TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

21 May, 11:04

Open in Telegram Share Report

.....✍ካለፈው የቀጠለ

ዘመናዊነት እና ድህረ ዘመናዊነት (modernity and postmodernity)

የዘመናዊነት እሳቤዎች

ከመካከለኛው ዘመን ተነስተን፣ በዘመነ ትንሳኤና በአብርሆት በኩል አልፈን ዘመናዊነት ላይ ደርሰናል፡፡ ይሄም ባጠቃላይ የአውሮፓ የ1500 ዓመታት የሐሳብ ታሪክ (History of Ideas) ነው፡፡ እነዚህ ዘመናት ሲመሩበት የነበረውን ዋነኛ ጭብጥ መግለፅ ካስፈለገ፣ እንዲህ በማለት ማስቀመጥ ይቻላል፤

👉መካከለኛው ዘመን - የክርስትና አስተምህሮ የበላይነት የነበረበት፣

👉ዘመነ ትንሳኤ – የጥንት ግሪክና ሮማውያን ሥነ ፅሁፍ ንቅናቄ፣
👉ዘመነ አብርሆት - ነፃነት (ከውጫዊ ስልጣኖች - ባህል፣ አጉል እምነትና ዘውድ ነፃ መሆን)፣

👉ዘመናዊነት - ምክንያታዊ ማህበረሰብ ግንባታ፣ ምክንያታዊነት እያደገ ሲሄድ ደግሞ የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ እየተሻሻለ ይሄዳል የሚል ተስፋ፤

‹‹ዘመናዊነት›› ምክንያታዊ የሆነ የማህበረሰብ ግንባታ ከሆነ ሂደቱ የጀመረው ቀደም ብሎ ነው ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ይሄንን ሂደት ‹‹ከዘመነ ትንሳኤ ጀምሮ የመጣ ነው›› ይሉታል፡፡ ሌሎች ምሁራን ደግሞ ‹‹ዘመናዊነት ‹‹የጥንቱን ባህል ማንሰራራት›› የሚለው የዘመነ ትንሳኤ ርዕይ ከተሳካ በኋላ የመጣ ቀጣዩ ፕሮጅክት ነው›› በማለት ይገልፁታል፡፡ በዚህ ትርጉም ከሄድን ‹‹ዘመነ አብርሆት›› የዘመናዊነት አካል ይሆናል ማለት ነው፤ ምክንያቱም ‹‹የአብርሆት እሴቶች ግልፅና ጉልህ ሆነው የወጡት በዘመናዊነት ነው፡፡

ዘመናዊነትን በአውሮፓ ለተከሰተው አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የተሰጠ የአመለካከት ግብረ መልስ አድርገው የሚመለከቱትም አሉ፡፡ ይሄም አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የሚገለፀው በዘመናዊ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የብሔር መንግስታት መመስረት፣ በገንዘብ ኢኮኖሚ፣ በካፒታሊዝም እና በኢንዱስትሪ መስፋፋት ነው፡፡ ይሄም አዲስ ነባራዊ ሁኔታ በህጎች፣ በመመሪያዎች፣ በመለኪያዎችና በቁጥሮች የሚመራ ቢሮክራሲና የህይወት ዘይቤ እንዲኖር አድርጓል፡፡ ከዚህም በመነሳት ነው ጀርመናዊው ሶሲዮሎጂስት ማክስ ቬበር (Max Weber) ‹‹ዘመናዊነት ማለት በህጎች፣ በመመሪያዎች፣ በመለኪያዎች፣ በቁጥሮችና በቢሮክራሲ የሚመራ የህይወት ዘይቤ ነው›› በማለት ትርጉም የሰጠው፡፡

በአጠቃላይ ዘመናዊነት

💡በድሮው ላይ ማመፅ ነው፤ ይሄም አመፅ ጎጂና ኋላ ቀር ከሆኑ የድሮው (የመካከለኛው ዘመን) ልማድ፣ አሰራርና አስተሳሰብ መነጠልን የሚያመላክት ነው፤ ከእነሱም ተነጥሎም ህይወትን በዕውቀትና በአመክንዮ መዘወር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በዘመናዊነት ውስጥ ‹‹ድርቅ የተከሰተው የሰው ኃጢያት ስለበዛና እግዚአብሔር ስለተቆጣ ነው›› አይባልም፤ በዘመናዊነት ውስጥ ‹‹በሽታ የሰይጣን ሥራ ነው›› አይባልም፤ ‹‹እንደዚህ የሆንኩት የ40 ቀን ዕድሌ ስለሆነ ነው›› አይባልም፡፡ በዘመናዊነት ውስጥ ከእንደነዚህ ዓይነት አስተሳሰቦች እንነጠልና፣ የምናምነው ሳይንስ የሚነግረንን የመንስኤ ውጤት ህግጋትን ነው፡፡

💡የፕ/ር መሳይ ከበደን ‹‹ዘመናዊነት ማለት ከድሮው ባህልና አስተሳሰብ መነጠል ሳይሆን፣ እንዲያውም የድሮው ባህሎችና እሴቶች እንደገና እንዲያብቡ ማድረግ ነው››የሚለውን ሐሳብ ከወሰድን ደግሞ ‹‹ዘመናዊነት ማለት ለጥንት ባህላችንና እሴቶቻችን አዲስ አመክኖያዊ መሰረት መስጠትና ዘመናዊ አሰራርን ማላበስ ነው›› በማለት መተርጎም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፣ የዘመን መለወጫ በዓል በጣም የቆየ ባህል ነው፡፡ በበዓሉ ውስጥ እርድ፣ ጠላ መጥመቅ፣ ዳቦ መድፋት፣ ባህላዊ ልብሶች መልበስ፣ ቤተ ዘመድ መሰባሰብ፣ አንድላይ መመገብ...ይከናወናል፡፡ በዘመናዊነት ውስጥ ይሄንን ባህል አልተውነውም፤ እንዲያውም የበዓሉን አከባበር በዘመን አመጣሽ አልባሳት፣ ምርቶችና የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በመጠቀም በዓሉን ይበልጥ ደማቅ እየሆነ ነው፡፡

የድህረ ዘመናዊነት እሳቤዎች

ከ1970ዎቹ ጀምሮ የተነሳው ድህረ ዘመናዊነት ሁለት መገለጫዎች አሉት፡፡

✍በአንድ በኩል፣ አሁን በተጫባጩ ዓለም ላይ ያለውን እውነታ የምናሳይበት መንገድ አድርገን ልንመለከተው እንችላለን፡፡

✍በሌላ በኩል ደግሞ፣ ድህረ-ዘመናዊነት ‹‹ሞደርኒቲ ከሽፏል፤ አልፎበታል›› የሚል አስተሳሰብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ሊዮታርድ ‹‹The Postmodern Condition: A Report on Knowledge›› በተሰኘ መጽሐፉ ውስጥ ድህረ-ዘመናዊነትን ሲተረጉመው እንዲህ ይላል፣

‹‹ድህረ-ዘመናዊነት በታላላቅ ትረካዎች አለማመን ነው

በዘመናዊነት ውስጥ የነገሮችን ተፈጥሮ እና ምንነት የምንረዳባቸው እንዲሁም እውነትን፣ ዕውቀትንና ግብረገብነትን የተመለከቱ ህይወታችንን የምንመራባቸው ቅቡል የሆኑ ታላላቅ ትረካዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ የዘመናዊነት ትረካዎች ውስጥ የተወሰኑት እንዲህ የሚሉ ናቸው፣

👉ሁሉንም ሰው የሚያስማማ እውነት አለ (There is Universal Truth)፤

👉ሁሉንም ሰው የሚያስማማ ሥነ ምግባር አለ (There is Universal Morality)፤

👉ዕውቀት ማግኘት ደስተኛ ያደርጋል፤

👉ዕውቀት ማግኘት ነጻነት ያለው ህይወት እንድንኖር ያደርገናል፤

ድህረ-ዘመናዊነት እንደነዚህ ዓይነቶችን ትረካ አይቀበልም፡፡ በመሆኑም፣ ድህረ- ዘመናዊነት ማለት፣

✍በእነዚህ የዘመናዊነት ትረካዎች የማናምንበትና የማንስማማበት፣

✍ሰዎችን ሁሉ እኩል በሆነ መንገድ የሚያስማማ የጋራ እውነት የሌለበት፣

✍እውነትና ሥነ ምግባር አንፃራዊ የሆኑበት፣

✍ሰዎች ሁሉ ትክክል የሆኑበት፣

✍ሁሉም ባህሎችና ሃይማኖቶች ትክክል የሆኑበት፤

✍ሰዎች እውነትን ገሃዱ ዓለምውስጥ ወጥተው የሚፈልጉበት ሳይሆን በዲስኩር፣ በቋንቋና በፖለቲካ ላይ ተሞርኩዘው የእውነትን ተፈጥሮ የሚረዱበት አዲስ ዓለምነው፡፡

በዘመናዊነት እና በድህረ-ዘመናዊነት አስተሳሰብ መካከል ያለውን ልዩነት የሚከተለውን ጥያቄ በማንሳት ማየት እንችላለን፡፡

💡አንድ ማህበረሰብውስጥ አላዋቂነት መኖሩ ነው ማህበረሰቡ እንዳይዘምን የሚያደርገው (The sleep of reason produces monsters)? ወይስ

💡የአዋቂዎች መብዛት ነው ማህበረሰቡ ውስጥ ችግር የሚፈጥረው (The dream of reason produces monsters)?

የመጀመሪያው፣ ‹‹አንድ ማህበረሰብ ውስጥ አላዋቂነት መኖሩ ነው ችግር የሚያመጣው የሚለው አስተሳሰብ ‹‹የሰው ልጅ የበለጠ ለባህልና ለሃይማኖት ራሱን በሰጠ ቁጥር፣የሰው ልጅ በዘፈቀደ ህይወቱን በመራ ቁጥር ነጻነትን ማግኘት አይችልም፣ ደስተኛ ህይወትን መምራት አይችልም››ወደሚል ድምዳሜ ይወስደናል፡፡ እንደ ካንትና ሄግል ያሉ ፈላስፎች ይሄንን አስተሳሰብ ተከትለው ነው ዘመናዊነት ምን እንደሆነ የሚነግሩን፡፡

ሁለተኛው፣ የድህረ-ዘመናዊነት ፍልስፍናን የሚያቀነቅኑ ፈላስፎች ደግሞ በተቃራኒው የሚሉን ‹‹የአዋቂዎች መብዛት ነው ማህበረሰቡ ውስጥ ችግር የሚፈጥረው፡፡ ይሄም ማለት በጣም ማለምም፣ በጣም መጠየቅም፣ በጣም ዘመናዊ መሆንና ምክኒያታዊነትን ማዳበርም አንድ ማህበረሰብ ውስጥ ተቃርኖን ይፈለፍላል፡፡ ለዚህ መደምደሚያ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ሉላዊ በሆነው ዓለም ውስጥ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተመንድጓል በምንልበት፣ የግለሰብ ነፃነት እስከ ጥግ በደረሰበትና ቁሳዊ ዕድገት ባለበት ዓለም ውስጥ እንደ ጀኖሳይድ እና ሆሎኮስት ያሉ እልቂቶች፣ የእርስበርስና የዓለም ጦርነቶች እንዲሁም የህይወት ትርጉም አልባ ስሜቶች ውስጥ መዘፈቃችን ነው፡፡

@zephilosophy

እስኪ እናንተ ጋርስ ያለው ሀሳብ ምንድነው ተወያዩበት👇👇👇

10.5k 0 28 5 54
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot