"ብሔርተኛነት ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ ነው።"
በብሔርተኛነት ላይ ትችት በማቅረብ የሚታወቁት ኤሪክ ሆብስቦውንን /Eric Hobsbawn/፣ እና ፍራንዝ ፋነንን /Franz Fanon/ የመሳሰሉ ምሁራን እንደሚሉት “ብሔርተኛነት የተካረረ ልዩነትንና ቅራኔን በመፍጠር አንድን ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ አነሳስቶ ስልጣንና ሀብትን ለመቆጣጠር በመሳሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል ርዕዮት ነው። የውጪ ጥራዝ- ነጠቅ ርዕዮት ሰለባ በመሆን ጤናማ የሆነውን የባሕልና የቋንቋ ወይም የብሔር ማንነታችንን አውዳሚ ወደሆነ የፖለቲካ መሳሪያነት በመቀየር አስተሳሳሪ ማንነታችንን በጣጥሰን ጥለነዋል። አሁን በእጃችን ላይ የቀረችው ስጋና ደሟ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ተነጥቃ በአፅመ-ቅሪቷ ብቻ በመኖርና ባለመኖር መካከል እየተንገዳገደች የምትገኘው አገረ-ኢትዮጵያ ነች። አገረ-ኢትዮጵያም የግንባታ ሂደቷ ከመቆምም አልፎ በመቀልበሱ ምክንያትም አሁን የምትገኝበት ደረጃ በከፍተኛ የህልውና የአደጋ ቋፍ ላይ ነው። ዓለም-አቀፍ እውቅና ኖሯት በስምና በካርታ ላይ ከመኖሯ በቀር ለህልውናዋ ዋስትና የሚሰጡ እጅግ ብዙ አስተሳሳሪ እሴቶቿን አጥታለች።
ብሔርተኛነትን በርዕዮትነት እንደማራመድ ለአገር አንድነትና ሰላም ብቻ ሳይሆን ለብሔር-ብሔረሰቦች የእኩልነት መብት መከበርም ፀር የሆነ የፖለቲካ አመለካከት የለም። አንድ ኃይል ራሱን በአንድ ብሔር ስም አደራጅቶ ለፖለቲካ ስልጣን ከታገለና ስልጣን ከያዘ በኋላ የሁሉንም የአገሪቱን ሕዝብ ጥቅምና ፍላጐት የሚያስጠብቅ የእኩልነት ስርዓት ሊመሰርት አይችልም። ብሔር የመሬት ወይም የግዛት ባለቤት ከሆነም ከዚያ ብሔር ውጪ ያሉ ዜጐች መጤና ሁለተኛ ዜጐች ተደርገው ከመታየት ሊድኑ አይችሉም።
በአገራችን በተግባር እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። አልበርት አንስታይን /Albert Einstein/ በጥሩ አባባል እንደገለፀው ብሔርተኛነት “ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ” /Infantile Disease/ ነው።
የኢትዮጵያዊነትን መሸነፍ እንደ ጥሩ ውጤትና ድል በመቁጠር የሚኩራሩ የዘመናችን ብሔርተኞች ብዙዎች ሆነዋል። ይህ መኩራራታቸው የሚመነጨው ግን ብሔርተኛነት ሄዶ ሄዶ የአጥፍቶ-ጠፊነት ውጤት እንደሚያስከትል ካለመረዳት ነው። ጆን ግሬይ /John Gray/፣ በርትራንድ ረስል /Bertrand Russell/፣ ሃናህ አረንት /Hannah Arendt/ እና መሰል ፀሐፍት እንደሚሉት “የብሔርተኝነት ትግል ሲጀመር በፍጥነት የሚያድግና የሚጠናከር ሲሆን፣ በሒደት ግን በውስጡ በሚፈጥረው የጥላቻና የመከፋፈል አዙሪት ባልተቋረጠ ሁኔታ እየተበተነና እየተዳከመ የሚሄድ ነው። ብሔርተኛነት በቆየና የበለጠ በተጠናከረ ቁጥር ሁሉጊዜ የሚፈጥረው ሌላ ከሱ የባሰ ጠባብና አክራሪ ብሔርተኛነትን ነው። ከዚህ የተለየ ሌላ የእድገት ዑደት የለውም። እድገቱ ቁልቁል ነጓጅ /Degenerative/ ሒደት ነው።
አንድ ጊዜ የጋራ መተሳሰሪያችን ከሆነው ከኢትዮጵያዊነት ወይም ከዜግነት ማንነታችን መነቀል ከጀመርን በኋላ አሁን ላይ ንዑስ-ብሔርተኞች ሲሉ እንደሚሰማው ከብሔር ማንነታችን አውርዳችሁ አድዋና ተንቤን፣ ወለጋና አርሲ፣ ወይም ጎንደርና ጎጃም ወዘተ... ብላችሁ አትከፋፍሉን ብሎ ሌሎችን ማማረር ትርጉም የለውም። እንዲህ ዓይነቱ አባባል የብሔር ፖለቲካን መነሻ እንጂ መድረሻን አስቀድሞ ካለማወቅ የሚመነጭ ድክመት ነው። በዜግነት ደረጃ ያልጠበቅነውን መተሳሰር ወደ ብሔር ደረጃ ከወረድን በኋላ አስጠብቀን የማስቀጠል ዋስትና ሊኖረን አይችልም። አንድ ጊዜ የብሔርተኛነት ፖለቲካን የተለማመደ ሕዝብም የራሴ የሚለውን አገር ከመመስረት ባነሰ በሌላ ማናቸውም ዓይነት ውጤት የመርካት ዕድል የለውም። ሁልጊዜም ብሶተኛ፣ ነጭናጫና ጠባጫሪ ሆኖ የሚኖር ነው።
ተዋቂው ፀሀፊ ኤሪክ ሆፈር /Eric Hoffer/ እንደሚለው፣ “ማንኛውም የግለሰቦችን መብት ለቡድን ጥያቄ አሳልፎ የሚሰጥ የቡድን እንቅስቃሴ ሕዝብን ለጊዜው በብሶት፣ በስሜትና በጥላቻ ከማነሳሳት ባለፈ አገርንና ስርዓትን በጋራ የመገንባትና የማስቀጠል ሚና የለውም”። ባለፉት 33 ዓመታት በአገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ሲሆን እንደታየው የብሔር “ነፃ አውጪ” ድርጅቶች ዕጣ-ፈንታ እየተበተኑ ከመሄድ የተለየ አልሆነም። የራሳቸውንም ሆነ “ነፃ እናወጣሀለን” የሚሉትን ሕዝብ ሕይወት ከመኖር ወደ አለመኖር ሲቀይሩት እንጂ ችግሩን ሲፈቱለት አልታዬም። የኦነግ፣ የብአዴን፣ የኦህዴድም ሆነ የ50 ዓመታቱ የሕወሓት የብሄርተኛነት ጉዞ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ብሔርተኛነትን በአገር ደረጃ በፖለቲካ ርዕዮትነት ማራመድ ከጀመርን በኋላ በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መጠን በሚሊየኖች ስንፈናቀልና በጭካኔ ስንጨፈጨፍ በገሃድ እያየንም ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ የተለየና አዲስ መፍትሄ ማሰብ አልቻልንም። በመረረ ጥላቻ፣ በአጉል እልህና ፉክክር ሕሊናችን ስለተጋረደ “የጅል ዘዬ ሁሌ አበባዬ”እንዲሉ ዛሬም “ብሔርተኝነት ወይም ሞት!” በማለት የጥፋቱን መንገድ የበለጠ አጠናክረን ቀጥለንበታል።
ከልደቱ አያሌው ገፅ የተወሰደ
@zephilosophy