Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
እውነተኛ ሱኒይ የሆነ ሰው የቢድዐ ሰው ሲነካ አይቆጣም!!
—————
እውነተኛና በአላህ ዲን ላይ ፅናት ያለው ሱኒይ (ሰለፊይ) የሆነ ሰው ለየትኛውም ስሜታዊ (ቢድዐና ሙብተዲዕ) ለሆነ አካል መነካት አይቆጣም!!።
ሁመይድ ኢብኑ ሙንሂብ (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው አባበክር ኢብን ዐያሽን እንዲህ ብሎ ሲጠይቀው ሰምቻለሁ አለ:- “አባበክር ሆይ! ሱኒይ ማለት ማን ነው? አባበክርም እንደሚከተለው መለሱ:- ስለ ስሜት (የስሜት ባለ ቤት በክፉ) ሲጠቀስ አንዳችም የማይወግን የሆነ አካል ነው። አሉ” [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱና አላለካኢይ 1/82]
በአሽ-ሸሪዐህ ዘገባ አቡበክር ኢብኑ ዐያሽ እንዲህ ብለዋል:- “ሱኒይ ማለት እርሱ ፊት ስለ ቢድዐ ሲወሳ የማይቆጣ ነው።” [አሽ-ሸሪዐህ ሊል ኣጁሪ 5/550]
ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ አካል ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ አላህ እርም ያደረጋቸው ነገሮች ሲደፈሩ ይቆጣል!!። ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ ሰው ስለ ሺርክና ቢድዐ ባለ ቤቶች ከመናገር ተቆጥበናል አይልም!!።
ኢብኑ ዐሳኪር - ረሂመሁላህ - ታሪኹ ዲመሽቅ በተሰኘው ኪታባቸው ከዑቅባ ኢብኑ ዐልቀመህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ የሚል ዘግቧል:- “አርጣአ ኢብኑል ሙንዚር ዘንድ ነበርኩና ከተቀማመጡ ሰዎች ከፊላቸው እንዲህ አለ:- ከሱና ሰዎች ጋር የሚቀማመጥና የሚቀላቀል ሆኖ ሳለ፣ ስለ ቢድዐ ሰዎች ሲወሳ ደግሞ ተውን! ስለነሱ እዚህ አታውሩ። የሚል ስለሆነ ሰው ምንትላላችሁ? አለ፣ አርጠአ ኢንዲህ በማለት መለሰ:- እሱ ከነርሱ ጋር ነው (ከቢድዐ ሰዎች ነው) የእርሱን ነገር አያምታታባችሁ፣ አለ። አልቀማ - ረሂመሁላህ- የአርጠአን ንግግር በወቅቱ አልተቀበልኩትምና ወደ ታላቁ ሰለፍ ኢማሙል አውዛዒይ - ረሂመሁላህ- ዘንድ ሄድኩኝ አሉ። አውዛዒይ ደግሞ እንዲህ ያለ ነገር ከደረሰው ግልፅልፅ የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ የነበረው ገላጭ ሰው ነበር። (ጉዳዩን ሳወሳለትም) አውዛዒይ:- አርጠአ እውነት አለ፣ (የተናገረው እውነት ነው)፣ ይህ ስለነሱ ከመናገር ይከለክላልን?፣ ታዲያ እነሱን በመጥቀስ ጠንከር ካልተባለ መች ነው ከነሱ ማስጠንቀቅ የሚቻለው?!።” [ታሪኹ ዲመሽቅ 8/15]
ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “አንድ ሰው ከቢድዐ ባለቤት ጋር ሲጓዝ አይተሀው፣ (የዚያን የቢድዐ ሰው) አስተሳሰብ እንደማይቀበለው በመሃላ አስረግጦ ቢነግርህ እንኳ እውነት ብለህ አትቀበለው!።”
አቡ ሷሊህ አል-ፈራእ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:- ለዩሱፍ ኢብኑ አስባጥ ስለ ወኪዕ አንስቼ የተወሰነች ስለተከሰተች ፊትና አወራሁት፣ ይህን ጊዜ ዩሱፍ እሱ ራሱ እንደ ኡስታዙ ነው አለኝ፣ (ኡስታዙ ሀሰን ኢብኑ ሀይን) ማለቱ ነው። ለዩሱፍም መልሼ ይህ ሀሜት እንዳይሆን አትፈራም? አልኩት፣ አንተ ሞኝ እንዴት ሀሜት ይሆናል?፣ እኔ እኮ ለእነዚህ ከወላጆቻቸው የበለጠ መልካም ነኝ!፣ እኔ እነሱ በፈጠሩት አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሰዎች ተከትለዋቸው እንዳይሰሩበትና በወንጀሉም ተጠያቂ እንዳይሆኑ ነው የምከላከለው፣ እነሱን ከፍ ከፍ እያደረገ የሚያወድሳቸው ሰው በነሱ ላይ እጅግ በጣም አደገኛ ነው!፣ አለ።” [አስ-ሰይር 7/364]
✍🏻 ኢብን ሽፋ: ረመዷን 14/1442 ዓ. ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን 👇👇 #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa