን የኢጎ ገፅታዎች አሉን። እነዚህ ኢጎዎች ከፍ ሲሉ በሀገራት ደረጃ አሁን የምናየውን ጎራ ለይቶ መጠፋፋት ያስከትላል።
አእምሮአችን ህይወትን ውስብስብ አድርጎብናል። ህይወት ግን በጣም ቀላል ናት። አእምሮአችን ማፍቀር አይችልም፤ አእምሮአችን የሚችለው ማስላት ነው። ህይወት አሁን ናት። ከአሁን ወጪ ማድረግ ምትችሉት ነገር አለ? መኖርስ? ያለፈው እና የወደፊቱ ጊዜ ቅዠት ብቻ ናቸው። ያለፈ የምንለው ጊዜ ስንኖርበት አሁን ነበር፤ የወደፊቱም አሁንን ሆኖ ነው ሚመጣዉ። አሁን ላይ መኖር ስትችሉ ከሁለንተና ጋር ትዋሀዳላችሁ።
ብዙ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ለምሳሌ፦ ተራራ መውጣት፣ ከፍተኛ ህመም፣ ከባድ የህይወት ፈተና ሲያጋጥማቸው አሁን ላይ የመገኘትን አጋጣሚ አግኝተዋል። ነገር ግን አሁን ላይ ለመገኘት የግድ እንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎች መጠበቅ የለባችሁም። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ አሁን ላይ መገኘት ትችላላችሁ።
@zephilosophy