ብቸኛው ባለቅኔ
ካህሊል ጂብራን
ለጋስነት በልቤ ውስጥ ተዘርታለች። ክምር ስንዴ አመረትኩ ፤ ለተራቡም አካፈልኩ። ነብሴ ለወይን ፍሬ ትሰጣለች፡፡ ወይኑን ጨምቄ ለተጠሙ አጠጣሁ። ፋኖሴን ዘይት ሞልቼ መስኮቴ ጋር አኖርኩኝ። በጭለማ ለሚጓዙ እንግዶች መንገዱን አበራሁ፡፡ ይህንን ሁሉ የማደርገው በእነዚህ ድርጊቶቼ ውስጥ ስለምኖር ነው። የሕይወት እጣ ለጋስ እጆቼን ብታስርበኝ ሞትን እመርጣለሁ። ገጣሚ ነኝና መለገስ ካልቻልኩ ፈፅሞ አልቀበልም። የሰው ልጅ ቁጣ እንደ አውሎ ነፋስ ያጓራል። እኔ ግን በዝምታ እተነፍሳለሁ፡፡ ምክንያቱም ትንፋሼ ፈጣሪ ጋር ሲደርስ ወጀቡ በሙሉ ይቆማልና። ሰዎች ምድራዊ ነገሮች ላይ ይንጠለጠላሉ፡፡ የኔ መሻት ግን የፍቅር ችቦ ናት። በብርሃኗ የልቤን ሰብአዊነት ታነፃልኛለች፡፡ ሰዎች በዘር ፣ በቀለም በሃይማኖት ተከፋፍለዋል። እኔ ደግሞ በሁሉም አገር እንግዳ ነኝ – የየትኛውም ወገን አይደለሁም፡፡ ሥነ-ፍጥረት (ዩኒቨርስ) አገሬ ስትሆን ጉሳዬ ደግሞ ሁሉም የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ አቅመቢስ ሆነውም የተከፋፈሉ ናቸው። በየጊዜው የምትጠበውን ምድር በግዛትና አገራት መሰነጣጠቅ አላዋቂነት ነው። የሰው ልጆች እጅ ለእጅ የሚያያዙት የነፍስን ቤተ መቅደስ ለማፍረስና ምድራዊ ድልድይ ለመገንባት ብቻ ነው። ብቻየን ቆሜ እንዲህ የሚል የውስጥ ድምፄ ተሰማኝ ፡
#ፍቅር ለሰው ልብ ሕይወት እንደምትሰጥ ሁሉ አለማወቅን ማወቅ ደግሞ የእውቀትን መንገድ ያሳየዋል። ፍቅርና አለማወቅን መረዳት ወደ ታላቅ ደስታ ይመራሉ– ምክንያቱም ፈጣሪ ከፀሀይ በታች ለሰው ልጅ መከራን አልፈጠረምና።
@Zephilosophy