ኢጎ እና የአሁኑ ቅፅበት
የአሁኑ ቅፅበት ወዳጅህ አድርገህ መወሰን የኢጎ ፍፃሜ ነው። ኢጎ በአሁኑ ቅፅበት ማለትም ከህይወት ጋር አንድ መሆን አይችልም። ምክንያቱም የኢጎ ተፈጥሮ እራሱ አሁንን ቸል የማለት፣ የመቃወምና፣ ዋጋ ያለመስጠት ነው። ኢጎ የሚኖረው በጊዜ ውስጥ ነው። ኢጎ ብርቱ ከሆነ፣ በህይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። እናም አብዛኛው የምታስበው ሃሳብ ካለፈው ጊዜ እና ከመፃኢው ጊዜ ጋር የተገናኘ ይሆናል። በዚህም የማንነት ስሜትህ፣ ማንነትህን ካለፈው ጊዜ ይቀዳል። ሙላትህን ደግሞ ከመፃኢው ጊዜ ይጠብቃል። ፍርሀት፣ ድብርት፣ ጥበቃ፣ ቁጭት፣ ፀፀት፣ ንዴት በጊዜ የተገደበው ህላዌ ብልሹነቶች ናቸው።
ኢጎ የአሁኑን ቅፅበት የሚያስተናግድበት ሶስት መንገዶች አሉት። እነዚህም፣ ለሆነ ግብ እንደ መረማመጃ፣ እንደ እንቅፋት ወይም እንደ ጠላት ናቸው። እነዚህ ልምዶች ሲነሱ እንድታስተውልና መልሰህም መወሰን እንድትችል፣ እያንዳንዳቸውን እንፈትሻቸው።
1.ለኢጎ የአሁኑ ቅፅበት የተሻለ ከተባለ፣ ሊሆን የሚችለው ለሆነ ግብ እንደ መረማመጃ ሲሆን ነው። ምንም እንኳን መፃኢ ጊዜ እራሱ በአእምሮ ውስጥ ከሃሳብነት ያልዘለለ፣ ሲመጣም የአሁን ቅፅበት ሆኖ ከመምጣት ውጪ መሆን የማይችል ቢሆንም፣ የአሁኑ ቅፅበት ግን በጣም አስፈላጊ ተደርጎ ለሚወሰደው መፃኢ ጊዜ እንደመረማመጃ ተደርጎ ይወሰዳል። በሌላ አገላለፅ ሌላ ጊዜ ላይ ለመሆን በጣም ከመጣደፍ የተነሳ፣ አሁንን በደንብ መኖር አትችልም።
2.ይህ ልምድ እጅግ ሲጎላ ደግሞ (የተለመደም ነው) ፣ የአሁኑ ቅፅበት ሊቀረፍ እንደሚገባ እንቅፋት ተደርጎ ይወሰዳል። በዘመናችን አኗኗር፣ በየሰው የእለት ኑሮ ውስጥ ጥድፊያ፣ ሰቀቀን እና ጭንቀት የሚነሱትና መደበኛ ሁኔታ የሆኑትም ለዚሁ ነዉ። ህይወት ማለትም አሁን እንደ "ችግር" ታይቷል፣ እናም ከመደሰትህ፣ በትክክል መኖር ከመጀመርህ በፊት ልትፈታቸው የሚገቡ ብዙ ችግሮችን ማኖር ትጀምራለህ። ችግሩ ግን ፣ አንድ ችግር በፈታህ ቁጥር ፣ ሌላ ችግር ደግሞ ብቅ ይላል። የአሁኑ ቅፅበት እንደ እክል እስከታየ ድረስ፣ ችግሮች ፍፃሜ አይኖራቸውም።
3.ሌላው በጣም የከፋና በጣም የተለመደው ደግሞ፣ የአሁኑን ቅፅበት እንደ ጠላት ማየት ነው። የምትሰራውን ስራ ስትጠላ፣ አካባቢህን ስታማርር፣ የሚከሰተውንና የተከሰተውን ነገር ስትረግም፣ ወይም ከራስህ ጋር የምታወራው ነገር በነበርና ባልነበር ሲሞላ፣ ስትወቅስና ስትወነጅል፣ ከሚከሰተው ነገር ጋር ስትጣላ፣ ሁሌም ቢሆን ከዚያ ውጪ መሆን ከማይችለው ክስተት ጋር ስትጣላ፤ ህይወትን ጠላት እያደረክ ነው፤ ህይወትም "የምትፈልገው ጦርነት ነው፣ የምታገኘውም ጦርነት ነው" ትልሀለች።
ከአሁኑ ቅፅበት ጋር ያለህን ብልሹ ግንኙነት እንዴት መቀየር ትችላለህ? በጣም አስፈላጊው ነገር፣ ራስህን፣ ሃሳቦችህንና ድርጊቶችህን መመልከት ነው። በምትመለከትበት ጊዜ፣ ከአሁን ጋር ያለህ ግንኙነት ብልሹ እንደሆነ በምታስተውልበት ጊዜ፣ ህላዌህ ውስጥ ነህ። ተመልካቹ፣ በውስጥህ የሚያንሰራራው ህላዌ ነው። ብልሹነቱን ባየህበት ቅፅበት፣ ብልሹነቱ መክሰም ይጀምራል።
👉 ከወሰን ባሻገር መሆን
ንቁ ከሆንክ፣ ትኩረትህ በአሁን ላይ ብቻ ከሆነ፣ ያ ህላዌ በምትሰራው ስራ ላይ ይፈስና ለውጥ ይፈጥራል። በዚያ ውስጥ ጥራትና ሀይል አለ። የምትሰራው ነገር፣ በዋናነት ለሆነ ግብ (ገንዘብ፣ ክብር፣ አሸናፊነት) መረማመጃ ካልሆነ፤ ይልቁንም በራሱ ምሉዕ ከሆነ፣ በምትሰራው ላይ ሀሴት እና ህያዉነት አለ፤ በህላዌህ ውስጥ ነህ። እንዲሁም ከአሁኑ ቅፅበት ጋር ወዳጅነት ካልፈጠርክ በቀር፣ ህላዌ ውስጥ አትሆንም። የተፈጠርነው ገደብን ለመኖር ብቻ ሳይሆን ከገደብ ባሻገር በመጓዝ በሕላዌያችን እንድናብብ ጭምር ነው።
መፅሀፍ፦ አዲስ ምድር
ደራሲ፦ ኤክሀርት ቶሌ
@Zephilosophy