{በቢድዓና በቢድዓ ሰዎች ላይ ምላሽ}


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የተለያዩ "በቢድዓና በቢድዓ ሰዎች" ላይ የሚሰጡ ምላሾች በፅሁፍና በድምፅ የሚገኝበት ቻናል ነው።
ቢድዓንና የቢድዓ ሰዎችን ለማህበረ ሰቡ ግልፅ ማድረግ ማህበረሰቡን ከተለያዩ የጥመት አንጃዎች መታደግ ነው! በዚህ ላይም የተለያዩ የሱና ዳዒዎች ትልቅ ሀላፍትና እንዳለባቸው ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል!
አላህ ሆይ ሀቅን አመላክተን መከተሉንም ወፍቀን!!!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
እውነተኛ ሱኒይ የሆነ ሰው የቢድዐ ሰው ሲነካ አይቆጣም!!
—————
እውነተኛና በአላህ ዲን ላይ ፅናት ያለው ሱኒይ (ሰለፊይ) የሆነ ሰው ለየትኛውም ስሜታዊ (ቢድዐና ሙብተዲዕ) ለሆነ አካል መነካት አይቆጣም!!።

ሁመይድ ኢብኑ ሙንሂብ (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው አባበክር ኢብን ዐያሽን እንዲህ ብሎ ሲጠይቀው ሰምቻለሁ አለ:- “አባበክር ሆይ! ሱኒይ ማለት ማን ነው? አባበክርም እንደሚከተለው መለሱ:- ስለ ስሜት (የስሜት ባለ ቤት በክፉ) ሲጠቀስ አንዳችም የማይወግን የሆነ አካል ነው። አሉ” [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱና አላለካኢይ 1/82]

በአሽ-ሸሪዐህ ዘገባ አቡበክር ኢብኑ ዐያሽ እንዲህ ብለዋል:- “ሱኒይ ማለት እርሱ ፊት ስለ ቢድዐ ሲወሳ የማይቆጣ ነው።” [አሽ-ሸሪዐህ ሊል ኣጁሪ 5/550]

ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ አካል ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ አላህ እርም ያደረጋቸው ነገሮች ሲደፈሩ ይቆጣል!!። ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ ሰው ስለ ሺርክና ቢድዐ ባለ ቤቶች ከመናገር ተቆጥበናል አይልም!!።
ኢብኑ ዐሳኪር - ረሂመሁላህ - ታሪኹ ዲመሽቅ በተሰኘው ኪታባቸው ከዑቅባ ኢብኑ ዐልቀመህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ የሚል ዘግቧል:- “አርጣአ ኢብኑል ሙንዚር ዘንድ ነበርኩና ከተቀማመጡ ሰዎች ከፊላቸው እንዲህ አለ:- ከሱና ሰዎች ጋር የሚቀማመጥና የሚቀላቀል ሆኖ ሳለ፣ ስለ ቢድዐ ሰዎች ሲወሳ ደግሞ ተውን! ስለነሱ እዚህ አታውሩ። የሚል ስለሆነ ሰው ምንትላላችሁ? አለ፣ አርጠአ ኢንዲህ በማለት መለሰ:- እሱ ከነርሱ ጋር ነው (ከቢድዐ ሰዎች ነው) የእርሱን ነገር አያምታታባችሁ፣ አለ። አልቀማ - ረሂመሁላህ- የአርጠአን ንግግር በወቅቱ አልተቀበልኩትምና ወደ ታላቁ ሰለፍ ኢማሙል አውዛዒይ - ረሂመሁላህ- ዘንድ ሄድኩኝ አሉ። አውዛዒይ ደግሞ እንዲህ ያለ ነገር ከደረሰው ግልፅልፅ የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ የነበረው ገላጭ ሰው ነበር። (ጉዳዩን ሳወሳለትም) አውዛዒይ:- አርጠአ እውነት አለ፣ (የተናገረው እውነት ነው)፣ ይህ ስለነሱ ከመናገር ይከለክላልን?፣ ታዲያ እነሱን በመጥቀስ ጠንከር ካልተባለ መች ነው ከነሱ ማስጠንቀቅ የሚቻለው?!።” [ታሪኹ ዲመሽቅ 8/15]

ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “አንድ ሰው ከቢድዐ ባለቤት ጋር ሲጓዝ አይተሀው፣ (የዚያን የቢድዐ ሰው) አስተሳሰብ እንደማይቀበለው በመሃላ አስረግጦ ቢነግርህ እንኳ እውነት ብለህ አትቀበለው!።”

አቡ ሷሊህ አል-ፈራእ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:- ለዩሱፍ ኢብኑ አስባጥ ስለ ወኪዕ አንስቼ የተወሰነች ስለተከሰተች ፊትና አወራሁት፣ ይህን ጊዜ ዩሱፍ እሱ ራሱ እንደ ኡስታዙ ነው አለኝ፣ (ኡስታዙ ሀሰን ኢብኑ ሀይን) ማለቱ ነው። ለዩሱፍም መልሼ ይህ ሀሜት እንዳይሆን አትፈራም? አልኩት፣ አንተ ሞኝ እንዴት ሀሜት ይሆናል?፣ እኔ እኮ ለእነዚህ ከወላጆቻቸው የበለጠ መልካም ነኝ!፣ እኔ እነሱ በፈጠሩት አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሰዎች ተከትለዋቸው እንዳይሰሩበትና በወንጀሉም ተጠያቂ እንዳይሆኑ ነው የምከላከለው፣ እነሱን ከፍ ከፍ እያደረገ የሚያወድሳቸው ሰው በነሱ ላይ እጅግ በጣም አደገኛ ነው!፣ አለ።” [አስ-ሰይር 7/364]
✍🏻 ኢብን ሽፋ: ረመዷን 14/1442 ዓ. ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን 👇👇 #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
አዲስ ወሳኝ ተከታታይ ሙሓዶራ ወሳኝ በሆኑ ርእሶች!!

ክፍል 4⃣

ርዕስ:- ከሙብተዲዕዎች ጋር መቀማመጥ የሚያሳድረው ተፅእኖ እና የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ተጨባጭና አመራሮቹ ሙብተዲዕ ስለመሆናቸው።

🎙🎙በሸይኽ ሐሰን ገላው (ሀፊዞሁሏህ)

የድምፅ ፋይሉን በሚከተለው 👇👇 ሊንክ ያገኙታል
https://t.me/IbnShifa/1367

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa


"ታላቅ ዲናዊ ኮርስ በጎንደር ከተማ"

በትራንስፖርት አለመመቻቸት ምክንያት በጎንደር ከተማ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሸይኽ አብዱልሐሚድ ያሲን አልለተምይ "ሃፊዞሁሏህ" ሊሰጥ የነበረው ኮርስ ተዘርዞ እንደነበር የሚታወስ ነው ሆኖም በአላህ ፈቃድ የፊታችን ጁሙዓ መጋቢት 03/ 2013 ከሰዓት በኋላ ጅማሮውን አድርጎ አስከ እሁድ መጋቢት 05/2013 ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ኮርሱን የሚሰጡት ፡- ታዋቂው ዓሊም ሸይኽ ዓብዱልሐሚድ ያሲን (አልለተምይ) - ሃፊዞሁሏህ - ይሆናሉ፡፡

ኮርሱ ፡- ሸይኽ ሙሐመድ ጀሚል ዘይኑ - ረሂመሁሏህ - “አቂደቱል ኢስላምያ ሚነልኪታቢ ወስ'ሱናህ” በሚል ርዕስ ባዘጋጁት አጭር የጥያቄና መልስ ኪታብ ዙሪያ ይሆናል፡፡

ኮርሱ የሚካሄደው ፡- “በመስጅድ አስ'ሱናህ”
አድራሻ፡- ቀበሌ 10 ብሪጋታ መውረጃ ጎን

ማሳሰቢያ ፡- - በዚህ ኮርስ ወንዶችም ሴቶችም መሳተፍ ይችላሉ፡፡

#ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በዝግጅቱ ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉና ለምትችሉ ሁሉ ይህ ታላቅ አጋጣሚ እንዳያልፋችሁ

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


የቢድዓ ሰዎች ላይ ሊኖረን የሚገባ አቋም እና
ጥቂት ነገሮች ከሰላሳ ምክሮች

ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር
t.me/Muhammedsirage


MuhammedSirage M.NUR

"በእኛ እና በአሕባሾች መካከል"

ተከታታይ ትምህርት

ክፍል 1-

الرحمن على العرش استوى
ወይስ
الله موجود بلا مكان ؟!

43 ደቂቃ ያህል ነው
السلفية
https://t.me/Muhammedsirage


Forward from: Bahiru Teka
🔊 ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም
በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ኮሰድ ቀበሌ
የፊታችን ማክሰኞ ጥር 11/2013 በተጠቀሰው ቀበሌ ታላቅ የተውሒድ ዳዕዋ አዘጋጅተናል
በኮሮና ምክንያት ከዳዕዋ የራቀው ማህበረሰባችን በጣም አስከፊ በሆነ የቀብር አምልኮ ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል በአላህ ፈቃድ ይህ ፕሮግራም የተውሒድን ብርሃን ፈንጥቆ የሽርክን ፅልመት የሚገፍ ይሆናል
ፕሮግራሙ የሚጀመረው
ከጠዋቱ 2 : 30 ላይ ይሆናል
በፕሮግራሙ ላይ የሚሳተፉት
እንግዶቻችን
የሱናና የተውሒድ ነበልባል የሚተፉት
ታላቁ የሱና ሸይኻችን
አሽሸይኽ ዐ/ ሐሚድ አልለተሚ
ወንድማችን ሚስባሕ ሙሐመድ
ወንድማችሁ ባሕሩ ተካ
አላህ በተባለው ቀን
በተባለው ቦታ በተውሒድ ማእድ ያገናኘን
http://t.me/bahruteka


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የውይይት ጥሪ ለአሕባሾች
~
① ጠሪ: –

አቡ ዒምራን ሙሐመድ ሲራጅ
እና
ኢብኑ ሙነወር

② የጥሪው አድማስ:–

ለሁሉም አሕባሾች። ሰሞኑን "እንወያይ" ሲሉ የነበሩትን ሀቢብ እና ወሂድን ጨምሮ እስከነ ዑመር "ኮምቦልቻ" … ባጭሩ ለሁሉም።
(ማሳሰቢያ:- ንፅፅር ላይ የሚሰራው ወሒድ ዑመር አይደለም።)

③ የውይይት ርእስ:–

"አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን እያከፈራችሁ ስለሆነ የምንጀምረው በዚህ የ"ኢስቲዋእ" ርእስ ነው። ይህንን ለመቋጨት ከበቃን እንደ "ኢስቲጋሣህ" ባሉ ሌሎች ወሳኝ ርእሶች እንቀጥላለን።

④ የውይይት መስፈርት: –

✅ ማስረጃዎች ከቁርኣን፣ ከሐዲሥ እና ነቢዩ ﷺ ምርጥነታቸውን ከመሰከሩላቸው ቀደምት ትውልዶች ንግግር ብቻ‼
✅ ይሄ ከጠበበባችሁስ?! በዚህ ምክንያት እንድትሸሹ አንፈልግም። እኛ:–

👉🏾 በሰለፎች አካሄድ ተገድባችሁ መሟገት አትችሉም ብለን ስለምናምን፣
👉🏾 በዚህ ምክንያት ከውይይቱ እንድትሸሹም ስለማንፈልግ፣
👉🏾 "እንከተላቸዋለን" ከምትሏቸው አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ፈፅሞ እንደማትገናኙ ማጋለጥም ስለምንሻ
እስከ አቡል ሐሰን ዘመነ–ህልፈት #ድረስ ያሉ ዓሊሞችን #ብቻ እንድታጣቅሱ እንስማማለን። ከዚያ በኋላ #ፈፅሞ አይሆንም።

✅ በዚህ ዘመን የምንገድብበት ምክንያት:–

1⃣ ውይይቱ ልጓም የለሽ ሆኖ እንዳይለጠጥ ለመወሰን፣
2⃣ እምነታችሁ ከጊዜ በኋላ የመጣ እንጂ የዚያ ምርጥ ዘመን ትውልድ እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
3⃣ ዐቂዳችሁ "ኢማማችን" የምትሉት አቡል ሐሰንም እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
4⃣ "አላህ ከዐርሽ በላይ ነው" የሚለው ዐቂዳ "የወሃቢዮች ዐቂዳ ነው" በማለት መጤ አስተሳሰብ በማስመሰል ነጭ ውሸት በመንዛት ህዝብ እያደናገራችሁ ስለሆነ

በተቃራኒው ይህ "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚለው እምነት በቁርኣንና በሐዲሥ የፀና፣ እነዚያ ምርጥ ትውልዶች የተጓዙበት፣ እንዲሁም የነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ጭምር ዐቂዳህ እንደሆነ ለማሳየት ርእሱን መገደብ ግድ ብሏል።

⑤ የውይይቱ ቦታ:–

ቴሌግራም ላይ በዚህ ግሩፕ ይሆናል:–
👇🏾
https://t.me/IbnuMuneworsb

🔊 መልእክቱን አዳርሱልን። ምናልባት ፈቃደኛ ሆኖ የሚቀርብ ሊኖር ይችላልና።


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ ረሒመሁላ፞ህ በስድብ፣ በማንቋሸሽ እና በመቅጠፍ ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ሲገጥማቸው እንዲህ ይሉ ነበር:–

"የላቀው አላህ በኔ ሰበብ አንድንም ሰው እሳት እንዳያስገባ እማፀነዋለሁ።"

ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ይቅርታቸውን ፈልጎ ወደሳቸው ሊመጣ እንደሆነ ሲነገራቸውም "ይቅርታ ለመጠየቅ መምጣት አያስፈልግም። እኔ ሁሉንም ሰው ይቅር ብያለሁ" ይሉ ነበር። አብረዋቸው ለሚሆኑ ሰዎችም ይህንን እንዲያደርሱ ይጠይቁ ነበር።
[ሸርሑል ኡሱሊ ሠላሣህ: 17–18]
~
እኛስ? ታሪኩን ያመጣሁት እንድንማርበት ነው። እስኪ እራሳችንን እንታዘብ። በደል የፈፀመብን፣ ክብራችንን ያጎደፈን ሰው ሳይጠይቀን ይቅር ማለቱ ቀርቶ ከልቡ እየለመነንስ ይቅር እንላለን ወይ? ለብዙዎቻችን ይሄ ከባድ ነው። የአፀፋ ዘመቻ ውስጥ የሚገባው ብዙ ነው። ጉዳዩ ከደዕዋ ወይም ከዱዓት ጋር ሲያያዝ ደግሞ ኸይሩም ሸሩም ለሌሎችም ይተርፋል።
(ٱلَّذِینَ یُنفِقُونَ فِی ٱلسَّرَّاۤءِ وَٱلضَّرَّاۤءِ وَٱلۡكَـٰظِمِینَ ٱلۡغَیۡظَ وَٱلۡعَافِینَ عَنِ ٱلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ یُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِینَ)
"ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡"
[ኣሉ ዒምራን: 134]

(وَلَا یَأۡتَلِ أُو۟لُوا۟ ٱلۡفَضۡلِ مِنكُمۡ وَٱلسَّعَةِ أَن یُؤۡتُوۤا۟ أُو۟لِی ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡمَسَـٰكِینَ وَٱلۡمُهَـٰجِرِینَ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِۖ وَلۡیَعۡفُوا۟ وَلۡیَصۡفَحُوۤا۟ۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن یَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورࣱ رَّحِیمٌ)

"ከእናንተም የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የሆኑት ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆች በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ላይሰጡ አይማሉ፡፡ ይቅርታም ያድርጉ፡፡ (ጥፋተኞቹን) ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡" [አነሕል: 22]
~~~
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱ ምኞቶች
~~~~~~~~~~~~~
(یَـٰلَیۡتَنِی كُنتُ مَعَهُمۡ فَأَفُوزَ فَوۡزًا عَظِیمࣰا)
«ዋ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አኒሳእ: 73]

(یَـٰلَیۡتَنِی لَمۡ أُشۡرِكۡ بِرَبِّیۤ أَحَدࣰا)
«ዋ ምኞቴ! በጌታዬ አንድም ባላጋራሁ!» [አልከህፍ: 42]


(وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا)

በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
[አልፉርቃን: 27]


(وَأَمَّا مَنۡ أُوتِیَ كِتَـٰبَهُۥ بِشِمَالِهِۦ فَیَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی لَمۡ أُوتَ كِتَـٰبِیَهۡ)
መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡ [አልሐቃህ: 25]

~~~~
ዛሬ ልንደርስባቸው የሚቻሉ የሙታን ምኞቶች ናቸው። ጊዜው ሳያልፍ ቶሎ እራሳችንን እናስተካክል። አላህ ሆይ! ልባችንን ከመዘንጋት አንቃልን። ሕይወታችንን በሂዳያ ብርሃን አብራልን።

የተተረጎመ
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ታ) በተመለከተ እነዚህን ቢድዐዎች፣ እነዚህን ነገሮች ስለሚያስፈፅም ከሆነ የሚሰጠው የሚቀበለው ነገር አስቀያሚ መሆኑ አይሰወርም። እነዚህን ነገሮች ምንም ሳይፈፅም እንዲሁ በዚህ ጊዜ የሚሰጠው ከሆነ ኢብኑ ሐቢብ ‘ለአስተማሪ በሙስሊሞች ዒድ ምንም አይወሰንለትም - ይህን መስራቱ የሚወደድ ቢሆን እንኳን’ ብለዋል። … ኢብኑ ሐቢብ ሸሪዐዊ በሆኑ በዓላት ላይ እንዲህ ካለ ሸሪዐዊ ባልሆኑት ላይ እንዴት ሊሆን ነው?!” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዒ ወተሶውፍ፡ 128-129]
5. አልኢማም አቡ ኢስሓቅ አሻጢቢ ረሑመሁላህ (790 ሂ.)፡-
መውሊድን ከተቃወሙ የስምንተኛው ክ/ዘመን ዐለማኦች ውስጥ አንዱ ሻጢቢ ናቸው። ሻጢቢ በቢድዐ ላይ የተሰላ ሰይፍ ነበሩ። “አልኢዕቲሷም” የተሰኘው ዳጎስ ያለ ስራቸው ቢድዐን እርቃኑን ያስቀረና ዛሬም ድረስ የቢድዐ አጋፊሪዎችን ምቾት እንደነሳ ነው። መውሊድን በተመለከተ ኢማሙ ሻጢቢ እውነትን ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ መልእክት ያዘለ ቅልብጭ ያለ ፈትዋ ሰጥተዋል። ይሄውና፡- “ሰዎች ዘንድ በተለመደው መልኩ የሚከበረው መውሊድ መጤ የሆነ ቢድዐ መሆኑ የታወቀ ነው። ቢድዐ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። ስለሆነም ቢድዐን ለመፈፀም ገንዘብን መለገስ አይፈቀድም። በዚህ ላይ ኑዛዜ ከተላለፈም ተፈፃሚ አይደለም። እንዲያውም ቃዲው ሊያፈርሰው ይገባል።…” [ፈታዋ ሻጢቢ፡ 203-204]
በተጨማሪም ስለቢድዐ ምንነት ካብራሩ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አሁንም ከነሱ (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሚካተተው (በዒባዳ ውስጥ) ተለይተው የተወሰኑ አፈፃፀሞችንና ሁኔታዎችን በቋሚነት መያዝ ነው። ለምሳሌ በአንድ ድምፅ በመሰባሰብ የሚደረግ ዚክር፣ የነብዩን - ﷺ - ልደት ቀን በዓል አድርጎ መያዝና እነዚህን የመሳሰሉትን ያካትታል።” [አልኢዕቲሷም፡ 1/53]
6. አልኢማም ኢብኑ ረጀብ (795 ሂ.)፡-
ሸሪዐው ዒድ ተደርጎ እንዲያዝ ያዘዘበትን ካልሆነ በስተቀር ሙስሊሞች ዒድ ሊይዙ አይፈቀድላቸውም። እነሱም (የታዘዙትም) ዒደል ፊጥር፣ ዒደል አዱሐና የተሽሪቅ (ከዒደል አድሓ ቀጥሎ ያሉት ሶስቱ) ቀናት ናቸው። እነዚህ አመታዊ በዓላት ናቸው። የጁሙዐ ቀን ደግሞ ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከዚህ ውጭ ያለን በዓልና ዐውደ- አመት አድርጎ መያዝ በሸሪዐችን መሰረት የሌለው ቢድዐ ነው።‛ [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 118]
7. አቡ ዐብዲላህ አልሐፋር አልገርናጢ (811 ሂ.)፡-
“የመውሊድ ሌሊት መልካም ቀደምቶች ማለትም የአላህ መልእክተኛ- ﷺ - ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት አልነበሩም። ከአመቱ ሌሊቶች ተጨማሪ ስራም አይሰሩባትም ነበር። ምክንያቱም ነብዩን- ﷺ - እንዲከበሩ በተደነገገው መልኩ እንጂ አይከበሩምና። እሳቸውን ማላቅ ከትልልቅ ወደ አላህ መቃረቢያዎች ነው። ነገር ግን ልቅናው ከፍ ወዳለው አላህ እሱ በደነገገው መልኩ እንጂ (በሌላ) መቃረብ አይፈቀድም። ሰለፎች ከሌሎች ሌሊቶች በተለየ ምንም የሚጨምሩ እንዳልነበሩ መረጃው በሷ (በተወለዱበት ቀን) ላይ መወዛገባቸው ነው። ለምሳሌ እሳቸው- ﷺ - የተወለዱት በረመዳን ነው ተብሏል፣ በረቢዕ ነውም ተብሏል። በዚህም ላይ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ አራት የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላጭ የሆኑት በመወለዳቸው ሳቢያ በማለዳዋ የተወለዱባት ሌሊት ዒባዳ የሚጠነሰስባት ብትሆን ኖሮ ውዝግብ ሳይከሰትባት በሰፊው በታወቀች ነበር። ነገር ግን ጭማሬ የሆነ ማላቅ አልተደነገገባትም።
የጁሙዐ ቀን ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጭ ቀን እንደሆነችና በበላጭ ቀን የሚፈፀመው በላጩ ነገር ፆም እንደሆነ አታውቅምን? ሆኖም ግን ነብዩ- ﷺ - ከትልቅ ልቅናው ጋር ከጁሙዐ ቀን ፆም ከልክለዋል። ይህም በየትኛውም ጊዜ ይሁን በየትኛውም ቦታ ካልተደነገገ በስተቀር አምልኮት መፍጠር እንደማይቻል ያመለክታል። ካልተደነገገ አይፈፀምም። ምክንያቱም የዚህች ህዝብ ኋለኛው ክፍል ከቀዳሚው የተሻለ የተቀና ነገር አያመጣምና። ይሄ በር ቢከፈትማ የሆኑ ሰዎች መጥተው ወደ መዲና የተሰደዱበትም ቀን ‘አላህ በሱ ኢስላምን ያላቀበት ቀን ነው’ በማለት ሊሰባሰቡበትና ሊያመልኩበት ነው። ሌሎች ደግሞ ተነስተው ኢስራእ ያደረጉባት ሌሊት ‘ልኬታው የማይገመት የሆነ ልቅና የተጎናፀፉባት ሌሊት ነች’ በማለት አምልኮት ሊፈጠር ነው። እናም (እንዲህ ከተከፈተ) የሆነ ወሰን ላይ ሊቆም አይቻልም። መልካም ሁሉ ያለው አላህ ለሳቸው የመረጣቸውን መልካም ቀደምቶች በመከተል ነው። የሰሩትን እንሰራለን። የተውትን እንተዋለን። ይሄ ከተረጋገጠ በዚች ሌሊት ላይ መሰባሰቡ በሸሪዐው ተፈላጊ እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል። እንዲያውም ይተው ዘንድ መታዘዝ አለበት። …
ይህቺ ሌሊት ደግሞ በሱፍዮች መንገድ ነው የምትዘጋጀው። በዚህ ዘመን የሱፍዮች መንገድ በዲን ውስጥ ከተፈጠሩ አስቀያሚ ነገሮች ውስጥ ነው። ምክንያቱም የጉባዔ ስርአታቸው ዘፈንና እንቶ ፈንቶ ነውና። ይሄ ነገር በነዚህ ጊዜያት ከሚፈፀሙ የላቁ መቃረቢያዎች እንደሆነና ይህ የወልዮች መንገድ እንደሆነ ለአላዋቂ ሙስሊሞች ያስተምራሉ። በሌሊትና በቀን ውስጥ ግዴታ የሆኑባቸውን ህግጋት በቅጡ የማያውቁ መሃይማን ሰዎች ናቸው። ይልቁንም አላዋቂ ሙስሊሞችን ለማጥመም ሸይጧን ምትኮች ካደረጋቸው ውስጥ ናቸው። ለሰዎች ከንቱ ነገሮችን ይሸላልማሉ። ወደ አላህ ዲንም ከሱ ያልሆነን ነገር ያስጠጋሉ። ምክንያቱም ዘፈንና እንቶ ፈንቶዎች ከዛዛታና ከጨዋታ ውስጥ ናቸውና። እነሱ ግን ወደ አላህ ወልዮች ያስጠጉታል። እነሱም በዚህ ላይ ገንዘብን ያለ አግባብ ለመብላት ይዳረሱ ዘንድ እየዋሹባቸው ነው።…” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዕ ወተሶውፍ፡ 128]
8. ኢብኑ ነሐስ (814 ሂ.)፡-
“አውደ-አመታትና በዓላት ውስጥ ከተፈጠሩት ውስጥ በከፊል ማውሳት” በሚል ንኡስ ርእስ ስር “ከነዚህ ውስጥ በወርሃ ረቢዐል አወል ሰዎች የፈጠሩት የመውሊድ ተግባር ነው” ይላሉ። በውስጡ ካሉ ቢድዐዎችና ጥፋቶች እንኳን ቢፀዳ ከቢድዐነት እንደማያልፍ ካጣቀሱ በኋላ ሰዎች መውሊድን ለማዘጋጀት የሚያነሳሳቸው ምክንያቶች ብለው የተወሰኑ ነጥቦችን አንስተዋል። ከነዚህም ውስጥ፡-
- ከሚጠሯቸው ቃዲዎች፣ መሪዎች፣ መሻይኾችና ከመሳሰሉት ጋር ለመተዋወቅ በማለም የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንድ መሻይኾች ደግሞ ሰዎች በመውሊድ ምክንያት በእርዳታ መልክ ወይም በስጦታ መልክ ወይም ሃፍረት ይዞት ወይም ደግሞ ከእኩዮቹ ጋር ለመፎካከር ሲል ከሚያመጡት ነገር የሚተርፈውን ለራሳቸው ለመጠቀም በማለም መውሊድን የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንዱ ክፉ ምላስ ያለውና ቁጡ ይሆንና ደካሞችን በመጥለፍና ምላሱንና ምግባሩን የሚፈሩ ሰዎችን በማጥመድ አላማውን የሚያሳካ አለ። … [ተንቢሁል ጋፊሊን ዐኒል አዕማሊል ጃሂሊን፡ 499]
9. ቃዱ ሺሃቡዲን ደውለት አባዲ አልሐነፊ (894 ሂ.)፡-
“በያመቱ መጀመሪያና በረቢዐል አወል ወር መሃይማን የሚሰሩት ተግባር ከምንም የሚቆጠር ነገር አይደለም። የሳቸው ﷺ ልደት ሲወሳ ይቆማሉ። ሩሐቸው ትመጣና ትካፈላለች ይላሉ። ይሄ ሙግታቸው ውድቅ ነው። ይሄ እምነት ሺርክ ነው።” [ፈታዋ ሸይኽ ሸምሲልሐቅ አዚምአባዲ፡ 166]
እንግዲህ ተመልከቱ። እነዚህ በሙሉ በ1206 ሂ. ከሞቱት ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ - ረሒመሁላህ - ዘመን ቀድሞ መውሊድን ያወገዙ ዑለማዎች ናቸው። መሃይማን ሱፍዮች ግን መውሊድን የሚቃወሙት ከ200 አመት ወዲህ የመጡ “ወሃቢዮች” ናቸው ሲሉ የራሳቸውን ድንቁርና በራሳቸው በራሳቸው አንደበትና ብእር እያጋለጡ ነው።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻና


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በዚህ ነጥብ ላይ ማተኮር የፈለግኩበት ምክንያት መውሊድን መቃወም የጀመሩት ከ200 አመታት ወዲህ የመጡ የነቢዩﷺ ጠላቶች ናቸው የሚል አሕባሽ ስላየሁ ነው። ከካፊር ዘንድ ተለጥፎ ሙስሊሞችን ሲያንገላታ የነበረው አሕባሽ ምንም ቢል አይደንቅም። ከመሆኑም ጋር ጉዳዩን በውል የማያውቁ አንዳንድ የዋሃን እንዲረዱት ያክል ግን ከ200 አመታት በፊት መውሊድን የኮነኑ ዑለማዎችን እጠቅሳለሁ።
1. ኢብኑ ተይሚያህ (728 ሂ.)፡- የሳቸውን አቋም ባለፈው አመት ስለዳሰስኩኝ በዚህ ሊንክ ከፍተው ማየት ይችላሉ። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3380210602050387&id=100001844423938
2. ታጁዱን ዐመር ኢብኑ ዐሊይ አልፋኪሃኒ (734 ሂ.)፡-
ሌላኛው መውሊድ ላይ ብርቱ ትችት የሰነዘሩት ፋኪሃኒ ናቸው፣ በዚህ ላይ አንድ ኪታብ ፅፈዋል። እንዲህ ይላሉ፡- “ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም በሱናም መሰረት አላውቅለትም። በዲን ላይ ተምሳሌት የሆኑትና የቀደምቶችን ትውፊቶች አጥብቀው የያዙ ከሆኑት የሙስሊሙ ህዝብ ምሁራኖች ከአንዳቸውም ተግባሩ አልተወሰደም። ይልቁንም ቦዘኔዎች የፈጠሩት ቢድዐ ነው!! ሆዳሞች ያተረፉበት የሆነ የነፍስ ዝንባሌ ነው!! … ይሄ (መውሊድ) ግን ሸሪዐው አልፈቀደበትም። ሶሐቦችም አልሰሩትም። ታቢዒዮችም እንዲሁ። እስካወቅኩት ድረስ ዲን የተላበሱ ዑለማዎችም አልሰሩትም። ይህ ነው ከሱ ከተጠየቅኩ ከአላህ ፊት የምመልሰው። የተፈቀደም ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በዲን ውስጥ ፈጠራ መፍጠር በሙስሊሞች ኢጅማዕ የተፈቀደ አይደለምና።
ስለዚህ የተጠላ ወይም የተከለከለ ከመሆን ውጭ የቀረ የለም!! የዚህን ጊዜ ወሬያችን ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል ማለት ነው፣ ሁለት የተለያዩ ሁኔታዎች ጋር።
አንዱ፡- አንድ ሰው ከራሱ ገንዘብ ለባለቤቱ፣ ለጓደኞቹና ለቤተሰቡ የሚያዘጋጀው ነው። በዚህም ጉባዔ ላይ ምግብን ከመብላት ሊያልፍና ወንጀሎችን የማይፈፅሙ ከሆነ ነው። ይህንን ነው የተጠላ ቢድዐና አስቀያሚ ነገር እንደሆነ የገለፅነው። ምክንያቱም የዘመናት መብራት፣ የሃገራት ውበት የሆኑት ምሁራኖችና የኢስላም ሊቃውንት የሆኑት ቀደምት የአላህ ታዛዦች አልሰሩትምና።
ሁለተኛ፡- ወንጀል የሚቀላቀለውና (ይህን ቢድዐ ለማክበር ገንዘብ ለመሰብሰብ) ትኩረት የሚበረታበት ነው። አንዳንድ ነፍሱ የተንጠለጠለ ሆኖ፣ ከግፉ ህመም የተነሳ ልቡ እያሳመመው የሆነን ነገር እስከሚሰጥ የሚደርስበት ነው። ዑለማዎችን አላህ ይማራቸውና ‘እፍረት አስይዞ ገንዘብን መውሰድ በሰይፍ እንደመውሰድ ነው’ ይላሉ።
በተለይ ደግሞ በዚህ ላይ ከጠገቡ ሆዶች ጋር እንደ ድቤና ዋሽንት ያሉ በከንቱ መሳሪያዎች የታጀበ ዘፈን ካለ፣ እንዲሁም ወንዶች ከወጣቶችና ከዘፋኝ ሴቶች ጋር መቀላቀል ከኖረ ወይ ከወንዶቹ ጋር ተቀላቅለው ወይ ደግሞ ከከፍታ ላይ ዘልቀው፣ እየተጣጠፉ በመጨፈር፣ ከዛዛታ ውስጥ መስመጥና አስፈሪውን (የቂያማ) ቀን መዘንጋት የሚደረስበት ነው።
ልክ እንዲሁ ሴቶች ብቻቸውን ሲሰባሰቡ ያለምንም ሀፍረት ድምፃቸውን በዘፈንና በነሺዳ ከፍ ያደርጋሉ። ከተለመደው የቁርኣን አቀራርና ዚክር አልፈው ከሸሪዐው ይወጣሉ። የላቀው ጌታ ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውናማለቱን ይዘነጋሉ። ይሄ ክልክል በመሆኑ ላይ ሁለት ሰዎች አይወዛገቡበትም። ስርኣት ያላቸው አስተዋዮች በጥሩ አያዩትም። ይሄ የሚፈቀደው የሞቱ ቀልቦችን ከያዘና ወንጀልንና ሃጢኣትን ከሚያበዙ ሰዎች ዘንድ ነው። እንዲያውም ልጨምርህና እነሱ እንደ ዒባዳዎች እንጂ እንደ መጥፎና ክልክል ነገሮች አይደለም የሚቆጥሩት። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ‘ኢስላም እንግዳ ሆኖ ነው የጀመረው። እንግዳ ሆኖም ይመለሳል።’ ሸይኻችን (ኢብኑ ደቂቀል ዒድ) አልቁሸይሪ ረሑመሁላህ እንዲህ ማለቱ ምንኛ እውነት ነው?!
‘በከባዱ ዘመናችን ሚዛን በተዘነጋበት
እኩይ ምግባር ተወዶ በጎው በክፉ ታየበት
ምሁራኑ ተዋርደው መሀይም ወጣ ከመድረክ
ሐቅም ካለው እርባና ቢስ ከቀደሙት ጋር ሲተረክ
ለደጋጎች እላለሁ ፈተናው ቢከፋም አትዘኑ
ተራችሁ ቢደርስ ነው ባይተዋርነት ሲነግስ በዘመኑ።’
አልኢማም አቡ ዐምር ብኑል ዐላእ ረሑመሁላሁ ተዓላ ‘በሚያስደንቅ ነገር መደነቅ እስካለ ድረስ ሰዎች ከመልካም ነገር አይወገዱም’ ሲል በርግጥም ጥሩ ብሏል። ይህ እንግዲህ ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ረቢዐል አወል ወር የሞቱበትም ከመሆኑ ጋር ነው። መደሰቱ በሱ ውስጥ ከማዘን ቅድሚያ የሚሰጠው አልነበረም።” [አልመውሪድ ፊ ዐመሊል መውሊድ፡ 2-8]
3. ኢብኑል ቀዪም (751 ሂ.)፡-
ሌላኛው መውሊድን የሚነቅፍ መልእክት ያስተላለፉት ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀዪም ናቸው። እንዲህ ይላሉ፡- “ኢስራእ ነብዩ ﷺከታደሏቸው ታላላቅ ትሩፋቶች ከመሆኑም ጋር ያንን ጊዜ ወይም ያንን ቦታ በሸሪዐዊ ዒባዳ መለየት አልተደነገገም። እንዲያውም ወሕይ መውረድ የጀመረበት የሒራእ ዋሻ ከነብይነታቸው በፊት ያተኩሩበት የነበረ ከመሆናቸው ጋር ከነብይነት በኋላ እራሳቸውም መካ ላይ በቆዩ ጊዜ፣ እንዲሁም ከሶሐቦች አንድም ያሰበው የለም። ወሕይ የወረደበት ቀንም እንዲሁ በዒባዳም ይሁን በሌላ ተለይቶ አልተያዘም። ወሕዩ የተጀመረበት ቦታም ይሁን ዘመኑ እንዲሁ በምንም ነገር ተለይቶ አልተያዘም። የሆኑ ቦታዎችን ወይም ጊዜዎችን ከራሱ በዒባዳዎች ለዚህና መሰል አላማ የለየ ሰው የመፅሐፉ ሰዎች አምሳያ ሆኗል። እነዚያ የመሲሕን (የዒሳን) ሁኔታዎች፣ ጊዜዎችና መሰባሰቢያዎች በዓላት አድርገው እንደያዙት። ለምሳሌ የልደት ቀኑን፣ የጥምቀት ቀኑንና መሰል ሁኔታዎቹን ለይተው እንደያዙት። ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዱየላሁ ዐንሁ የሆኑ ሰዎችን ወደ አንድ ቦታ ለሶላት ሲቻኮሉ ያዩዋቸዋል። ‘ምንድነው ይሄ?’ ሲሉ ጊዜ ‘የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሰገዱበት ቦታ ነው’ አሉ። ‘የነብዮቻችሁን ፋናዎች መስገጃዎች አድርጋችሁ ልትይዟቸው ትፈልጋላችሁን? ከናንተ በፊት የነበሩት ሰዎች የጠፉት በዚህ ነው። በዚያ እያለ ሶላት የደረሰበት እዚያው ይስገድ። ያለበለዚያ ግን ጉዞውን ይቀጥል’ አሉ።” [ዛዱል መዓድ፡ 1/59]
4. አቡል ዐባስ አሕመድ ኢብኑል ቃሲም አልቁባብ (778 ሂ.)፡-
በመውሊድ ቀን ልጆችን ሰብስቦ ሻማ ስለመለኮስ፣ በነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ስለማለት፣ ድምፁ ያማረውን ከውስጣቸው በመምረጥ አስር የቁርኣን ሱራዎችን እንዲያነብ ስለማድረግና ነብዩን ﷺየሚያወድሱ ግጥሞችን ስለመነሸድ፣ በዚህ ሰበብም ወንዶችና ሴቶች መሰባሰባቸውን እንዲሁም አስተማሪው ሻማዎችን መቀበል የሚፈቀድለት ስለመሆኑ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ ነበር የመለሱት፡-
“የገለፅካቸው በሙሉ ቢድዐ የሆኑ መጤ ፈሊጦች ናቸው። ስለሆነም የግድ ሊቋረጡ ይገባል። እነዚህን ነገሮች የሚፈፅም ወይም በነዚህ ላይ የሚያግዝ ወይም እንዲቀጥሉ የሚተጋ ሰው በቢድዐና በጥመት ላይ ነው እየተጋ ያለው። እሱ ግን በድንቁርናው ሳቢያ በዚህ ተግባሩ የአላህ መሌእክተኛን - ﷺ - የሚያከብርና መውሊዳቸውን የሚያከብር እንደሆነ ያስባል። እሱ ግን ሱናቸውን እየጣሰና ክልከላቸውን እየፈፀመ ነው። ይህንን በይፋ እየፈፀመ ዲን ያልሆነን እንግዳ ነገር እየፈጠረ ነው። እውነተኛ የሆነን ማክበር ቢያከብራቸው ኖሮ ትእዛዛቸውን ባከበረና በዲናቸው ውስጥ እንግዳ ነገር ባልፈጠረ ነበር። እንዲሁም አላህ እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳይደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁሲል ካስጠነቀቀው ጋር ባልተላተመ ነበር።

አስተማሪው የሚቀበለውን (ስጦ


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
» ለመሆኑ በአለባበስሽ፣ በአመጋገብሽ፣ በአነጋገርሽ፣ ነቢዩ ﷺ ያዘዙሽን ፈፅመሻል?

» ብረት እንደሚገፋ ወንድ ሰውነትሽን ወጣጥረሽ፣ እንደ አርሶ አደር (ገበሬ) ቁምጣ የሆነ ቁርድ ለብሰሽ፣ ሰርግ ሳይኖር ሰርግ አስመስለሽ ድቤ እየደበደብሽ የሞቱበትን ቀን እያከበርሽ ነው እወዳቸዋለሁ ምትይኝ?! ቤትሽ ውስጥ አህያ ቢኖርና መሳቅ ቢችል ይህን ሰምቶሽ ሁሌ እያስታወሰ በተግባርሽ ይስቅብሽ ነበር።

» ለመሆኑ ነቢዩ ﷺ "ሽቶ ተቀብታ ከቤቷ የወጣች ሴት ዝሙተኛ ናትና ወደ ቤቷ ተመልሳ የጀናባ ትጥበትን ትታጠብ።" እያሉ፣ ተቀባብቶ መውጣቱ ሀራም መሆኑን እያወቅሽ፣ ተቀብተሽ እየወጣሽ ተመልሰሽም እንደ ጀናባ ትጥበት መታጠብ ሳትችይ ነው እንዴ ስለምወዳቸው ነው መውሊዳቸውን የማከብረው ምትይው? ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይሰማሽም በአላህ?! አትሸማቀቂም?!

ይልቅ ወደራስሽ ተመለሺ፣ ሱናቸውን ካላወቅሽ ተማሪ!! ቁርኣንና ሀዲስን በትክክለኛ ሰዎች ተማሪ። ተግብሪው። ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ለባሏና ለተወዳጁ ነቢይ ፍቅሯን እና ውዴታዋን የገለፀችበት መንገድ (እሱም ችለሽ ከተገበርሺው) በቂሽ ነው!!! እሷ የገለፀችበትን መንገድ ለማወቅ ከፈለግሽ፣ ቁርኣንና ሀዲስን ሳያጭበረብሩ በትክክል በሚያስተምሩ ሰዎች ላይ መማር ነው።

⑦ » አላህ ዲኑን ሙሉ አድርጌዋለሁ እያለ ነው፣ አንተ ከዲኑ ውጪ የሆነውን መውሊድን አከብራለሁ ስትል፣ ከአላህ በላይ በዲኑ ላይ ህግ አወጣለሁ ስለ ዲኑም አውቃለሁ እያልከ ነውን??

"ዑለማዎች እንዲከበር አዘዋል" አትበለኝ!!
⑧ » የትኛዎች ዑለማዎች ናቸው?
እነዚያ መንገዱን ተሳስተው አሳሳቾች ናቸው? ነቢዩ ﷺ ጠመው አጥማሚ መጥፎ የጥመት ዓሊሞች ያሉዋቸው ናቸው?
⑨ » ወይስ ከነቢዩ ﷺ ዲኑን አቀበት ቁል ቁለቱን፣ ጋራ ሸንተረሩን፣ ወጥተው ወርደው ቸነፈር እያሰቃያቸው፣ ወርሰው በትክክል ያስወረሱንን እንደ እነ ኢማሙ ሻፊዒይና ኢማሙ አህመድ ያሉ ብርቅዬ የጨለማ ማብራት የነበሩ ከዋክብቶችን ነው ምትለኝ?
» እነሱ መውሊድን አክብረዋልን? የታለ ማሰረጃህ? ኢማሙ አቡ ሀኒፋ፣ ኢማሙ ሻፊዒይ፣ ኢማሙ አህመድ፣ ኢማሙ ማሊክ አክብረዋል????

ይልቅ በትክክል የአላህ እና የመልእክተኛው ﷺ ወዳጅ ነኝ ካልን፣ በምን እንደሚገለፅ እንዲህ በማለት አላህ በተቀደሰው ቃሉ መልሱን በአጭሩ አስቀምጦታል:-

﴿قُل إِن كُنتُم تُحِبّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعوني يُحبِبكُمُ اللَّهُ وَيَغفِر لَكُم ذُنوبَكُم وَاللَّهُ غَفورٌ رَحيمٌ﴾ آل عمران ٣١
“በላቸው:– አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ #ተከተሉኝ፣ አላህ ይወዳችኋልና። ኃጢያቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና። አላህ መሃሪ አዛኝ ነው።” ኣል ዒምራን 31

እውነት ከልባችን አላህን እና መልእክተኛውን ﷺ የምንወድ ከሆነ ውዴታችን መግለፅ የምንችለው በትክክል መልእክተኛውን በመከተል ብቻና ብቻ ነው!!።
ብዙ ማለት ብፈልግም፣ ብዙ ሰው ረጅም ፅሁፍ ማንበብ ስለማይወድ እዚህጋ ለማቆም እገደዳለሁ።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ረቢዐል አወል 1/1442 ዓ. ሂ

#Join ⤵️

https://telegram.me/IbnShifa


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ልዩ የመውሊድ ስጦታ ለአስተዋዮች!!
"""""""""""""""""""""""
ለመውሊድ ስጦታ መሰጣጠት ባይፈቀድም #ይህ_ልዩ_የመውሊድ_ስጦታይ ነው።

በትግስት አንብባችሁ ለሌሎችም #Share በማድረግ አሰራጩት።

መውሊድ እንዲከበር የሚተጉ የጥመት ቡድኖችና የሙስሊሙ ጠላቶች "ለነቢዩ ﷺ ውዴታና ፍቅር ስላለን ነው ምናከበረው፣ የሚቃወሙን ሰዎች ደግሞ ለነቢዩ ﷺ ውዴታ ስለሌላቸው ነው" እያሉ ስለ ዲኑ በቂ እውቀት የሌለውን ሙስሊም ያሞኛሉ።

የትኛው የነቢዩ ﷺ ፍቅርና ውዴታ ነው ያላችሁ?!
የነቢዩ ﷺ ፍቅርና ውዴታ መለኪያ ምንድነው?!

እናንተ ለነቢዩ ﷺ ውዴታ መለኪያ ያደረጋችሁት መውሊድን ነው። መውሊድን ደግሞ ነቢዩ ﷺ አያውቁትም! አይወዱትም!!። ምክንያቱም በዲናችን የሌለ አዲስ መጤ ነገር ነው!፣ ነቢዩ ﷺ ደግሞ በየ ሳምንት ጁምዓ "አደራ በዲን ላይ አዲስ መጤ ነገርን ተጠንቀቁ!፣ አዲስ መጤ ነገር ሁሉ ጥመት ነው" ይሉ ነበር። ስለዚህ መውሊድ መጤ ነገር ስለሆነ አይወዱትም ማለት ነው።

ያውም በመውሊድ ቀን የሚባሉ ስንኞች የተለያዩ ድንበር ያለፉና ሺርክ የተሞላባቸው ናቸው።

ታዲያ አንተ የነቢዩን ﷺ ትእዛዝ በመቃረን ነው እንዴ ውዴታቸውን ምትገልፀው??

እንደሚታወቀው ደግሞ የሚወዱትን ሰው ይታዘዙታል እንጂ አያምፁትም!!፣ ሚያስከፋውን ነገር ይጠነቀቁለታል እንጂ ሚያስከፋው ነገር ለመተግበር ፈፅሞ አይታሰብም!!።

ምን ይህ ብቻ ከሚወደድ ነገር ሁሉ ኣቻ የሌለው ተወዳጁን አላህን እንኳን እንወዳለን ብለን ብንሞግት አላህ ነቢዩን ﷺ በትክክል እንድንከተል መስፈርት አድርጎብናል፣ እንዲህ በማለትም አዞናል:-

﴿قُل إِن كُنتُم تُحِبّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعوني يُحبِبكُمُ اللَّهُ وَيَغفِر لَكُم ذُنوبَكُم وَاللَّهُ غَفورٌ رَحيمٌ﴾ آل عمران ٣١
“በላቸው:– አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ #ተከተሉኝ፣ አላህ ይወዳችኋልና። ኃጢያቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና። አላህ መሃሪ አዛኝ ነው።” ኣል ዒምራን 31

በትክክል አላህን እና ነቢዩን ﷺ የምንወድ ከሆነ በየትኛውም አቅጣጫ ከሚፈልጉት መንገድ ውጪ እየተጓዙ እወዳቸዋለሁ ማለት የማይታሰብ ነው!። ገጣሚው እንዲህ ይላል:–

تعصى الإله وأنت تدعي حبه هذا محال في القياس بديع
"አምላክህን ታምፃለህ፣ ነገር ግን እንደምትወደው ትሞግታለህ። ይህ ፈፅሞ የማይታሰብና አዲስ ፈጠራ የሆነ ልኬት (ቂያስ) ነው።"

አንድ ሰው ፈጣሪውን እና ከፈጣሪው ዘንድ የተላከለትን ታላቁን መልእክተኛ ﷺ ቀርቶ፣ በጣም የሚወደውን ጓደኛውን እንኳን እየተቃረነውና ከርሱ ሀሳብ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እየሄድ እወደዋለሁ አይልም።
በተለይ ያ! ጓደኛው "እነዚህን ነገሮች አትዳፈርቢኝ" ብሎ በተለየ መልኩ ቀይ ያሰመረበት ነገር ካለና ያንን ነገር ያለ ፈቃዱ ሚነካካና ከርሱ ሀሳብ ተቃራኒ ሆኖ እየተጓዘ እወድሃለሁ ቢለው፣ ጓደኛው የሚረዳው እያፌዘበት መሆኑን እንጂ ፈፅሞ እንደሚወደው አይደለም!።

ነቢዩ ﷺ ዒርባድ ኢብን ሳሪያ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ በማለት በዲን ላይ አዲስ ነገር ከመፍጠር (ከመጨመር) እንድንጠነቀቅ አሳስበውናል:–
«وإيَّاكم ومُحْدَثاتِ الأُمورِ، فإنَّ كلَّ مُحْدَثةٍ بِدْعةٌ، وإنَّ كلَّ بِدْعةٍ ضَلالةٌ»
“አደራችሁን (በዲን ላይ) አዳዲስ ነገሮችን (ከመጨመር) ተጠንቀቁ!! ሁሉም (በዲን ላይ አዲስ መጤ) ፈጠራ ነው፣ ፈጠራ ነገር ሁሉም ጥመት ነው።” ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።

አላህን በትክክል የምትወድ ከሆነ አላህ ዲኑን ሙሉ አድርጌዋለሁ ብሏልና ስሜትህን በመከተል አዲስ ነገር ካልጨመርኩ ማለትህን ትተህ ሙሉ በሆነው ዲን ውስጥ ያለውን ነገር ተግብር።
{اليَومَ أَكمَلتُ لَكُم دينَكُم}
“የዛሬ ቀን ሀይማኖታችሁን ሙሉ አደረግኩላችሁ።” አልማኢዳ 3

አዎ! ዲኑ ሙሉ ነው!! አንተ ጎበዝ ከሆንክ ሙሉ በሆነው ዲን ውስጥ ያለውን የታዘዝከውንና ሱንና የሆነውን ብቻ ተግብር። ትክክለኛ ውዴታ የሚገኘውም የሚወዱትን አካል ትእዛዝ በማክበር ነውና!።

በትክክል አላህን እና መልእክተኛውን ﷺ የምትወድ ከሆነ በዲኑ የሌለን አዲስ ነገር መፍጠር ትተህ ያዘዙህን ታዘዝ፣ ከከለከሉህ ነገር ሁሉ ተቆጠብ!።

እስቲ ልጠይቅህ/ሽ?

① » መውሊድ ከዲኑ ከነበረ ለምን እንደ 2ቱ ዒዶች በቁርኣንና በሀዲስ እንዴት መከበር እንዳለበት በዝርዝር አልመጣም??

② » በመልካም ነገር ሶሃቦችን ከማነሳሳታቸው በፊት ቀድመው ለራሳቸው የሚተገብሩት ታላቁ ነቢይ ﷺ መውሊድን አክብረውታልን??

③ » አንተ ቢድዓ በሆነው መውሊድ ላይ እንደምትነቃቃው ለምን ሌሎች ግዴታ በሆኑ ዒባዳዎች ላይ አትነቃቃም (አትነሽጥም) ??

④ » ነቢዩን ﷺ ኮቴ በኮቴ እየተከታተሉ የሸኑበት ቦታ ሳይቀራቸው፣ ሽንታቸውን በሸኑበት ቦታ የሚሸኑ የነበሩት ብርቅዬ ሶሃቦች መውሊድን አክብረውታል??

⑤ » አንተ/አንቺ ለነቢዩ ﷺ ሱንና ከሶሃቦችና ከተከታዮቻቸው (ታቢዒዮች) የበለጠ ተቆርቋሪ ናችሁ??

⑥ » በዲኑ ላይ አዲስ ነገር በቁርኣንም በትክክለኛ (ሶሂህ) ሀዲስም የሌለን ነገር ለመጨመር ከመናፈቅህ በፊት፣ ቁርኣን እና ሀዲስ ውስጥ ያለውን ጨርሰህ ተግብረሃል??

» ነቢዩ ﷺ ልብሳቸውን ያሳጥሩ ነበር አሳጥረሃል?

» ነቢዩ ﷺ ፂማቸውን ያሳድጉ ነበር አሳድገሃል?

» የነቢዩ ﷺ እጅ ባእድ የሆነችን ሴት ጨብጣ አታውቅም አንተ ሴት መጨበጥ ትተሃል?
» ነቢዩ ﷺ የሌሊት ሶላትን እግራቸው እስኪሰነጣጠቅ ይሰግዱ ነበር፣ አንተስ እየሰግድከ ነው? እንደው የለይሉ ሶላት ቢቀር ዊትሯን ትሰግዳታለህ? ውትሯም ባትኖር እንዳው በጊዜ ተነስተህ የሱብሂ ሶላትን በጀመዓ ትሰግዳለህ?

» ነቢዩ ﷺ የምርጥ ስነ-ምግባር ባለቤት ነበሩ፣ አንተስ ስነ-ምግባርህ ምንና ማንን ይመስላል?

» እንደምትለው እውነት የነቢዩ ﷺ ውዴታ ካሰመጠህ የአውሮፓ ተጫዋቾችን እና ዘፋኞችን፣የፊልም አክተሮችን ባህሪ እርግፍ አድርገህ ትተህ የነቢዩን ﷺ ስነ-ምግባር ለምን አትከተልም??

ይህን ማድረግ ሳትችል ነቢዩ ﷺ ካዘዙበት መንገድ ውጪ፣ ነቢዩን ﷺ እወዳለሁ ማለትህ የለየልህ ተወዳዳሪ የሌለህ ነገ ከሞት በኋላ ተቀስቅሰህ አላህ ፊት እርቃንህ መቆምህን የዘነጋህ በስሜት ምትነዳ ግልብ ውሸታም ነህ!!!

እህቴ ሆይ! እስቲ ልጠይቅሽ? በአላህ ይሁንብሽ! ለኔ ባትመልሺልኝም ቆም ብለሽ አስተውለሽ ጥያቄውን ለራስሽ መልሺው። ከላይም ከታችም ያለው ጥያቄ አንቺንም ይመለከታል!! ግን ተጨማሪ በሴትነትሽ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ልጨምርልሽ ወደድኩ…

» መውሊድ ማከብረው ለነቢዩ ﷺ ውዴታ መግለጫ ነው ካልሽ ነቢዩ ﷺ በሚጠሉት በቢድዓ መንገድ ነው ምትገልጪላቸው እንዴ?
ከልብሽ አስተውይ! አንቺን ባልሽ እወድሻለሁ እያለሽ አንቺ በእጅጉ የምትጠይውን ነገር እያወቀ ሚሰራ ከሆነ እውነትም ይወደኛል ብለሽ ታምኚዋለሽ?!

» ወይስ የነቢዩን ﷺ ውዴታ ምትገልጪበት ሱናቸውን ሁሉ ጨርሰሽ ተግብረሽ ጭማሪ አስፈልጎሽ በመውሊድ ውዴታቸውን ለመግለፅ ነው የተነሳሽው?!

» ቆይ ግን አንቺ ነቢዩን ﷺ ከተወዳጁ የጓደኛቸው የአቢበክር ልጅና ሚስታቸው ከሆነችው ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የበለጠ ትወጂያቸዋለሽ?!

» ታዲያ ይህች ውድ እናትሽ የታላቁ ነቢይ ድንቅና ውድ የሆነችው ምስታቸው ዓኢሻ፣ ለዚህ ህዝብ ዲኑን ያስተማረችው ምርጧ የዚህ ህዝብ እናት መውሊድን አክብራለች?! የትና መቼ?




Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
👉🏻ልብ ይበሉ! ይህ ብዙዎች ዘንድ በሶላታቸው የሚታይ ስህተት ነውና ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል!!
—————
ከፊል የኢማሙ ተከታዮች የሶላቱ የተወሰነው ክፍል ካመለጣቸው፣ ያመለጣቸውን ለማምጣት (ቀሪውን ለማሟላት) ሲሉ ኢማሙ ሁለተኛው (ወደ ግራ) ያለውን ሰላምታ ከመሰላመቱ በፊት ተነስተው ሲቆሞ ይስተዋላል፣ ይህ ስህተት ነው!!

የአላህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል:–
"እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ኢማማችሁ ነኝ በማጉንበዝ (በሩኩዕ) አትቅደሙኝ፣ በሱጁድም አትቅደሙኝ፣ በመቆምም አትቅደሙኝ፣ በመዞርም አትቅደሙኝ ....." ሀዲሱ ረዘም ይላል። ሙስሊም ዘግበውታል

ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–


አላህ ይዘንላቸውና በመቀጠልም እንዲህ ብለዋል:–
ኑሩን አለደርብ 12/3688
✍🏻ኢብን ሽፋ
https://telegram.me/IbnShifa


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ታላቁ ዓሊም ሱፍያን አስ-ሰውሪይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-

"የቢዳዓ ባልተቤት ጋር የተቀማመጠ ከሶስት ነገር ባንዱ ሰላም አይሆንም

1, ወይ ለሌሎች ሰዎች ፊትና ይሆናል! (ይህ በብዛት በዚህ ጊዜ የሚስተዋለው ከባድ አደጋ ነው)

2, ወይ በልቦናው ላይ የሆነ ነገር ሊከሰት (ይችላል) በርሱ ምክኒያት ይጠምና አላህ እሳት ያስገባዋል

3, አልያም (ሙብተዲዕዎች) በተናገሩት ንግግር በአላህ ይሁንብኝ ደንታ የለኝም፣ እኔ በነፍሴ እተማመናለሁ፣ ይላል። አላህን ደግሞ የዐይን እርግብታ ያክል በዲኑ ላይ (ምንም አያደርገኝም በራሴ እብቃቃለሁ በማለት) የተማመነ (አላህ) ዲኑን ይቀማዋል።"

【አል–ኢዕቲሷም 1/130】

አኚህ ታላቅ ዓሊም ከቢዳዓ ሰዎች ጋር የሚቀማመጥን ሰው በነዚህ ሶስት ከባባድ አደጋዎች አስጠንቅቀዋል!!።

ስለዚህ:-
ከቢደዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ እራስህን ቆጥብ!!
https://telegram.me/IbnShifa


Forward from: Bahiru Teka
👉 የሙመይዕና የደካማ ሰለፍይ ልዩነት
በአሁኑ ጊዜ በሚያሳዝን መልኩ ድሮ ከኢኽዋን ከተብሊግና ከሱፍይ ሚንሀጅ አራማጆች ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ሲተናነቁ ለተውሂድና ለሱና ሲሉ ከወንድምና እህታቸው የተለያዩ የነበሩ የወላእና በራእ ድንበር እንዳይደፈር ዘብ በመቆም ውድ ዋጋ በመክፈል ወጣቱ የተውሂድና የሱና ባንዲራ ከፍ እንዲያደርግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከቻሉ በአውቶብስ ካልቻሉ በእግራቸው ኑ ወደተባሉበት በመሄድ ከውስጥ እንደ ነበልባል እየነደደ በሚወጣ የቁጭት ስሜት ህዝቡ የተዘፈቀበትን የሽርክ ረመጥ እያወገዙ የተውሂድ ዘር ሲዘሩ የነበሩ ሰዎች
ዛሬ ያኔ ባላወቅንበትና ባልበሰልንበት ጊዜ ነበር አሁን አውቀናል በስለናል የሰለፍያ ዳዕዋ ማለት እንደሱ አይደለም
ማጠንከር አያስፈልግም ዳዕዋ በማለስለስ ነው የሚደረገው የሰው ስም መጥራት አያስፈልግም ይለያያል ሰዎችን ያርቃል የሚፈለገው አንድነት ነው እያሉ
በምን ላይ ? ሲባሉ
አይታወቅም ብቻ ሰዎችን አታባሩ በሚል ወደኀላ ተመልሰው ለሌላው ወደኀላ መመለስና ለዘብተኛ መሆን ጥብቅና በመቆም ይህን አልቀበልም ያለና ሌላውም እንዳይቀበል ያደረገን ወሰን አላፊ ሂክማ የሌለው መስለሃ የማያውቅ በማለት ከዚህ አልፎም ሀዳዲ እያሉ ስም በማጥፋት ሰው ትክክለኛው የሰለፍያ ዳዕዋ እንዳይረዳ ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ በማድረግ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት ሲፈፅሙ ይታያል
ይህ ድርጊት ብዙ ሙሪዶች እንዲያገኙ ስላደረጋቸውና
አብዛኛዎች ዲናቸውን በእውቀት ሳይሆን በሰው ላይ ተንጠልጥለው ስለሆነ የያዙት ያ ሰው ወደ ዞረበት ስለሚዞሩ መረጃ የሚያደርጉት ከመጀመሪያ አሽርጌታቸው ያገኙት ከእገሌ የበለጠ አንተ ታውቃለህ ወይ ስለሆነ
በዚህም ምክንያት በሙመይዕና በደካማ ሰለፍይ መካከል ያለው ልዩነት ለብዙዎች ግልፅ ባለመሆኑ አለመግባባትና ንትርክ እየተፈጠረ ስለሆነ በአላህ ፈቃድ ልዩነቱን ላስቀምጥ ወደድኩኝ
ሙመይዕ ማለት
ከነበረበት አቋም በመንሸራተት ሰለፍያ ሚንሃጅ ሁሉንም የሚያቅፍ ሰፊ ሚንሃጅ ነው በማለት በሰለፎች የማይታወቅ ቀመር ( ፎርሙላ ) በማምጣት ሰዎች ኢኽዋኖችም ሆነ ተብሊጎች ከጠማማ አንጃዎች መሆናቸውን እንዲጠራጠሩ የሚያደርጉ
ማግራራት የሚል አዲስ ሚንሀጅ የሚያመጡ አታጥብቁ ስዎችን አታርቁ የሚሉ ሚንሀጅ ሚንሀጅ አትበሉ ተህዚር ተህዚር አትበሉ በሚል ፍልስፍና ሁሉንም በሰለፍያ ስም ማቀፍ የሚፈልጉ ማለት ሲሆን
ደካማ ሰለፊ ማለት ግን
እነዚህ አባባሎችን የሚቃወም በአቋም ሁሉንም የሰለፍይ ሚንሀጅ መርሆችን የሚቀበል ተብሊግም ሆነ ኢኽዋኖች ከጥመት አንጃዎች ናቸው እያለ
በእነርሱ ላይ ረድ የሚያደርጉትን የማይቃወም እነርሱን የማይተች ነገር ግን ከእነርሱ ጋር ሰላም የሚባባል ለማኩረፍ አቅም የሌለው በተለያየ ምክንያት ከእነርሱ ጋር የሚቀራረብ ነው
በመሆኑም እንደነዚህ አይነት ወንድሞች ብዙ ስለሆኑ እባካችሁን ልንረዳቸው ይገባል ካልሆ ሸይጣን በመካከላችን ገብቶ ለመበታተን ስለማይተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል
አላህ ሁላችንንም በሀቅ ላይ ያፅናን
http://t.me/bahruteka


Forward from: MuhammedSirage M.Nur.
የሳውዲ መሪዎችን ሁኔታ በፍትህ አይን ተመልከቱ !
እምነታቸው አላህን በብቸኝነት በማምለክ ላይ የተገነባ ነው !
የሰነቁትን ተውሒድ አለሙ ይቋደሰው ዘንድ ፣ አላህም በብቸኝነት ይመለክ ዘንድ ሃገራችንን ጨምሮ በተለያዩ ሃገሮች ቢሊዮኖችን አፈሰሱ! ነገር ግን አመስጋኙ ጥቂት ሆነ !! መልካማቸውን ሁሉ ከበላና ከጠጣ በሇላ እንደ ኢኽዋን ጡት የሚነክሰው ውለታ ቢስ በዛ !

ወላሂ ! ከፈጣሪያችን አላህ እርዳታ በሇላ ዛሬ ያለንበት ተውሒድ ላይ የሳውዲ መሪዎች የማይሳሳ እጅ አለበት! !


ከሃያ አምስት አመታት በፊት ጀምሮ በሃገራችን የቲሞችን በመርዳት ላይ ፣ መስጂዶችን በመገንባት ላይ ሳይታክቱ ብዙ ሰሩ ! !

የሳውዲ መስጅዶች ውስጥ የአህሉሱናን እምነት የሚፃረር ዓቂዳ ፣ በተለይ ሽርክን መስበክና ወደ ቀብር አምልኮ መጣራት የሚታሰብ አይደለም ! በፍፁም!
የሳውዲ መሪዎች የነ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን ፣ የኢብኑል ቀይምን ና የሌሎችን የሱና ዑለሞች መፃህፍት ይታተሙ እና ይሰራጩ ዘንድ ሲረዱ ሲደጉሙ ኖረዋል!
የቱርክ መሪዎች ምድርን ሊነጅሱ የቀብር መመለኪያ ዶሪሖችን ሲገነቡ ጀግኖቹ ግን ከምእራብ እስከ ምስራቅ መስጂዶችን አብዝተውና አስፍተው ሲገነቡ ቆይተዋል !

ከሃዲያን በነዚህ መልካም ስራዎች ምክንያት በርካታ ክሶችን እስኪያቀርቡባቸው ድረስ አብዝተው ደከሙ ፣ አብዝተው ሰሩ ።
ኢኽዋን ይህንን ሁሉ የሳውዲ መልካም ስራ ሲቀብረው ኖረ ! ደግነታቸው አይወሳ ዘንድ ሲሸፋፍነው ኖረ! ! እስኪጠረቃ ድረስ ከጃቸው በላ ። እስኪበቃው በነሱ ገንዘብ ገነባ! ! ግን አንገት የለውና ዞሮ ጡት ነካሽ ሆነባቸው ። ይሄ አልበቃ ብሎት ሙስሊሙ ማህበረሰብ እነሱን ይጠላ ዘንድ አነሳሳ ።
ወንድሞች ፣ እህቶች ሆይ ንቁ !!
ያችን የተቀደሰች ምድር ፣ ዑለሞቿን ፣ ህዝቦቿንና መሪዎቿን አላህ ይጠብቅ! !
t.me/Muhammedsirage


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
መጅሊሱ የማን ተወካይ ነው???
። ። ።
በሀገራችን ውስጥ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለያየ መንገድ የተለያዩ ችግሮች ሲፈጠሩ ይስተዋላል። አንዳንዴ የብሔር ግጭት፣ ሌላ ጊዜ የሀይማኖት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከዜጎች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ህዝብ ከመንግስት ጋር ግጭት ሲፈጥር ይስተዋላል።

ታዲያ ሁሉም ለተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎች በየ አቅጣጫው ግጭቶችን በመቀስቀስም ይሆን በሌላ መንገድ የሚፈልገውን የህዝቡን ክፍል ለማሳመን ሲፍጨረጨር ይስተዋላል።

በዚህ አጋጣሚ ደግሞ የሚጎዳው መሃል ላይ ያለው ሚስኪኑ ህዝባችን ነው። "ሁለቱ በሬዎች ሲፋለሙ የሚቸግረው ሳሩ ነውና" በእንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ችግሩ የሚደርስበት ከታች ያለው አካል ነው። አንዳንዴ በብሔር ሌላ ጊዜ ደግሞ በሃይማኖት የከፋ ችግር ውስጥ ይወድቃል።

በእንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ደግሞ ለፖለቲካውም ይሁን ለጥቅሙ አለያም እውነተኛ ተቆርቋሪም ይሁን በሀይማኖትም ሆነ በብሔር ለተጎዳው አካል የሚከራከርለትና ችግር እንደ ደረሰበት የሚያሳውቅለት፣ ተገቢውን ካሳ እንዲያገኝና ዳግም የችግሩ ሰለባ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥረት የሚያደርግለት ተወካዩ የዚያ ሀይማኖት ወይም ብሔር ተጠሪ የሆነው አካል ነው።

ከላይ እንደጠቀስኩት ሀገራችን የተለያዩ ችግሮች እየገጠሟት ቆይታለች፣ በቅርብ ጊዜ ደግሞ የፖለቲካ አለመግባባቶች ጎልተው እየወጡ በመሄዱ የተለያዩ ፖለቲከኞች መታሰራቸውን ተከትሎ ሙስሊሞች የሚበዙባት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ተከስቷል።

ይህን ተከትሎ በክልሉ የሰው ህይወት እንደ ቅጠል መርገፉን እና ንብረትም መውደሙን በተለያየ አቅጣጫ ሰምተናል። ሁላችንም እንደታዘብነው "የጋራ ነው" የሚባለው የመንግስት ሚዲያ እንደ ልማዱ የአንዱን ወገን ጩሀት ብቻ ሲያስተጋባ ቆይቷል። ተወካዮችም እንደ ሀይማኖትም እንደ ብሔርም (የሙስሊሙ ተወካይ ነው ሚባለው መጅሊስ ሲቀር።) ሁሉም የኔ ነው ብለው ለተወከሉለት አካል ጩሀቱን ሲያስተጋቡና አልፎ ተርፎ ለበቀል ሲያነሳሱ ቆይቷል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ግን ሁሌም የቲም ነው። ኢኽዋኑም፣ ሱፊይና አሽዓሪውም እንደ አመችነቱ በደሙ ይነግዱበታል። ኢኽዋኑም ወንበሩ ስትነቃነቅበት ህዝቡን ምንም ላይፈይደው ቁስሉን ነካክቶ በማነሳሳት ይጠቀምበታል፣ ወንበሩ ስትረጋጋ ደግሞ ህዝቡን ያነሳሱበት ነጥብ እንኳን ያስነቃብናል ብለው ሳይሸማቀቁ "በጥቃቅን ነገር አትከፋፍሉን፣ ሁላችንም አንድ ነን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘናል" ብለው ፍጥጥ ይላሉ። ያው "የሌባ ዐይነ ደረቅ…" እንደሚባለው ነው።

ሙስሊሙን አሽዓሪያውና ሱፊዩም (አህባሹ) ከከሀዲዎች ጋር ሆኖ ለወንበሩ ፊዳ ያደርገዋል። ይወክለኛል የሚለው መጅሊስ ዋና ፀሃፊ አሽዓሪያው አቶ ቃሲም ታጁ በሰሞኑ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተከሰተውን የኢማሞችን ግድያ አስመልክቶ ከመጅሊሱ የስራ ቦርድ ጽ/ቤት የተሰጠውን መግለጫ "ህገ ወጥ ነው፣ ተገደሉ የተባለውም ያልተጣራ ወሬ ነው።" ብሎ በማጣጣል ለአሜርካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ (VOA) ሲናገር ሰምቼው በጣም ተገረምኩ። (ያልተጣራ ነው ብሎ ካመነበትም ህዝበ–ሙስሊሙን ወክሎ ከተቀመጠ ከማንም በፊት ፈጥኖ ደርሶ በማጣራት ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለግ የነበረበት ራሱ የፌዴራል መጅሊስ አመራር ነበር፣ ቢያንስ ደግሞ አብዘሃኛው ሙስሊም የሆነበት ክልል የሟቹ ቁጥር ከፍ ሲል ከፍተኛው የሟች ቁጥር ሙስሊሙ እንደሆነ ጥርጥር የለውም!።)

ይህን መናገር ከነሱ የማይጠበቅ ስለሆነ ሳይሆን፣ መንግስት እንኳን ክስተቱን አምኖ የኦሮሚያ የፀጥታ ዘርፍ ኀላፊው አቶ ጂብሪል መሀመድ "በስህተት የተፈጠረ ክስተት ነው" በማለት የተናገሩትን ተጨባጭ ይነቃብኛል ሳይል ለሙስሊሙ ያለውን ንቀት ማሳየቱ ነው።
"ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአንድ ሙስሊም ደም ከሚፈስ ከዕባ ቢወድም ይሻላል" በማለት የሙስሊምን ደም ክብደት የገለፁትን፣ እሱ ግን የከሃዲዎችን ፊት ፍለጋ በሙስሊሙ ደም ይቀልዳል።

ታዲያ ይህ መጅሊስ ውክልናው ለማን ነው?! ለህዝበ–ሙስሊሙ እንዳልሆነ እንዲህ ያሉ በርካታ ተግባሮቻቸው እየገለፁልን ነው። ከሀዲዎች ተገደለብን እያሉ ሲያስተጋቡ ተቀብሎ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋባላቸው መጅሊስ፣ ሙስሊሙ የመስጂድ ኢማሜ ተገደለብኝ ሲል ደግሞ ለገዳዩ ወግኖ "ያልተጣራ ወሬ" እያለ የሚያጣጥልና ከቻለም ሰምቶ እንዳልሰማ የሚሆን መጅሊስ ማንን ነው የሚወክለው?!

አላህ በእዝነቱ ሙስሊሙን ከሸረኞች ሴራ ይጠብቅ!! ሀገራችንም አላህ ሰላም ያድርጋት!!
✍🏻ኢብን ሽፋ: ሙሀረም 12/1442 ዓ. ሂ
ነሀሴ 25/2012 ኢትዮ

#Join ⤵️

https://telegram.me/IbnShifa



20 last posts shown.

1 138

subscribers
Channel statistics