2.መጽሐፍ ቅዱስ ከህዋ አንፃር የሰው ልጅ ምንድን ነው? በማለት ይጠይቃል?
“የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፣
ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፣
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?”
በማለት መዝሙረኛው ንጉስ ዳዊት ይጠይቃል፡፡
መዝሙረኛው ያነሳው ጥያቄ የዚህ ምዕራፍ ርዕስ ጉዳይ ነው፡፡ ሰው ተፈጥሯዊ የሆነ የአጋጣሚ ክስተት ውጤት ነው ወይስ ታላቅ አላማ ለማሳካት የተፈጠረ ልዩ ፍጥረት? ሰው በተፈጥሮ ሂደት በአጋጣሚ የተገኘ ቢሆንና የፍጥረታት ሁሉ የበላይና የመጨረሻ ግብ ሁኖ ሊወሰድ ይችላልን? ከፀሐይና ከጨረቃ-ከህዋ-አንፃር ሲታይስ እዚህ ግባ የማይባል ተፈጥሯዊ ማንነት ያለው ከብናኝ አፈር፣ በእግራችን ረግጠን እንደምንገድላቸው ትናንሽ ነፍሳት አይነት የሆነ ተራ ፍጥረት ነውን ወይስ በህዋ ውስጥ ያሉትን ነገሮች እንደፍላጐቱ ማድረግ የሚችል ኃያል ፍጥረት? ህዋ ለሰው ጥቅምና መልካም ግልጋሎት ተብሎ የተፈጠረ ነገር ነውን ወይስ መጥፋያው? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ አይነት ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ ሁለት አይነት ነው፡፡ በአንድ በኩል የሰውን ኃያልነት ሲያጐላ በሌላ በኩል ተራ ፍጥረት መሆኑን ይነግረናል፡፡ መለኮታዊ ማንነት ያለውና በፍጥረታት ሁሉ ላይ ገዥነቱን የሚነግረን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዳለ ሁሉ በሌሎች ክፍሎች ደግሞ ሰውን አዋርዶና አቅልሎ ይነግረናል፡፡ የሰውን ልዩ ማንነትና ገዥነቱን መዝሙረኛው ዳዊት እንዲህ በማለት ይገልፀዋል፡፡
“ከመላዕክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፣
በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው፣
በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፣
ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፣.."
ከጥቅሱ መረዳት እንደሚቻለው ሰው ከመላዕክት አንሶ የማያንስ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ተሹሞ ዘውድ የደፋ ታላቅ ፍጥረት ነው፡፡ የሰው ታላቅነት ከአፈጣጠሩ ልዩ መሆን ይጀምራል፤ በእግዚአብሔር መልክ (በልጁ መልክ) የተፈጠረና የመለኮት ባህሪ ተካፋይ የሆነ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጅ ሌላ ማንነት ይሰጠዋል፡፡ ከሌሎች ፍጥረታት የማይለይ ይባስ ብሎ ከሌሎች ፍጥረታት አሣንሶ ሰውን ይገልፀዋል፡፡ መጽሐፈ መክብብ እንዲህ ይላል፡፡
“እኔ በልቤ ስለሰው ልጆች እንደ እንስሳ መሆናቸውን እንዲያዩ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል አልሁ፡፡ የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፣ ድርሻቸውም ትክክል ነው፡፡ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፣ የሁለም እስትንፋስ አንድ ነው፣ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፡፡”
መጽሐፈ ኢዮብ ደግሞ የሰውን ማንነት ከዚህ በባሰ መልኩ ይገልፀዋል፡፡
“እነሆ፣ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደሉም፣
ክዋክብትም በፊቱ ንጹሀን አይደሉም፣
ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው
ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ፡፡”
ፍልስፍናስ ምን ይላል? ፍልስፍና ትኩረት ከሚሰጥባቸው ጉዳዮች አንዱና ዋናው የሰውና የህዋ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ፍልስፍና ሰፋፊ፣ ጥልቀትና ብዛት ያላቸው አስተሳሰቦችን አቅርቧል። በቀጣይ እናያለን....
@zephilosophy