የዘመናዊ ፍልስፍና ሙግቶች
የቀጠለ
....የዳሳሽነት (empiricism) ፍልስፍናን ያራመዱ የብሪታንያ ፈላስፋዎች ሰውን የሁሉ ነገር ማዕከል አድርገው የተረዱ ቢሆንም ከሰው አሳቤ ውጭ ህዋ የራሱ የሆነ ህልውና የለውም በማለት ህዋንና ሰውን ያስተሳሰረውን ገመድ ቆርጠው ጣሉት፡፡ በርክሌይ የተባለው ፈላስፋ ቁሳዊ ነገሮች ከሰው ህሳቤ ውጭ ህልውና የላቸውም ማለቱና የስሜት ህዋሳቶች መረጃዎች መገኛቸው ቁሳዊ ነገሮች ሣይሆኑ እግዚአብሔር ነው ማለቱ የሳይንስን መሠረት የሆነውንና ሰው ማንነቱ ሊገለጽበት የሚችለው ቁስ አካል ከንቱ (ዋጋ የሌለው) ነገር ሁኖ እነዲታሰብ አደረገው፡፡ ይባስ ብሎ ዴቭድ ሂዩም የሰው ልጅ የስሜቶችና የሀሳቦች መንሸራሸሪያ መንገድ ከመሆን ውጭ ሌላ ማንነት የለውም፤ የህዋን (የቁስ አካላት) ህልውናንም ማረጋገጥ አይቻልም በማለቱ በፍልስፍና ተሟሙቆ የነበረው የሰውን ኃያልነት የማሳየት አስተሳሰብ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸለሰበት፡፡
ሌሎች ደግሞ የህዋን ህልውና ሙሉ በሙሉ ሀሳባዊ አደረጉት፡፡ እንጀ ሜልብራንች ያሉ ፈላስፋዎች (Malebranche) እኛ የምናውቀው እግዚአብሔር የገለፀልንን ነው፤ እርሱ ከሰጠን ሃሳብ ውጭ ምንም የምናውቀው ነገር የለም የሚል እምነት ያዙ፡፡ ሜልብራንች ሲናገር “እግዚአብሔር ዓለምን ቢያጠፋና አሁን እንዲሰማኝ እንዳዳረገኝ ወደፊትም እንዲሰማኝ ቢያደረገኝ ወደፊት የማየው አሁን የማየውን ነው፡፡” በሌላ አገላለጽ ይህ ማለት “እግዚአብሔር ዓለምን ቢያጠፋ ነገር ግን ልክ አሁን እንደሚሰማኝ (እንዳልጠፋች አድርጐ እንዳስብ ቢያደርገኝ) የማስበው ወይም የምረዳው መጥፋቷን ሣይሆን መኖሯን ነው፡፡የሚል ራሱን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ሀሳብ ብቻ እንደሆነ አድርጐ እንዲያስብ የሚያስችል አመለካከት ያራምድ ነበር።
በዘመናዊ ፍልስፍና የታዩ አንዳንድ ፈላስፋዎች ደግሞ ከጊዜው ነባራዊ ሁኔታ ውጭ ሆነውና የሣይንስን መንገድ ስተው የሰውን ልጅ ወደ ጥንታዊ ኑሮው ለመመለስ የሚከጅል ሀሳብ ማራመድ ጀመሩ፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው የዣን -ዣክ ሩሶ (Rousseau) ፍልስፍና ነው፡፡ ሩሶ እንደሚለው ሣይንስ የተፈጥሮ ህግ እውቀት ነው፤ ሳይንስ የሰውን ልጅ ኑሮ ይምራ ማለት ሰው በህግ ይመራ ማለት ነው፡፡ ሳይንስ ሰውን በህግ አስሮ መያዝ ይፈልጋል፡፡ ሰው ግን እንደፈቃዱና ስሜቱ መኖር የሚሻ ፍጥረት ነው፡፡ ሳይንስና ሳይንስ ያመጣቸው ስልጣኔዎች ግን የሰውን ልጅ ነፃነት የሚጋፉ በመሆናቸው አያስፈልጉም የሚል እምነት ማራመድ ጀመረ፡፡
ከላይ የተመለከትናቸውን ፍልስፍናዎች አጠቃለን ስናያቸው ዘመናዊ ፍልስፍና መስመር ይዞ መራመድና ወጥ የሆነ አቋም መያዝ እንደተሳነው መረዳት እንችላለን፡፡ በአንድ በኩል የሰውን ልጅ የበላይ አድርጐ ሲመለከት በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔርን በሰው ዘር ህሊና ላይ ይሾማል፤ አንዳንዴ ደግሞ ሰው ስለራሱም ሆነ ስለሚኖርበት ዓለም እንዲጠራጠር ሲያደርግ በሌላ በኩል ደግሞ ሰውን የራሱ የሥራ ውጤት ከሆነው ሥልጣኔ አርቆ ተፈጥሯዊ ኑሮ ብቻ መኖር ወደ ሚችልበት ወደ ተፈጥሮአዊነት ኑሮ መመለስ ይሻለዋል የሚል ሙግት ውስጥ ገባ፡፡
ኢማኑየል ካንት እንደብሪታንያ ፈላስፋዎች ሁሉ ሰው የሚረዳው የራሱን ሃሳብ ነው የሚል እምነት ቢኖረውም በምክንያታዊ አስተሳሰብ ሰው ከራሱ ውጭ የሆነ ቁሳዊ ዓለም መኖሩን፣ የእግዚአብሔርን ህልውናም ሆነ ዘላለማዊነት እና ነፃነት አለ ብሎ እንዲያምን አስችሎታል በማለት አሣወቀ፡፡ እነዚህ እምነቶች ደግሞ ተግባራዊ የሆነ ሥነ ምግባራዊ ኑሮና ሌላም አይነት ማኀበራዊ ህይወት እንዲኖርና ራሱንም ከተፈጥሮ በላይ አድርጐ እንዲያስብ አስችሎታል የሚል መደምደሚያ ሃሳብ ላይ ደረሰ፡፡ ይህን የመሰለው የካንት አስተሳሰብ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሰውን በህዋ ላይ ያለውን የበላይነትና ክብር የመመለስ አስተሳሰብ ሁኖ ተወሰደ፡፡
በካንት መጫሚያ እግራቸውን ያስገቡ ሌሎች የጀርመን ፈላስፋዎች የሰውን ልጅ በህዋ ውስጥ ያለው መንፈሳዊና ህሊናዊ ኃይል ወራሽ በማድረግ ከቁስ አካላትና ከሌሎችም ፍጥረታት ሁሉ በላይ የሆነ ማንነት ያለው መሆኑን የሚያመለክት ጥልቅና ረቂቅ የሆነ ሀሳባዊ ፍልስፍና አቀረቡ፡፡ ካንትን ተከትለው የመጡ እንደ ሩዶልፍ ኸርማን ሎዝ፣ ሼልንግና ሄግል አይነት ፈላስፋዎች ህዋና ሰውን በአንድ አይናቸው የተመለከቱ ፈላስፋዎች ናቸው፡፡ ህዋ ለእነዚህ ፈላስፋዎች ህያው ነው፤ ህሊናዊ ነው፤ ሁልጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ ለመሸጋገር የሚንቀሳቀስ ነገር ነው፡፡ በዚህ ህሊናዊ የለውጥ ሂደት ህዋ የራሱን የመጨረሻ የዕድገት ደረጃ የደረሰው በሰው ነው፡፡ ህዋ ሙሉ የሚሆነውና ራሱን የሚያውቀው በሰው ነው፡፡ ለእነዚህ ፈላስፋዎች ሰው ማለት ትንሽ ህዋ ነው፡፡
ከብዙ ፍልስፍና ሀሳቦች በጥቂቱ ስንቃኘው የህዋና የሰው ግንኙነት በፈላስፋዎች ዘንድ ይኼን የመሰለ አስተሳሰብ ፈጥሯል፡፡ በእኛም ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቀላል አይሆንም፡፡ በህዋ ውስጥ ሰው ያለው ቦታ ለመወሰንና በሰውና በህዋ መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ከውዝግብ የፀዳና የማያሻማ መልስ ማግኘት ባንችልም ርዕሰ ጉዳዩን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሰፋ አድርገን እንድንመለከተው የሚያስችል ሃሳቦችን አግኝተናል ።
ረ/ፕርፌሰር ዋለልኝ እምሩ
@zephilosophy