ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ
ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ !
"ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? "
ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል !
ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር
@JemalEndroAbuMeryem

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት ይቻላልን?
~
ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት አይቻልም የሚለው የአራቱም የፊቅህ መዝሀቦች አቋም ነው። አልፎም ባጠቃላይ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። መረጃ የሚደግፈውም ይህንኑ ነው። ሁለት መረጃዎችን እጠቅሳለሁ:-

♻️ [መረጃ አንድ]:- ሐዲሣዊ ማስረጃ ♻️

ነብያችን ﷺ ወደ የመን በላኩት ደብዳቤ ላይ
أَنْ لَا يَمَسَّ الْقُرْآنَ إِلَّا طَاهِرٌ
"ቁርኣንን ጦሀራ የሆነ እንጂ እንዳይነካው" ሲሉ አሳስበዋል። [ሙወጦእ: 468]
ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ "ሶሒሕ" ብለውታል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7780]

👉🏾 ብዥታ!
~
ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት ይቻላል የሚሉ ዓሊሞች ግን "የሐዲሡ መልእክት ሌላ ነው። 'ጦሀራ የሆነ እንጂ እንዳይነካው' ማለት 'ሙስሊም እንጂ እንዳይነካው' ማለት ነው" ይላሉ። ለዚህም "ሙስሊም አይንነጀስም" የሚለውን ሐዲሥ ያጣቅሳሉ።
ይሄ ግን - ወላሁ አዕለም - ልክ አይደለም። ይልቁንም መልእክቱ በቀጥታ ጦሀራ/ውዱእ የሌለው ሰው እንዳይነካው ማለት ነው። የሐዲሡ ሌሎች ዘገባዎች ይህንን መልእክት ግልፅ ያደርጉልናል። ለምሳሌ:-

✅ 1ኛ፦ የዐብዱረዛቅ ዘገባ ላይ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
لَا يُمَسُّ الْقُرْآنُ إِلَّا على طُهْرٍ
"በጦሀራ ላይ ተሁኖ እንጂ ቁርኣን አይንነካም።" [አልሙሶነፍ: ቁ. 1328]

✅ 2ኛ:- የኢብኑል ሙንዚር ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
لَا تَمَسَّ الْقُرْآنَ إِلَّا على طَهورٍ
"በጦሀራ ላይ ሆነህ እንጂ ቁርኣን እንዳትነካ።" [አልአውሰጥ፡ 2/103]

▶️ ልብ በሉ! ሙስሊሙን ሰው ነው "በጦሀራ ላይ ሆነህ እንጂ ቁርኣንን እንዳትነካ" ያሉት። ይህም ሐዲሡን "ሙስሊም ያልሆነ እንዳይነካው ማለት ነው" በማለት የተረጎሙት ልክ እንዳልሆኑ ያሳያል።

♻️ [መረጃ ሁለት]:- ቁርኣናዊ ማስረጃ ♻️

በቁርኣን ውስጥም እንዲህ የሚል መጥቷል:-
{ لَّا یَمَسُّهُۥۤ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ }
"የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም።" [አልዋቒዐህ፡ 79]

በርግጥ የዚች አንቀፅ ቀጥተኛ መልእክት ጥብቁን ሰሌዳ (ለውሐል መሕፉዝን) የሚገልፅ እንደሆነ አገባቡ ያሳያል። ይሁን እንጂ መልእክቱ ለቁርኣንም የሚውል እንደሆነ ጥቆማ አለው ይላሉ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [ሸርሑል ዑምደህ: 384] ዝርዝሩን ከዚህ በላይ ላለማስረዘም ስል ስለተውኩት በቦታው ተመልከቱት።

ባይሆን ይህንን ሃሳብ የሚደግፍ አንድ የሶሐቢይ ንግግር ልጥቀስ። ሶሐቢዩ ሰልማኑል ፋሪሲይ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ናቸው። ዐብዱረሕማን ብኑ የዚድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦

"ከሰልማን ጋር በሆነ ጉዳይ ላይ ነበርን። እሳቸው ጉዳያቸውን ለመፈፀም (ለመፀዳዳት) ሄደው ተመለሱ። 'ውዱእ አድርግማ የዐብደላህ አባት! ምናልባት ከቁርኣን ስለሆኑ አንቀፆች ልንጠይቅህ እንችላለን' አልናቸው። በዚህን ጊዜ (ሰልማን) እንዲህ አሉ፦
فَاسْأَلُوا، فَإِنِّي لَا أَمَسُّهُ، إِنَّهُ {لَا يَمَسُّهُ إِلَّا الْمُطَهَّرُونَ}
'ጠይቁ! እኔ አልነካውም። ነገሩ {የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም}።'
ከዚያም "ጠየቅናቸው። ውዱእ ሳያደርጉ ቀሩልን" አሉ። [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ ቁ. 1100]

መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት ጦሀራ የሌለው ሰው ቁርኣንን ሊነካ አይገባም የሚለው የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። ኢብኑ ዐብዲል በር እንዲህ ይላሉ፦
أجمع فقهاء الأمصار الذين تدور عليهم الفتوى وعلى أصحابهم بأن المصحف لا يمسه إلا طاهر
"ጦሀራ ላይ የሆነ ካልሆነ በስተቀር ሙስሐፍ እንደማይንነካ ፈትዋ የሚቀርብላቸው የሙስሊም ሃገራት ሊቃውንት እና ባልደረቦቻቸው ወጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።" [አልኢስቲዝካር፡ 8/10]
ከኢብኑ ሁበይራም በተመሳሳይ ኢጅማዕ እንዳለበት ተጠቅሷል። [አልኢፍሷሕ፡ 1/68]

ይሄ እንግዲህ እነሱ በሚያውቁት መጠን ነው። እንጂ ጥቂቶች ቢሆኑም የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቁ ተገኝተዋል።

የሆነ ሆኖ ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት አይቻልም የሚለው ከሶሐቦች ውስጥ ከ0ሊይ፣ ከሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ፣ ከኢብኑ ዑመር፣ ከሰልማኑል ፋሪሲይ - ረዲየላሁ ዐንሁም - ተገኝቷል። ከሶሐቦች ውስጥ እነዚህን የተቃረነ አይታወቅም ይላሉ ነወዊይ እና ኢብኑ ተይሚያህ። [አልመጅሙዕ፡ 2/80] [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 21/266]
ይህንን ሃሳብ አስምሩበት። ከሶሐቦች ውስጥ እነዚህን የተቃረነ አይታወቅም። ስለዚህ ውዝግቡ የመጣው ከሶሓቦች በኋላ ነው ማለት ነው። አዋቂው አላህ ነው።

ማሳሰቢያ፦ ሞባይልና መሰል 'ዲቫይሶች'ን ተጠቅሞ መቅራት እዚህ ውስጥ አይገባም። እንዲሁም ትርጉምና የተፍሲር ኪታቦችም የሙስሐፍ ብይን ስለሌላቸው ያለ ጦሀራ መንካት ይቻላል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 21/1444፣ ሚያዚያ 04/2015)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በኒያ ጉዳይ መጨናነቅ አያስፈልግም
~
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

"ነገ ረመዷን እንደሆነ ያወቀና ሊፆመው የፈለገ ሁሉ ፆሙን ነይቷል።"

[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/215]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me//IbnuMunewor


ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!
∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼

«الليلة  (⓸)  رمضان ١٤٤٦»

ጁዝ

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله

=
t.me/abu_reyyis_arreyyis/10143


በረመዳን እንዴት እንጠቀም

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔗 t.me/Achachir_mkroch


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አደራ! ቁርኣን እንቅራ
~
በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027]
ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።"
ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ክፍል 3 የሱቢሂ ግብዣ ለአርባ ምንጮች

ረመዿን 2/1446

📖 ሱረቱል በቀራ ከ135 - 163

🎙 በኡስታዝ ወንድም ሙሐመድ ሐሰን (ጁድ) ሃፊዘሁላህ

ከአርባ ምንጭ ትዝታዎች

አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ 2010 ተመራቂ


📆 ረመዷን 3/1443

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15540


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አክታን መዋጥ
~
1. ከአቅም በላይ ከሆነ
ማስወገድ በማይችለው መልኩ ከጭንቅላቱ ቀጥታ ወደታች የሚወርድ አክታ ከሆነ ሊጠነቀቀው አይችልም፡፡ አላህ ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ነገር አይዝም፡፡

2. መቆጣጠር ሲቻል ቢዋጥስ?
ሆነ ብሎ አውጥቶ አፉ ጋር ካደረሰው በኋላ መትፋት ሲችል ቢውጠው ፆሙ ይበላሻል ያሉ ዐሊሞች አሉ፡፡ ከፊሎቹ ግን ይህም ቢሆን አይበላሽም ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ታዲያ “ፆሙ አያበላሽም” ይበሉ እንጂ ድርጊቱ ፆመኛ ለሆነም ይሁን ላልሆነ ሰው ሐራም እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ አንደኛ አፀያፊ ነው፡፡ ሁለተኛ ምናልባትም በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን የተሸከመ ሊሆን ስለሚችል ወደ ሆድ ሲገባ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ነው፡፡ [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 6/428] ከውዝግብ ለመውጣት ሲባል መራቁ ራሱን የቻለ ዋጋ አለው፡፡ ወልላሁ አዕለም፡፡
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለባለሃብቱ!
~
ለገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የምትከፍለውን ግብር እያሰብክ ከዘካ እንዳትዘናጋ። ዘካ ለደካሞች የሚሰጥ ሐቅ እንጂ ለሹማምንት የሚሰጥ ግብር ወይም ጉቦ አይደለም። አኺል ከሪም! ገንዘቡን የሰጠህ አላህ ነው። እንጂ ካንተ የበለጠ የሚለፉ ድሃዎች በዙሪያህ አሉኮ። በእውቀቴ አገኘሁት እንዳትል ካንተ የበለጠ የተማሩ ድሃዎች ሞልተዋልኮ። ጥለኸው ለምትሄደው ገንዘብ ብለህ በራስህ ላይ አትሳሳ። እውነተኛው ያንተ ገንዘብ ማለት ለአኺራህ ያሻገርከው ነው። ዐብዱላህ ብኑ ሺኺር - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
أتَيْتُ النَّبيَّ صلى الله عليه وسلم، وَهُوَ يَقْرَأُ: {أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ} قَالَ: ((يَقُولُ ابْنُ آدَمَ: مَالِي، مالي، وَهَلْ لَكَ يَا ابْنَ آدَمَ مِنْ مَالِكَ إلا مَا أكَلْتَ فَأفْنَيْتَ، أَو لَبِسْتَ فَأَبْلَيْتَ، أَوْ تَصَدَّقْتَ فَأَمْضَيْتَ؟)
"ነብያችን ﷺ ዘንድ መጣሁኝ። {በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ} የሚለውን እየቀሩ ነው። ቀጥለው እንዲህ አሉ፦
'የአደም ልጅ 'ገንዘቤ ገንዘቤ!' ይላል። የአደም ልጅ ሆይ! በልተህ ከጨረስከው፣ ለብሰህ ካሳለቅከው፣ ሶደቃ ሰጥተህ አጅሩን ካሻገርከው ውጭ ገንዘብ አለህ'ንዴ?' " [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2958]
እወቅ! የምታወጣው ካጠቃላይ ገንዘብህ 2.5 ከመቶ ብቻ ነው። መቶ ብር ያለው ሰው ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ቢያወጣ ብዙ ነው ወይ? ምስሉ ላይ በጣት የተጠቆመችዋን ተመልከት። ካጠቃላይ ሃብትህ ይቺን ታክል ለዘመዶችህ፣ ለጎረቤቶችህ፣ ለምታውቃቸው ምስኪኖች ብታወጣ ብዙ ነውን? በአኺራ እጥፍ ድርብ ምንዳ እንደሚጠብቅህ የቂን የለህም ወይ?
ደግሞም እወቅ! ወላሂ ሶደቃ ሃብትን አይቀንስም። ይልቁንም ይበልጥ በረካ እንዲኖረው ነው የሚያደርግልህ። አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ያግራልህ።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዛሬ እሁድ ረፋድ በሑዘይፋ መስጂድ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል ኢንሻአላህ።

አድራሻ :- ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor




የረመዷንን ሌቦች ተጠንቀቁ!
|•|
አንደኛው ሌባ፦
ቴሌቭዥን ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ ከፍታ አጋዥ ካልሆኑ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ነው። በተለይ ደሞ የረመዷን ሙሰልሰላቶችን እና አዘናጊ ድራማዎችን ተጠንቀቁ፤ የረመዷን ዉድ ጊዜያት ለዉድ ነገሮች መዋል አለባቸው፡፡

ሁለተኛው ሌባ
ስልክ ብዙ ማውራት ለብዙ ስህተት ያጋልጣል፣ ትርፍ ንግግር ወደ ሀሜትና ያልታሰቡ ወንጀሎች ይመራል፤ለተሻለ ምንዳ በረመዷን በንግግር ጭምር ቁጥብ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ሦስተኛ ሌባ፦
ወጣ ገባ ማብዛት/መዞር፡፡ በረመዷን ከመስጊድ እና ከቤት የበለጠ ማረፊያ የለም፡፡ ወደ ከተማም ይሁን ወደ ገበያ ያለበቂ ምክንያት ወጣገባ ማብዛት ዐይንንም ሆነ ጆሮን ያልሆነ ነገር ይጥላል፡፡ፆምን ይሰርቃል፤ ምንዳዉንም ያጓድላል፡፡ 

አራተኛ ሌባ፦
ማምሸት፡ ያለምክንያት ማምሸት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለዉም፡፡ የረመዷን ምሽቶች ምርጥና ዉብ ናቸው፡፡ በቁርኣን፣ ዚክር እና በተለያዩ ዒባዳዎች መዋብ አለባቸው፡፡

አምስተኛ ሌባ፦
ኩሽና:በተለይ ለሴቶች፡፡ሙሉዉን ረመዷን ማዕድ ቤት የሚያሳልፉ ቁርኣንን፣ ሶላትና ዚክርን የረሱ ብዙ ናቸው፡፡ ረመዷን የፆም ወር ነው፡፡ ትልቁን ትኩረት ለሆድ መስጠት ዓላማዉን መሳት ነው የሚሆነው፡፡

ስድስተኛው ሌባ፦
ሶሻል ሚዲያ፡፡ ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ችግር ሆኗል፡፡በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ነው፡፡ በዚህም ከዚክር፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ እንዳንጠቀም ሆነናል፡፡ እንጠንቀቅ፡

፡via AbuSufiyan

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15534


📌 አደራ!
ኒያን ማሳደር እንዳትረሱ፣ ማለትም ፈጅር ከመውጣቱ በፊት በሌሊቱ ወቅት የመፆሙ ኒያ (ቆራጥ ሀሳብ) በቀልቡ ሊገኝ ይገባል።

🚫 ኒያ ደግሞ በአፍ ወይም በቃል የሚባል ነገር የለውም፣ ቦታው በቀልብ በቁርጥ ማሰብ ብቻ ነው።

🤲 አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን። በፆም፣ በሶላት ፣ በዒባዳ ላይ ይገዘን፣ አብሽሩ በርቱ ያጀመዓ።


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ሰሑር ተመገቡ። በሰሑር ውስጥ በረካ አለና።" [አልቡኻሪይ፡ 1923] [ሙስሊም፡ 1095]

በጤና ምክንያት የሚከብዳችሁ ካላችሁ ቀለል ያለ ነገርም ቢሆን ተመገቡ። እሱ ቢቀር ጥቂት የተምር ፍሬዎች ቢሆኑ እንኳ። ይህም ቢቀር ውሃም ቢሆን ተጎንጬ። በረካው አይለፋችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


🎉
እንኳን ለ1446ኛው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ

የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ቅዳሜ የካቲት 22, 2017 E.C. (March 1, 2025 G.C.) የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል ።
ረመዿን 1/1446


አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዷን ሙባረክ! 🌙✨


ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም
ከወሎ–ወረኢሉ


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15530


‏عاجل:አላሁ አክበር አላሁ አክበር

‏رؤية هلال رمضان في تمير..
‏وغدا السبت أول أيام رمضان بالسعودية .

➜ነገ ቅዳሜ ረመዳን 1 ነው

March 1 2025
ramadan 1 1446

የሳዑዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ።


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የጁሙዐ ኹጥባ በሌላ ቋንቋ
~
በሃገራችን ከጥንት ጀምሮ ኹጥባ የሚደረገው በዐረብኛ ቋንቋ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከተማ አካባቢ ካለው ጥቂት ለውጥ ውጭ በሰፊው ያለው አፈፃፀም ይሄው ነው። የዚህ መነሻው በጉዳዩ ላይ ያለው የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። ይህንን መጥቀስ ያስፈለገኝ የጁሙዐ ኹጥባ በዐረብኛ መደረጉ ያን ያህል የሚያንጨረጭር ነገር እንዳልሆነ ለመጠቆም ነው።

ከዚህ ውጭ ሺርክና ቢድዐ ላይ ድምፁ ተሰምቶ የማያውቅ፣ ወገናችን የተዘፈቀበትን ሺርክ እንዲሁም የጥፋት ቋት የሆነውን መውሊድ ለስለስ ባለ ቃና እንኳ ለመቃወም ወኔ የሌለው አካል፣ እንዲያውም ከዚህ በተቃራኒ ሺርክና ቢድዐን የሚዋጋው ደዕዋ የሚጎረብጠው አካል ኹጥባ ለምን በዐረብኛ ይደረጋል ብሎ ደም ስሩ ተገታትሮ እያበሻቀጠ እየተወራጨ ሲያወራ ማየት አስገራሚ ነው።

ለማንኛውም ከኢስላም ሊቃውንት ውስጥ ኹጥባ በዐረብኛ ብቻ ነው መደረግ ያለበት የሚሉት ዓሊሞች ብዙሃን ናቸው። ከአራቱ መዝሀቦች ውስጥ ከአቡ ሐኒፋ ውጭ የማሊኪያ፣ የሻፊዒያ፣ የሐናቢላ እና የአቡ ሐኒፋ ተማሪዎች የሆኑት የአቡ ዩሱፍ እና የሙሐመድ አቋም ነው። [አልመውሱዓቱል ፊቅሂየህ፡ 19/180 - 181]
በዚህ ላይ የተለየ የተንፀባረቀው እንደምታዩት ከአቡ ሐኒፋ ነው። የአቡ ሐኒፋም ቢሆን "በዐረብኛ መሆኑ ሸርጥ አይደለም፣ በሌላም ቋንቋ ይቻላል" የሚል እንጂ በዐረብኛ መሆኑን የሚነቅፍ አይደለም። እንዲያውም የተወደደ ነው የሚል ነው።

መነሻ መሰረቱ ይሄ ከመሆኑ ጋር ለመዝሀብ ጭፍን ውግንና የሌላቸው የዘመናችን ታላላቅ ዑለማኦች ለምሳሌ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ የሳዑዲ የታላላቅ ዑሉማኦች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በዐረብኛ ቋንቋ ማድረጉን የሚያስገድድ ማስረጃ ስለሌለ ታዳሚውን ከግምት ባስገባ መልኩ በቋንቋቸው ማድረግ ይቻላል ይላሉ። [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብኒ ባዝ፡ 12/372] [ፈታዋ ኑሪን ዐለ ደርብ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን] [ፈታዋ ለጅነቲ ዳኢመህ፡ 8/253] ሸይኹል አልባኒይ ደግሞ ኹጥባ በመሰረቱ በዐረብኛ መሆን እንዳለበት አስረግጠው ከመናገራቸው ጋር የኹጥባው መልእክት ለህዝቡ ይደርስ ዘንድ ኸጢቡ ከሚንበር ከመውረዱ በፊት ለታዳሚው የኹጥባውን መልእክት በቋንቋቸው ያስጨብጣቸው ይላሉ። [ተስጂላቱን ሙተፈረቃህ ካሴት ቁ. 304]
ልብ በሉ! አልባኒይ ዐረብ አይደሉም። ስርአት የሌለው አካል በአጉል ዘረኝነት እንዳይወርፋቸው በመስጋት ነው ይህን የምጠቁመው።

ሃሳቤን ስጠቀልል መባል ያለበት ከዐረብኛ ውጭ ባለ በሌላ ቋንቋ መደረጉን የሚከለክል ማስረጃ እስከሌለ ድረስ ማህበረሰባዊ ፋይዳውን በመመልከት በየካባቢው ህዝቡ በሚናገረው ቋንቋ ቢሆን ይሻላል ነው። ከዚህ አልፎ ለምን በዐረብኛ አደረጋችሁ ብሎ ማበሻቀጥ አይገባም። እንዲህ አይነት አካሄድ የራስን ጅህልና ነው የሚያጋልጠው። ከዚህ ቀጥሎ ያለው ከአመት በፊት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፌው የነበረ ፅሁፍ ነው።
.
በሀገራችን አብዛኛው ህዝብ ከጁሙዐ ኹጥባ አይጠቀምም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ኹጥባው የሚተላለፍበትን ዐረብኛ ቋንቋ ህዝባችን የማያውቅ መሆኑ ነው።
ህዝባችን ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ ስለዲኑ ያውቅ ዘንድ ባጠቃላይ ከኹጥባ ይጠቀም ዘንድ ኹጥባው በየአካባቢው ቋንቋ ቢቀርብ ተመራጭ ነው። በየሳምንቱ ስለ እምነቱ ጉዳዮች የ20/ 30 ደቂቃ ምክር ማግኘት ቀላል አይደለም። ለአመታት ሲደመር የሚኖረውን ፋይዳ ደግሞ አስቡት። በአንፃሩ ለአመታት ሰው ምንም ሳይጠቀምበት ሲያልፍ ደግሞ ያስቆጫል።
ኹጥባ ማለት ተግሳፅ ነው፣ ምክር ነው። የቋንቋ ልዩነት ከኖረ ግን የኹጥባው አላማ አልተሳካም፣ ግቡን አልመታም።
በአሁኑ ሰዐት አንዳንድ አካባቢዎች በአካባቢው ቋንቋ ኹጥባ በማድረግ ጥሩ እያስተማሩ ነው። ይሄ ነገር በሌሎችም ቦታዎች ቢለመድ ህዝባችን ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆን ነበር።
በነገራችን ላይ ኹጥባን ከዐረብኛ ውጭ ባለ ቋንቋ ማድረግን አስመልክቶ ከዑለማዎች የተለያዩ ሀሳቦች ቢሰነዘሩም የሚከለክል ግን አንድም ማስረጃ የለም። ለዚህም ነው በርካታ የዘመናችን ዐሊሞች በሌሎች ቋንቋዎች ማድረግን የሚፈቅዱት።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


ማስታወሻ ስለ ዕውቀት
በኡስታዝ አንሷር ሰይድ (ሙርሰል)



አባያ ካምፓስ የመለያያ ያደረገልን ነሲሃ ነው ተጋበዙ
አሁን ያለበትን የፈለገ አንባሰል ወረዳ


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15528




ክፍል 2 የሱቢሂ ግብዣ ለአርባ ምንጮች

📖 ሱረቱል በቀራ ከ135 - 163

🎙 በኡስታዝ ወንድም ሙሐመድ ሐሰን (ጁድ) ሃፊዘሁላህ

ከአርባ ምንጭ ትዝታዎች

📆 ረመዷን 3/1443

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15524


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ጣፋጭ የቁርአን ግብዣ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጫሞ ካምፓስ የሴቶች ዶርም 2010

ከJemalEndro33 ቲክቶክ ፔጅ የተወሰዴ


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15523

20 last posts shown.