Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ~ ~ ~ ~~~~ ~ ~~~~ ~~
ሱፍዮች ይሄ ከዘመናት በኋላ በሺዐዎች የተጠነሰሰው መውሊድ ቢድዐ እንደሆነ ሲኮነንባቸው የማይገናኘውን ሁሉ በግድ እየጎተቱ ማስረጃ ሊያደርጉ ሲውተረተሩ ይታያሉ። ለሚያመጧቸው “መረጃዎች” ሁሉ እንዳመጣጣቸው ዝርዝር ምላሽ መስጠት ቢቻልም ለሁሉም ግን አንድ ጥቅል ምላሽ መስጠት ይቻላል። እርሱም የምትጠቅሷቸው የቁርኣን አንቀፆችና ሐዲሦች እውነት ለመውሊድ ማስረጃ ቢሆኑ ኖሮ ልክ ዛሬ በምታከብሩት መልኩ ያኔም ይከበር ነበር የሚል ነው። ነብዩ ﷺ ምርጥነቱን በመሰከሩለት ቀደምት ትውልድ አለመፈፀሙ ያለ አግባብ የምታጣቅሷቸው የቁርኣን አንቀፆችና ሐዲሦች መልእክት ፈፅሞ ለመውሊድ ድጋፍ እንደማይሆን በቂ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም መውሊድ በነዚህ ማስረጃዎች ውስጥ ቢጠቀስና ኸይር ቢሆን ኖሮ ከማንም በፊት እነሱ ይፈፅሙት ነበርና። መቼም ከነሱ በላይ ነብዩን ﷺ እንወዳለን እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን።
ወደዝርዝር ነጥቦች ስንመጣ እንዚህ የመውሊድ አጋፋሪዎች ከሚያጣቅሷቸው “መረጃዎች” ውስጥ አንዱ የሚከተለው ህልም ነው፦
“የነብዩ ﷺ አጎት ዐባስ አቡ ለሀብን በህልማቸው አዩት። ስለሁኔታው ሲጠይቁት ዘወትር ሰኞ ቅጣት እንደሚቃለልለትና ይህ የሆነበት ሰበቡም ነብዩ ﷺ መወለዳቸውን ያበሰረችውን ሱወይባ የተባለች አገልጋዩን ነፃ ስለለቀቃት መሆኑን ገለፀ። ዐባስ ህልማቸውን ለነብዩ ﷺ አወጉ። እርሳቸውም በዝምታ አፀደቁት። ቡኻሪ 'ሙዐለቅ' በሆነ ሰነድ የዘገቡት ሐዲሥ ነው” ይላሉ።
ከዚህ ታሪክ ውስጥ ለመውሊድ ማስረጃ ሊያደርጉ የሚፈልጉት አቡ ለሀብ “ዘወትር ሰኞ ቅጣት የሚቃለልለት ሰበቡ ነብዩ ﷺ መወለዳቸውን ያበሰረችውን ሡወይባ የተባለች አገልጋዩን ነፃ ስለለቀቃት ነው። ስለዚህ ካፊር በሳቸው ልደት ተደስቶ ይህን በማድረጉ የቅጣት ማቅለያ ካገኘ ሌላው ተደስቶ መውሊዳቸውን ቢያክብርማ የበለጠ ያገኛል” የሚል ነው።
መልስ፡-
1. በመጀመሪያ ይህንን ታሪክ በቡኻሪ ስም ማውራት ማጭበርበር ነው። ምክንያቱም የታሪኩ ጫፍ እንጂ እነሱ መረጃ የሚያደርጉት ክፍል ቡኻሪ ውስጥ አይገኝምና። የቡኻሪ ዘገባ ይሄውና፡-
قَالَ عُرْوَةُ، وثُوَيْبَةُ مَوْلاَةٌ لِأَبِي لَهَبٍ: كَانَ أَبُو لَهَبٍ أَعْتَقَهَا، فَأَرْضَعَتِ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَلَمَّا مَاتَ أَبُو لَهَبٍ أُرِيَهُ بَعْضُ أَهْلِهِ بِشَرِّ حِيبَةٍ، قَالَ لَهُ: مَاذَا لَقِيتَ؟ قَالَ أَبُو لَهَبٍ: لَمْ أَلْقَ بَعْدَكُمْ غَيْرَ أَنِّي سُقِيتُ فِي هَذِهِ بِعَتَاقَتِي ثُوَيْبَةَ
“ዑርዋ እንዲህ አለ፡- ‘ሡወይባህ የአቡ ለሀብ ባሪያ ናት። አቡ ለሀብ ነፃ አውጥቷት ነበር። ከዚያም ነብዩን ﷺ አጥብታለች። አቡ ለሀብ ሲሞት ጊዜ ከቤተሰቡ ውስጥ የሆነ ሰው በህልም በክፉ ሁኔታ አይቶት ‘ምን አገኘህ?’ ሲለው አቡ ለሀብ፡ ‘ከናንተ በኋላ (እረፍት) አላገኘሁም። ባይሆን እኔ ሡወይባን ነፃ በማውጣቴ በዚች (በአውራ ጣቱና በአመልካች ጣቱ መካከል ባለችው ክፍል) ጠጥቻለሁ’ አለ።” [ቡኻሪ፡ 5101]
እንደምታዩት በቡኻሪ ዘገባ ውስጥ “ዘወትር ሰኞ ቅጣት እንደሚቃለልለትና ይህ የሆነበት ሰበቡም ነብዩ ﷺ መወለዳቸውን ያበሰረችውን ሱወይባ የተባለች አገልጋዩን ነፃ ስለለቀቃት መሆኑን ገለፀ” የሚል የለም።
2. ቡኻሪ ውስጥ የሚገኘው ዘገባ እራሱ ለመውሊድ መረጃ የሚሆን ቃል ካለመያዙም ጋር ሙርሰል ነው- ቆራጣ። ዑርዋ ከማን እንደሰማው አልጠቀሰም። ሙርሰል ማለት አንድ ታቢዒይ ሶሐባን ሳያጣቅስ የሚያወራበት ሰነድ ነው። እንዲህ አይነት የተቆረጠ ሰንሰለት ለማስረጃነት ብቁ አይደለም።
ብዙሃኑ የሐዲሥ ምሁራን ሙርሰል ከደካማ ሐዲሥ እንደሚመደብ ነው የገለፁት። እዚህ ላይ “ፉቀሃዎች ሙርሰል ተቀባይነት አለው ብለዋል” የሚል ሙግት አይሰራም። ምክንያቱም በየትኛውም የእውቀት ዘርፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዘርፉ ምሁራን ነው። እዚህም ላይ ጉዳዩ የሐዲሥ ጥናት እንደመሆኑ የሐዲሥ ምሁራኑ አቋም ቅድሚያ ይሰጠዋል። አልኢማም ሙስሊም፡- “በኛም ይሁን በዘርፉ ምሁራን መሰረታዊ አቋም ሙርሰል ብቁ መረጃ አይደለም” ብለዋል። [ሙስሊም፡ 1/23] ኢብኑ አቢ ሓቲምም እንዲህ ይላሉ፡- “አባቴንና አቡ ዙርዐን ‘ሙርሰል ሐዲሦችን ማስረጃ አድርጎ መጥቀስ አይቻልም። ማስረጃ የሚፀናው ሰንሰለታቸው የተሟላ በሆኑ ትክክለኛ ሐዲሦች ነው’ ሲሉ ሰምቻለሁ። እኔም እንዲሁ ነው የምለው።” [አልመራሲል፡ 7] ኢብኑ ሶላሕም “የሙርሰል ብይኑ የደካማ ሐዲስ ብይን ነው። … ሙርሰልን መረጃ ማድረግ እንደማይቻልና ብይኑም ደካማ እንደሆነ የገለፅነው የብዙሃኑ የሐዲሥ ሐፊዞችና የትውፊት ሀያሲዎች እይታ የፀናበት ነው። በድርሳኖቻቸውም ተቀባብለውታል። የምዕራቡ ሓፊዝ ኢብኑ ዐብዲል በርም ከበርካታ የሐዲሥ ምሁራን ይህን ካወሱት ናቸው።” [ሙቀዲመቱ ኢብኑ ሶላሕ፡ 51-55] ሸይኹል አልባኒም ረሒመሁላህ “ከሐዲሥ ጥናት ዘርፍ ብዙሃኑ የሐዲሥ ምሁራን ዘንድ የሚታወቀው ሙርሰል የሆነ ሐዲሥ ከደካማ ሐዲሥ ክፍሎች ውስጥ እንደሆነ ነው” ይላሉ። [አዶዒፋህ፡ 1/55]
ኢብኑ ረጀብ ደግሞ የሙሐዲሦቹና የፉቀሃዎቹ ሀሳቦች ያን ያህል የሚለያዩ እንዳልሆኑ ይገልፃሉ። ምክንያቱን ሲገልፁም ሙሐዲሦቹ ሙርሰል ሐዲሥን ሶሒሕ እንዳልሆነ የሚገልፁት ወደነብዩ ﷺ የሚያደርሰው ሰነድ የተቆረጠ ስለሆነ ነው። የፊቅህ ምሁራኑ ሙርሰል ሐዲሥን “ሶሒሕ ነው” የሚሉበት ምክንያት ደግሞ የሐዲሡ መልእክት ጤናማ ሲሆንና ብርቱ የሆነ መሰረት እንዳለው የሚያመላክቱ ጠቋሚዎች ሲኖሩ ነው። [ሸርሑ ዒለሊ ቲርሚዚ፡ 1/543] ሲጠቃለል ሙርሰል ሐዲሥ በራሱ ደካማ ስለሆነ መረጃ ሆኖ መቅረብ አይችልም። መሰረት እንዳለው የሚጠቁም አጋዥ ሲያገኝ ግን ብዙሃኑ የፊቅህ ምሁራን መረጃ እንደሚሆን ጠቁመዋል። ስለዚህ እዚህ ላይ ለመውሊድ መረጃ ተደርጎ የቀረበው የዑርዋ ሙርሰል በሙሐዲሦች ብይን መሰረት ደካማ ነው። ፉቀሃዎች ዘንድ ዋጋ የሚያሰጠው ጠንካራ መሰረትም የለውም። እንዲያውም ከቁርኣን ጋር የሚጋጭ መልእክት አለው። አላህ {በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም} ሲል በዚህ የዑርዋ ሙርሰል ላይ ግን ከሃዲው አቡ ለሀብ “ጠጣሁኝ” እያለ ነው። በዚህ መልኩ ለእርጉሙ አቡ ለሀብ ቀርቶ ለአቡ ጧሊብም አልተገኘም።
3. “ይሁን” ብለን ሶሒሕ እንደሆነ ብንቆጥረው እንኳን ለመውሊድ ቢድዐ መረጃ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ህልም ነውና። በህልም ላይ ተመስርቶ ሸሪዐዊ ብይን መስጠት አይቻልም። ይሄ የተረጋገጠ ሐቅ ነው። ነብዩን ﷺ በህልም አይቶ ሸሪዐዊ ብይን መውሰድ ካልተቻለ ከሃዲው አቡ ለሀብን በህልም አይቶስ ብይን መውሰድ ይቻላልን? እንዴት ተብሎ?!!
የመውሊድ ታጋይ ሱፍዮች ግን ከዚህ ለማምለጥ አንድ መላ ይዘይዳሉ። እሱም “ይህ ተራ ህልም ሳይሆን ነብዩ ﷺ ሰምተው ያፀደቁት ነው” የሚል ነው። ይሄ የለየለት ቅጥፈት ነው። ቡኻሪ ውስጥ ቀርቶ ኩቱቡ ሲታ ውስጥ እራሱ አይገኝም። እነዚህ ሰዎች ቢድዐቸውን ለማሻሻጥ ሲሉ በነብዩ ﷺ ላይ እንኳ ለመዋሸት የማያመነቱ ናቸው። ሙርሰልነቱን (ቆራጣነቱን) ካመኑ በኋላ “ነብዩ ﷺ ሰምተው ያፀደቁት ነው” ማለታቸው ደግሞ ሰዎቹ ምን ያክል አይናቸውን በጨው ያጠቡ እፍረተ ቢሶች እንደሆኑ የሚያሳይ ነው።