ቴሌቭዥን
ምንጭ ፦ አሁናዊ ሀይልን ማግኘት
ትርጉም ፦ ሙሉቀን ታሪኩ
በመላው ዓለም በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ የሚመርጠው መዝናኛ ቲቪ መመልከት ነው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑ አሜሪካውያን ከ60 ዓመት እድሜያቸው 15 ዓመታትን ቲቪ በማየት ያሳልፋሉ። የሌሎች አገራትም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው።
ለብዙዎች ቲቪ መመልከት “ዘና ያደርጋል”። በእርግጥ የቲቪ ስክሪን ላይ አፍጥጣችሁ ሳላችሁ የማሰብ ተግባራችሁ ይቋረጣል። የትኛውም ዓይነት ፕሮግራም ስትመለከቱ አእምሮ ምንም ዓይነት ሃሳብ አያፈልቅም፤ ችግሮቻችሁን ትረሳላችሁ፤ እንዲሁም ለአጭር ጊዜም ቢሆን ከራሳችሁ ነፃ ትሆናላችሁ። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ?
ይህ ማለት ቲቪ መመልከት ውስጣዊ ስፍራን (Inner Space ) ይፈጥራል?አሁናዊ ንቃተ-ኅሊና ላይ ያደርሰናል? በእርግጥ ይህንን አያስችለንም። ቲቪ ስትመለከቱ አእምሮአችሁ ሃሳብ ማመንጨት ቢያቆምም ከቲቪው የሃሳብ ተግባራት ጋር መጣመሩ አይቀሬ ነው። በመሆኑም አእምሮ የቲቪውን ሃሳብ ማሰላሰሉ ይቀጥላል። በቲቪ የሚያየውን ምስልና ድምፅ እየመጠጠ ይመለከታል። ይህም መፍዘዝና የቀረበውን ነገር መቀበልን ያስከትላል። ፖለቲከኞችና የማስታወቂያ ሰዎች ብዙ ሚሊየን ከፍለው በቲቪ የሚጠቀሙት የተመልካቹን ሕዝብ ቀልብ መያዝ ስለሚችሉ ነው። ወይም ሕዝቡ ያለማስተዋል የቀረበለትን ስለሚቀበል ነው። በዚህም ሃሳባቸውን የተመልካቹ ሃሳብ ማድረግ ያስችላቸዋል።
እንደ አልኮልና እፅ ኹሉ ቴሌቭዥን መመልከት ከሃሳብ በላይ መቆም ሳይሆን ከሃሳብ በታች መውደቅ ያስከትላል። ለጊዜው ከአእምሮ ፋታ ቢሰጣችሁም ዋጋ ያስከፍላችኋል። ዋጋው ደግሞ ንቃተ-ኅሊና ማጣት ነው። በዚያ ላይ ደግሞ እንደ እፅ ሁሉ ቲቪም ሱስ ይሆናል። አንዳንዴ ሪሞት አንስታችሁ ቲቪ ለመዝጋት ትዘጋጃላችሁ። ይሁንና ሳታውቁት ለሰዓታት ቻናል እየቀያየራችሁ ታያላችሁ። ጣታችሁ የማይነካው የመዝጊያውን ቁልፍ ብቻ ይሆናል።
የተሻለ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞች መመልከት የቲቪን ተፅዕኖ ለመቀልበስ ያስችላል። አንዳንድ ፕሮግራሞች እጅግ ጠቃሚ ናቸው። የብዙሃንን ሕይወት የቀየሩና ለንቃተ-ኅሊና ያበቁ ይገኛሉ። ኮሜዲ ይዘት ያላቸው ጭውውቶች ሳያስቡት ንቃተ-ኅሊናን ይቀሰቅሳሉ። ኮሜዲ የሰውን ልጅ ኢጎ ማጋለጥ ይችላል። በዚያ ላይ ተመልካቹን እያሳቁ ሕይወትን በቀላል እይታ እንዲመዘን እና ምንም ነገር ከባድ እንዳልሆነ ያሳያሉ። ይሁንና ቲቪ በኢጎ የበላይነት ቁጥጥር ስር ባሉ ሰዎች የሚመራ ኢንዱስትሪ በመሆኑ ድብቅ አጀንዳቸው እናንተን ማስተኛትና ከንቃተ-ኅሊና ማራቅ ነው። ይህም ሆኖ ግን በርካታ ያልተረጋገጡ ጥቅሞች አሉት።
በከፍተኛ ፍጥነት ምስል የሚቀያይሩ ማስታወቂያዎችንና ተመሳሳይ የቲቪ ፕሮግራሞችን አትመልከቱ። የዚህ ዓይነት ትዕይንት ተመልካቹን ለትኩረት ማጣት (attention deficit disorder) ያጋልጣሉ። በመላው ዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት የዚህ ችግር ተጋላጭ የሆኑት በቲቪ ምክንያት ነው። ቲቪ መመልከት ካለባችሁ ግን ዘወትር ውስጣችሁ ንቁ ሆኖ ተመልከቱ። በየመሃሉ ዓይናችሁን ከቲቪው ላይ በማንሳት ረፍት ስጡት። ቲቪውን እንደዘጋችሁት ወደ መኝታ አትሂዱ። በተለይ ደግሞ ቲቪ እያያችሁ በዚያው መተኛት ጉዳት ያስከትላል።
@zephilosophy