ክለቦች የምዕተ ዓመት የዋንጫ ረሀባቸውን ያስታገሱበት (2024/25)
1. ክሪስታል ፓላስ - በ120 ዓመት የክለቡ ታሪክ ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ ለመጀመርያ ጊዜ የኤፍ ኤ ዋንጫን ያነሳበት።
ንስሮቹ ከአሁን በፊት ሁለት ጊዜ በኤፍ ኤ ዋንጫ ለፍጻሜ ቢደርሱም በማንችስተር ዩናይትድ ተሸንፈው ክብሩን ማጣታቸው ይታወሳል።
2. ጎ ኤሄድ ኤግልስ - በኤርዲቪዜው የሚሳተፈው ክለብ የደች ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ሲያነሳ ዘንድሮ ከ 93 ዓመት በኋላ ከዋንጫ ጋር የተገናኝበት ሆኗል።
3. ኒውካስል ዩናይትድ - ከተመሰረተ 133 ዓመት የሆነው ኒውካስትል የእንግሊዝ ሊግ ካፕን ለመጀመርያ ጊዜ ያነሳበት ዓመት ሆኗል።ክለቡ ከዋንጫ ጋር ሲገናኝ ደግሞ ከ70 ዓመት በኋላ ነው።
4. ቦሎኛ - በጣልያን ዋንጫ ፍጻሜ ኤሲ ሚላንን በማሸነፍ ከ51 ዓመት በኋላ ከዋንጫ ጋር የተገናኝበት ነው።
በቀጣይ ሁለት ሳምንት ውስጥ መልስ ሊያገኙ የሚችሉ የረጅም ዓመታት የዋንጫ ጥያቄዎች
• ፒ ኤስ ጂ - በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ የደረሰው የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ኢንተር ሚላን ማሸነፍ ከቻለ ለመጀመርያ ጊዜ የአህጉሩን ትልቁን ክብር የሚያሳካበት ይሆናል።
• ሪያል ቤቲስ - በአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ለፍጻሜ የደረሰው የስፔኑ ክለብ ቼልሲን ካሸነፍ ለመጀመርያ ጊዜ የአውሮፓ መድረክ ውድድር ላይ የነገሰበት ይሆናል።
• ቶተንሀም ሆትስፐርስ - በዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ከማንችስተር ዩናይትድ የሚገናኝበትን ፈተና በድል የሚወጣ ከሆነ የ40 ዓመታት የዩሮፓ ሊግ የዋንጫ ድርቁን ያስታግሳል።
• ሀሪ ኬን - በግል ደግሞ የ31 ዓመቱ እንግሊዛዊው ሃሪ ኬን ለመጀመርያ ጊዜ ከዋንጫ ጋር የተገናኝበት ዓመት ሆኖለታል።
በአንተነህ ሲሳይ
ኢቢሲ የስፖርት ገፅ ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ ኢቢሲ ድረ ገፅ ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ