ኢጎ የአእምሮ በሽታ ነው
✍️ኤካህርት ቶሌ
አዕምሮአዊ ቀውሶች የተገነቡት በማንኛውም ጤናማ ሠው ላይ በሚሰሩ ተመሳሳይ ኢጎአዊ ባህሪዎች ነው። ልዩነቱ ከሚሰቃየው ሠው በቀር ለሌላው ሠው ሁሉ እጅግ ጎልተው መታየታቸውና በሽታዊ ባህሪያቸው ግልፅ መሆኑ ነው።ለምሳሌ፣ ጤናማ የሚባሉ ሠዎች በጣም አስፈላጊ መስለው ለመታየትና የተለዩ ለመምሰል በሌሎች አዕምሮ ውስጥ ያላቸውን ምስል ለማጎልበት እገሌን አውቀዋለሁ ፣ አንዲህ ነገር አሳክቻለሁ፣ ይህን እችላለሁ፣ይሄ አለኝ እና ማንኛውንም ኢጎ ሊዛመድበት የሚችለውን ነገር በመጠቀም በየጊዜው ይዋሻሉ። አንዳንዶች ደግሞ እንዲሁ በኢጎ የጎዶሎነት ስሜት እና የማግኘት ወይም ተጨማሪ ብዙ በሚለው ፍላጎቱ ተነድተው፣ እንደ ልምድ ከፍቃዳቸው ውጪ ይዋሻሉ። ስለራሳቸው የሚናገሩት ብዙ ነገር (ታሪካቸው)፣ ባጠቃላይ ምኞትና ኢጎ ታላቅና ልዩ ለመሆን ለራሱ የቀመረው ምናብ ነው። ለራሳቸው የፈጠሩት አስደማሚና የተጋነነ ምስል፣ ለጊዜው ሌሎችን ሊያጃጅል ይችላል። ትንሽ ቆይቶ ግን የፈጠራ ታሪክ እንደሆነ በብዙዎች ይደረስበታል።
ፓራኖይድ እስኪዞፍሬኒያ ወይም ባጭሩ ፓራኖያ እየተባለ የሚታወቀው የአዕምሮ በሽታ፣ በመሰረቱ የኢጎ የተጋነነ ገፅታ ነው። በአብዛኛው የተገነባው አዕምሮ ከጀርባው ለሚሰማው ጠንካራ ፍራቻ ትርጉም ለመስጠት በፈጠረው ምናባዊ ታሪክ ነው። የታሪኩ ዋናው ክፍል፣ የሆኑ ሠዎች (አንዳንዴም ብዙ ሠው ወይም ሁሉም ሰው) በኔ ላይ ሊያሴሩብኝ ነው” ወይም “እኔን ለመቆጣጠር ወይም ለመግደል እያደቡ ነው” የሚል እምነት ነው።
ተረኩ ወጥነት ያለውና ምክንያታዊ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንዴ ሌሎችን ሰዎች እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል። አንዳንዴ ድርጅቶችና አገሮችም ጭምር ከስራቸው የዚሁ የፓራኖይድ ሲስተም እምነት አላቸው። “የኢጎ ፍራቻና ሌላውን አለማመን፣ የሌሎችን “ሌላነት” በሚያየው ስህተታቸውና ይህንንም ስህተት ማንነታቸው በማድረግ ላይ ትኩረት መስጠት ባህሪው ምክንያት፣ የተወሰነ እርምጃ በመውሰድ ሌሎችን ኢ-ሰብዓዊ ጭራቆች ያደርጋል።
ኢጎህ እየጠነከረ ሲመጣ፣ ሌሎች ሠዎች የህይወትህ ዋነኛ ችግሮች እንደሆኑ ወደማመኑ ትመጣለህ። አንተ ደግሞ ይበልጡኑ ለሌሎች ህይወትን ከባድ ታደርግባቸዋለህ።.. በርግጥ ይህንን መመልከት አትችልም። ሁልጊዜ የሚሰማህ ሌሎች አንተ ላይ እያደረጉ እንደሆነ ነው።
ፓራኖያ የምንለው የምንለው የአዕምሮ በሽታ፣ በሁሉም ኢጎ ላይ የሚታይ ሌሎች መገለጫዎች አሉት። ምንም እንኳ በፖራኖያ ላይ በጣም የጎላ ቢሆንም። በሽተኛው እራሱን በሌሎች እንደሚጨቆን፣እንደሚሰለል፣ እንደሚያስፈራሩት ሲያይ ሁሉም ነገር በሱ ዛቢያ እንደሚሽከረከር፣ የብዙ ሠዎችን ትኩረት የሳበ ምናባዊ ቁልፍ ሠው እንደሆነ በማሰብ፣ ልዩና አስፈላጊ ሠው እንደሆነ የተጋነነ ማንነት ስሜት ይሰማዋል። የተበዳይነት ስሜቱና ብዙዎች በስህተት ተመለከተውኛል ማለቱ በጣም ልዩ እንደሆነ እንዲሰማው ያደርገዋል። ቅዠታዊ መዋቅሩን በፈጠረው ታሪክ ውስጥ እራሱን የሚመለከተው ኣንድም እንደተበዳይ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ አለምን ለማዳን ወይም እነዚህን የጥፋት ሃይሎች ለማሸነፍ አቅም እንዳለው ጀግና ሠው ነው።
@Zephilosophy