Forward from: Sost Kilo
ኧረ አሸሼ ፥ አሸሼ አሼሸ
አብይ መጣልን ከመሸ ።
[ ልዑል ዘወልደ ]
ወሬ ሁሉ ቲም-ለማ በሆነ ግዜ ቅዱሱን ለውጥ የሚያወድስ ዘፈን እንዲቀመር አቅጣጫ ይቀመጣል ። አቅጣጫውን ከዳላሩ (*በዶክተርዬ አክሰንት) ያስቀመጡት የዲሲ ግብረኃይሎች ናቸው ፤ ሀቅ ለመናገር ከዛ ቀድሞ አላውቃቸውም ።
ዜማና ቅንብሩን ሔኖክ ነጋሽ ሰርቶ በራሱ በ'ሔ - ሄኒ ቲዩብ እንዲለቀቅ ከስምምነት ይደረሳል ፥ ሙዚቃዊ ሀትሪክ ይሏል። ባይሆን ግጥሙ እንኳ የአንጋፋ እጅ ይዳብሰው ተብሎ ለጉምቱ ይልማ ገብረአብ ተሰጠ ።
ዜማ ልምምዱ በጎን ይጧጧፍ ጀመር ። ዘፈኑ ላይ በስቱዲዮ በኩል ያለፉ ሁሉ በአጃቢነት ተሳተፉ ። ፋሲል ደሞዝና ( ዛሬ ለውጡን ሊጠላ ነገር ) አብዮት ካሳነሽ በእንቅጥቅጥ ሸጋ ዱየት ወጣቸው ።
ስራው እየተሳለጠ ሳለ ችግር አይኑ ይጥፋ ችግር ተፈጠረ ። ይልማ የአዝማቹን መግቢያ እንደፃፈ ጨንጓራውን አመመው ። በአራቷ መስመር አረጠ ።
ኧረ አሸሼ ፥ አሸሼ አሸሼ
አብይ መጣልን ከመሸ ፤
ኧረ እንድያ ነው እንድያ
ፀሐይ ወጣልን ከወድያ ። (00:21)
ስራው ጊዜውን ጠብቆ ካልወጣ ጭንቅ ሊሆን ነው ። እንደ ደልፊ ሚቲንግ ሁሉም አስተያየቱን ከዛም ከዚ ይወረወር ገባ ። በመሀል ይልማ ጨጓራው ጋብ ሲልለት እየተነሳ የመብል ስንኝ ወርውሮ ይተኛል ።
ሠላም ነው ድግሱ
ኑ ፀበል ነው ቅመሱ - ሃሃ (04:16)
የሆነ ቀን እንዲሁ ከአልጋው ተነስቶ መድሀኒቴን ስጡኝ ሲል ፥ በመድሀኒት አንድ ሌላ አንጓ መጣለት ፤ ወስዶ ሰካው ።
መድኃኒት ወጣልሽ ኢጦቢያ ከጉያሽ
ደመቀ መኮንን ሆኖልሻል ቀያሽ - ሃሃ (5:34)
በዛ አካሄድ ሰባት ደቂቃ ሙሉ መቀጠል ስላልተቻለ ማሲንቆ ገዝጋዡ ዳዊት " እንዲያ እንዲያ " ከሚል ሐረግ ጋር ረጅም ትራክ ተሰጠው ። ነገር ግን ትርፉ የአብዮት ካሳን አንገት በእስክስታ ማዛል ሆነ ። ጀብደኛው አብዮት አንገቱ ከመሸማቀቁ በፊት ፋሲልን ይዞ ደውለለኝ ።
- ኧረ ግጥሙን በምን እንጨርሰው ?
- በመደመር ሃሃ
( ፋሲል በመሃል ገብቶ...)
- ዋ ! አትቀልድ'ዪ አባ ፥ ታሜሪኻ መስሎኝ ምንደውል
- ሰለም ነው ፋሲሎ !
- አለሁ የናቴ ልጅ ፥ ኧረ በጀ በለን?
- እኔ'ኳ ከመሰረቱ አዝማቹ ራሱ ይቀየር ባይ ነኝ ።
ኧረ አሸሼ ፥ አሸሼ አሸሼ
አብይ መጣልን ከመሸ ፤
ኧረ እንድያ ነው እንድያ
ፀሐይ ወጣልን ከወድያ ። (02:40)
- አይ እድሌ ፥ ምኑ ይቀየራል ይሄ አሁን ?
- አንደኛ " ፀሐይ ወጣልን ከወዲያ " ማለት ትልቅ ስተት ነው ። ፀሐይ እኮ አትወጣም ፋሲሎ ፥ የሌትና ቀን ፈረቃ ምድር መሽከርከሯ ያመጣው ሁነት ነው ።
- አሯ ፥ ለያ ኖሯል ምራብ ተ'ምስራቅ ምንከላወሰው ? አፈር በበላሁ ፥ ሁለተኛውስ ?
- " አሸሸ አሸሸ ፥ አብይ መጣልን ከመሸ " ማለት ከምሽት ለጥቆ ያለው እንግዲህ ለሊት ነው ። ከጨለማው ዘመን ይባስ ወደ ድቅድቁ ገባን መሆኑ እኮ ነው ።
- ማነህ ልዑል
- አቤት
- በደሞዝ ሞት ፥ ወያኔ ነህ አደል ?