EOTC ቤተ መጻሕፍት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ Channel የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ስብከትች እንዲሁም የተለያዩ ለአብነት ትምህርት የሚሆኑ በድምፅ ፤ይሁን በጹሁፍ እንዲሁም በ Video ሚለቀቅበት Channl new
ተጨማሪ ወይም ሚፈልጉትን መፃህፍት
ብለው ይጠይቁን
ማስታወቂያም እንሰራለን በውስጥ መስመር ይጠይቁን
የሰማነዉን እንናገራለን!
ያየነዉን እንመሰክራለን!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱




ቻናል መግዛት ሚፈልግ ሰው በውስጥ መስመር ያናግረኝ እውነተኛ ገዥ ከሆነ
@yesadikusitota
@yesadikusitota
@yesadikusitota














በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
#አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
#አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
፠ውኃ የሚከተርበት ቦታ ‹‹#ባሕረ_ጥምቀት(#ጥምቀተ_ባሕር_››) (#የታቦት_ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡
#ሥርዐተ_ከተራ
፠ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡
፠ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤
*ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡
*የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤
*መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡
*እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡
*ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡
*የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡
*ሕዝቡም ደግሞ ‹‹#ለጥምቀት_ያልሆነ_ቀሚስ_ይበጣጠስ›› እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ የጀብዱነት ሽልማት ያለው በሽልማቱ አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡
**ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡
ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (#የምራት_ባለተረኛ) “#ወረደ_ወልድ_እምሰማያት_ውስተ_ምጥምቃት_፤ #በፍሥሓ_ወበሰላም” (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው #ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹#አንሺዎች_›› ይባላሉ፡፡
የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዐት ነው፡፡ በዚያን ዕለት ምሽት ፈቃደኛ የሆኑ ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ ባልቴቶችና ኮረዳዎች ሕፃናትም ጭምር እዚያው በጥምቀተ ባሕሩ ዙሪያ ስለሚያድሩ እንደ የዕድሜ ደረጃቸው ማለትም በልጅነት ዕድሜ ላይ ያሉት በሀገር ባህል ዜማ ሲያመሰግኑ ፥ እናቶችም ታቦቱን የሚያሞግስ ግጥም እየገጠሙ ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ በከተሞች ደግሞ ስበከተ ወንጌልና መዝሙር ሲዘመር ያድራል፡፡
#በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት_አላቸው_እነዚሁም_፤
#ታቦቱ_የጌታችን ምሳሌ
#ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ምሳሌ
#ባሕረ_ጥምቀቱ_የዮርዳኖስ_ወንዝ_ምሳሌ
#ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን_ወደ_ቅዱስ_ዮሐንስ_እየመጡ_የንስሐ_ጥምቀት_ሲጠመቁ_የነበሩ_ሰዎች_ምሳሌ
#ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው_መድኀኔ_ዓለም_ክርስቶስ_በእደ_ዮሐንስ_በፈለገ_ዮርዳኖስ_ለመጠመቅ_ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ_ከማታው_ጀምሮ_መውረዱንና_ተራውን_ሲጠብቅ_አድሮ_መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/
#ጥምቀቱ_የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡
ትም በልጅነት ዕድሜ ላይ ያሉት በሀገር ባህል ዜማ ሲያመሰግኑ ፥ እናቶችም ታቦቱን የሚያሞግስ ግጥም እየገጠሙ ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ በከተሞች ደግሞ ስበከተ ወንጌልና መዝሙር ሲዘመር ያድራል፡፡
#በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት_አላቸው_እነዚሁም_፤
#ታቦቱ_የጌታችን ምሳሌ
#ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ምሳሌ
#ባሕረ_ጥምቀቱ_የዮርዳኖስ_ወንዝ_ምሳሌ
#ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን_ወደ_ቅዱስ_ዮሐንስ_እየመጡ_የንስሐ_ጥምቀት_ሲጠመቁ_የነበሩ_ሰዎች_ምሳሌ
#ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው_መድኀኔ_ዓለም_ክርስቶስ_በእደ_ዮሐንስ_በፈለገ_ዮርዳኖስ_ለመጠመቅ_ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ_ከማታው_ጀምሮ_መውረዱንና_ተራውን_ሲጠብቅ_አድሮ_መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/
#ጥምቀቱ_የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5


#ከተራና_ባሕረ_ጥምቀት_ጥምቀተ_ባሕር #ታቦታት_ለምን_ከመንበራቸው_ወጥተው_ያድራሉ?
#በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት #ሥርዐተ_ከተራ ……. (#ያንብቡ)

#ከተራ_፤ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡
#ከተራ_ለምን_ተባለ?
በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
#አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
#አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
፠ውኃ የሚከተርበት ቦታ ‹‹#ባሕረ_ጥምቀት(#ጥምቀተ_ባሕር_››) (#የታቦት_ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡
#ሥርዐተ_ከተራ
፠ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡
፠ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤
*ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡
*የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤
*መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡
*እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡
*ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡
*የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡
*ሕዝቡም ደግሞ ‹‹#ለጥምቀት_ያልሆነ_ቀሚስ_ይበጣጠስ›› እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ የጀብዱነት ሽልማት ያለው በሽልማቱ አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡
**ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡
ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (#የምራት_ባለተረኛ) “#ወረደ_ወልድ_እምሰማያት_ውስተ_ምጥምቃት_፤ #በፍሥሓ_ወበሰላም” (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው #ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹#አንሺዎች_›› ይባላሉ፡፡
የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዐት ነው፡፡ በዚያን ዕለት ምሽት ፈቃደኛ የሆኑ ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ ባልቴቶችና ኮረዳዎች ሕፃናትም ጭምር እዚያው በጥምቀተ ባሕሩ ዙሪያ ስለሚያድሩ እንደ የዕድሜ ደረጃቸው ማለ#ከተራና_ባሕረ_ጥምቀት_ጥምቀተ_ባሕር #ታቦታት_ለምን_ከመንበራቸው_ወጥተው_ያድራሉ?
#በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት #ሥርዐተ_ከተራ ……. (#ያንብቡ)
#ከተራ_፤ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡
#ከተራ_ለምን_ተባለ?

በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ


ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥምቀት

የጥምቀት
 #ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።


የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ፤ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ፤በአብትረ ያዕቆብ በርሀ ሥላሴክሙ ፀሐይ፤ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ፤ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ።

ዚቅ
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ፤ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ፤እለ ፩ዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ፤እለ ይከውኑ ሰማዕተ ፫ቲሆሙ፤ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ፤ከመ ይቀድስ ማያተ፤ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ጸጋ ወጽድቅሰ፤በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ።

ወረብ
መኑ ይወርድ "ውስተ ቀላይ"/፪/ ክርስቶስ ውእቱ/፪/
፩ዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ ፩ዱ ውእቱ/፪/

ነግሥ
ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ።

ዚቅ
ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ።

ወረብ
ርእዩከ "እግዚኦ"/፪/ ርእዩከ ማያት/፪/
"ደንገፁ"/፪/ ቀላያተ ማያት ደንገፁ ቀላያተ ማያት/፪/

ትምህርተ ኅቡዓት
እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅዓ፤በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ፤ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤ወማየ መንጽሔ ዚአነ።
=>ዚቅ የለውም

ወረብ
"ወደሞ ክቡረ"/፪/ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ/፪/
ወማየ መንጽሔ ዚአነ/፬/

ዓርኬ
ሰላም ለጥምቀትከ በዘቦቱ ይነጽሑ፤ኃጣዉአ ሰብእ ዘዘዚአሁ፤አመ ላዕሌከ እግዚኦ አዕዳወ ዮሐንስ ሰፍሑ፤ሶበ ርእዩከ ቀላያት ደንገፁ ወፈርሁ፤ማያትኒ በርእስከ ፈልሑ።
=>ዚቅ የለውም

ምልጣን
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤አማን፤መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።

ምልጣን ዘዜማ
እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤አማን፤መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።

አመላለስ
አማን በአማን መንክር/፪/
መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ/፪
ወረብ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ/፪/
"ወለደነ ዳግመ"/፪/ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ/፪/

እስመ ለዓለም
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ፤ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።

አመላለስ
መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ/፪/
ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ/፬/

ወረብ
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ/፪/
ከመ ያጥምቆ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ/፪/

ዕዝል
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል፤ቃለ እግዚአብሔር፤ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ወተገሠ በሥጋ፤መንፈስ ዘኢይትገሠሥ ወዘኢይትለከፍ፤ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ፤ወረደ ዲበ ምድር፤ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤በበህቅ ልህቀ በ፴ ክረምት፤በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

ምልጣን
ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ።

አመላለስ
ወገብረ መንጦላዕተ/፪/
ሥጋ ሰብእ መዋቲ/፬/

አቡን በ፭:
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤እስመ ስምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዚ በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል፤ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ዘኪያሁ ሠመርኩ ይቤ፤ወበይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል፤ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ምልጣን
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ወረ
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5


ይኽንን ያውቃሉ ?
ጥምቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ ላይ እንዲከበር ያደረገው ቅዱስ ላሊበላ እንደሆነ።

የጥምቀት ዓመታት አከባበር በኢትዮጵያ
(አጭር ታሪካዊ ዳሰሳ -)
--------------------------------------------------
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 የሚከበረው የከተራ እና የጥምቀት በዓል የዛሬውን መልክ እና የአከባበር ሥርዓት ከመያዙ አስቀድሞ በየዘመናቱ በነግሥታቱ እና በየዘመኑ በነበሩ ቅዱሳን ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ በዓሉ በርካታ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ እሴቶች ያሉት ሲሆን የዚህ አጭር ጽሑፍ ዓላማ በበዓሉ የአከባር ሥርዓት ላይ በየዘመናቱ የተደረጉትን ዐበይት ታሪካዊ ማሻሻያዎች መዳሰስ ነው፡፡
1.በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን
--------------------------------
የበዓለ ጥምቀት አከባበር በኢትዮጵያ የተጀመረው የክርስትና እምነት እንደገባ መሆኑ ቢታመንም ታቦታትን ወደ ጥምቀተ ባህር ማውረድ የተጀመረው ግን በ328 ዓ.ም በጣና ቂርቆስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ግን ከዛሬ 1,484 ዓመታት በፊት በአፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (በ530ዓ.ም) የጥምቀት በዓል በሜዳና በወንዝ ዳር እንዲከበር ተወስኗል፡፡ በወቅቱ የበዓሉ አከባበር እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በአጥቢያቸው በሚገኝ ሜዳና ወንዝ ተሰባስበው ለየብቻቸው ያከብሩ ነበር። በዚህ ዘመን ማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ በሥጋ በምድር የነበረበት ዘመን በመሆኑ ቅዱሱ የበዓሉን አከባበር መንፈሳዊ ሥርዓት እና ዝማሬ ከንጉሡ አፄ ገብረመስቀል ጋር በመሆን ወስኗል፡፡

2.በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት
-----------------------------------------
ከዛሬ 874 ዓመታት በፊት ከአንድ ዐለት መቅደሶችን በመፈልፈል የሚታወቀው ንጉሡ ቅዱስ ላሊበላ (ቅዱሱ አርኪቴክት) ዘመነ መንግሥት (በ1178 ዓ.ም.) በዓለ ጥምቀት በየአድባራቱ ለየብቻ በየአካባቢው በተናጠል መከበሩ ቀርቶ በአንድ ላይ ተሰባስበው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ጥር 11 ቀን ወርደው እንዲያከብሩ እና እለቱን ወደማደሪያ መቅደሳቸው እንዲመለሱ ሥርዓት ተሠርቷል፡፡ በዚህ ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅደስ የኖሩበት ዘመን ስለነበር ቅዱስ ላሊበላን የበዓለ ጥምቀት አከባበሩን ለመወሰን በምክር እና በጸሎት ረድተዋቸዋል፡፡

3.በአፄ ይኵኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት
----------------------------------------------
ከዛሬ 769 ዓመታ በፊት ደግሞ በአፄ ይኵኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (በ1245) በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ቀን ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸው ቀርቶ በዋዜማው ጥር 10 ቀን (በከተራ) ወደ ጥምቀተ ባሕር በመውረድ እንዲያድሩ እና በነጋታው ወደ ማደሪያቸው እንዲመለሱ ተወስኗል፡፡ የዚህ ሃሳብ አመንጪ የሆኑትም በዘመኑ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡

4.በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት
--------------------------------------------
በመንፈሳዊነታቸውንና በደራሲነታቸው የሚታወቁት አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከዛሬ 588 ዓመታት በፊት ታቦታት ወደ ወንዝ ወርደው ሀገርን በኪደተ እግር (በእግር በመኼድ) እንዲባርኩ፣ በኼዱበት መንገድ እንዳይመለሱ ሥርዐት ሠርተዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ “ታቦት እና ሙሽራ በኼደበት መንገድ አይመለስም” የሚባል አነጋገር አለን።

5.በአፄ ናዖድ ዘመነ መንግሥት
----------------------------------
ከዛሬ 528 ዓመታት በፊት በአፄ ናዖድ ዘመን (1486 ዓ.ም.) ምእመናን ከየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚወጡትን ታቦታት አጅበው ወደ ጥምቀተ ባሕሩ በመውረድ እያከበሩ እንዲያድሩ እና በነጋታውም አጅበው እንዲመለሱ ዐውጀዋል። በዚህም አዋጅ መሠረት በዓሉ ይበልጥ ህዝባዊ ሆኗል፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ’’ እንደሚባለው ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው በዓሉን ይበልጥ ማድመቅ ጀምረዋል፡፡

6.በሀገር አቀፍ ደረጃ የታወቁ ምጥማቃት
----------------------------------------------
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በዓለ ጥምቀት በተለየ ደምቆ የሚከበርባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌም በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን “ማይ ሹም”፣ በላስታ የላሊበላ እራሱ ለዚህ ተግባር ሰርቶት በነበረው የዮርዳኖስ ወንዝ ፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ”፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን (ጃንሜዳን) ወዘተ እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ በዓለ ጥምቀት እየተከበረባቸው ይገኛሉ፡፡

7.ጥምቀት የማይዳሰስ የዓለማችን ቅርስ
-----------------------------------------------
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ታህሳስ 01 ቀን 2012 ዐ.ም. በኮሎምቢያ - ቦጎታ በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ እያካሄደ በነበረው ስብሰባ የጥምቀት ክብረ በዓል አከባበርን በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ (Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity) አድርጎ መዝግቦታል። ለምዝገባ ያበቁት ዋና ዋና ነጥቦች ሲዘረዝር እንዲህ ይለዋል፡፡
‹‹የበዓለ ጥቀት አከባበር ምንም እንኳን መንፈሳዊ ሥርዓት ቢሆንም ማኅበራዊ እሴትን በመላበሱ ለኢትዮጵያውን ማኅበራዊ ትስስር በማጠንከር የሀገሪቱ ሰላም ለማጽናት አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ በዓሉ አንድነትን እና መከባበር ሥር እንዲሰድድ አግዟል፤ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ልዩ ልዩ ነገዶች በመገናዘብ አብረው እንዲኖሩ ከማስቻሉም በላይ የማንነት ስሜትን እና ማኅበረሰባዊነትን አዳብሯል››.
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5


3ኛ. አውግስታ ደብረ ጽዮን ማርያም
4ኛ. ጻድቃኔ ማርያም
5ኛ. ፈለገ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት
6ኛ. ወይራ ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና ዕጨጌ ዮሐንስ
#፴፩ኛ) #ወረዳ_4_ #አየር_ጤና_ኪዳነ_ምሕረት_ቤተ_ክርስቲያን_አጠገብ
1ኛ. አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. ጀሞ ፈለገ ኮሬብ ቅድስት ሥላሴና ቅድስት ማርያም
3ኛ. ዓለም ባንክ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል
#፴፪ኛ) #ወረዳ_1_ #በቴል_አጠገብ_(ኳስ ሜዳ)
1ኛ. ቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል
#፴፫ኛ) #በላፍቶ_ክፍለ_ከተማ_ወረዳ_4 #ገብርኤል_ጠበል
1ኛ. ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ
#፴፬ኛ) #ወረዳ_2_ #ሮል_ሳሙና_ፋብሪካ_ፊት_ለፊት
1ኛ. ረጲ ደብረ ጎልጎታ መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ካራ ቆሬ ቅዱስ ሩፋኤል
3ኛ. ደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል
4ኛ. ግራር ደ/አ/ቅድስት አርሴማ
5ኛ. ወይብላ ደብረ ጽዮን ማርያም

፠ ፠ ፠ #ነፋስ_ስልክ_ላፍቶ_ክፍለ_ከተማ_ (13ት ጥምቀተ ባሕር)
#፴፭ኛ) #ደብረ_ኢያሪኮ_መድኀኔ_ዓለም_ቤተ_ክርስቲያን_አጠገብ
1ኛ. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ፉሪ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ማርያም
3ኛ. ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለም
4ኛ. ደብረ ወርቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
5ኛ. ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ
6ኛ. ፉሪ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል
#፴፮ኛ) #ጎፋ_ሠፈር
1ኛ. ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ቤዛ ብዙኃን ኪዳነ ምሕረት
3ኛ. ቄራ መብራት ኀይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስና ዮሐንስ መጥምቅ
#፴፯ኛ) #ጀሞ_መድኀኔ_ዓለም
1ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል
#፴፰ኛ) #ቻይና_ካምፕ
1ኛ. ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት ማርያም
#፴፱ኛ) #ጀሞ_ቊጥር_3_አደባባይ
1ኛ. ጀሞ ቊጥር 3 ቅዱስ ገብርኤል
#፵ኛ) #ቶታል_አደባባይ
1ኛ. ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. መካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፵፩ኛ) #መካኒሳ_ኮንዶሚንየም
1ኛ. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል
#፵፪ኛ) #ዮሴፍ_አካባቢ
1ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2ኛ. ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ
3ኛ. ብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም
4ኛ. አዲስ አምባ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
5ኛ. ሐመረ ወርቅ ቅድስት ማርያም
#፵፫ኛ) #ብሥራተ_ወንጌል
1ኛ. ደብረ ቢ/ያ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፵፬ኛ) #ደብረ_ዕንቊ_ቅዱስ_ገብርኤል
1ኛ. ደብረ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል
#፵፭ኛ) #ፉሪ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም
1ኛ. ፉሪ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
#፵፮ኛ) #ፉሪ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ዑር(ራ)ኤል
1ኛ. ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል
#፵፯ኛ) #ቡልቡላ_ ኤምባሲ_አጠገብ
1ኛ. ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ለቡ በዓለ ወልድ
፠ ፠ ፠ #አቃቂ_ቃሊቲ_ክፍለ_ከተማ_ (9ኝ ጥምቀተ ባሕር)
#፵፰ኛ) #ወረዳ_1 #አቃቂ_በሰቃ_ወንዝ
1ኛ. ቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. ጃቲ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
4ኛ. ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም
5ኛ. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኀኔ ዓለም
6ኛ. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል
7ኛ. ፈንታ ደ/ጽ/ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ
8ኛ. ቀርሣ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያም
#፵፱ኛ) #ወረዳ_5 #ከቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል
#፶ኛ) #ወረዳ_4 #ሰርቲ_መድኀኔ_ዓለም_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ሰርቲ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም
#፶፩ኛ) #ወረዳ_9 #ገብረ_መንፈስ ቅዱስ_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ኮዬ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፶፪ኛ) #ቃሊቲ_አካባቢ
1ኛ. ሠፈረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል
#፶፫ኛ) #ወረዳ_9 #ሥላሴ_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ቂሊንጦ ቅድስት ሥላሴ
#፶፬ኛ) #ወረዳ_10 #ገላን_ጉራራ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ገላን ጉራራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል
#፶፭ኛ) #ወረዳ_11 #ገላን_ኢዶሮ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ገላን ኢዶሮ ቅዱስ ገብርኤል
#፶፮ኛ) #መጠሊ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. መጠሊ ደ/አ/ቅዱስ ገብርኤል
፠ ፠ ፠ #ቦሌ_ክፍለ_ከተማ_ (19ኝ ጥምቀተ ባሕር)
#፶፯ኛ) #ጉምሩክ_ወረዳ_3
1ኛ. ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኀኔ ዓለም ወመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ
#፶፰ኛ) #ወረዳ_23 #አየር_መንገድ
1ኛ. ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ክርስቶስ ሰምራ
#፶፱ኛ) #ወረዳ_06 #መገናኛ
1ኛ. መገናኛ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
#፷ኛ) #ወረዳ_02 #ሩዋንዳ_አካባቢ
1ኛ. ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ቦሌ አየር ማረፊያ መንበረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፷፩ኛ) #ወረዳ_13 #አድዋ_ፓርክ
1ኛ. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
2ኛ. ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል
#፷፪ኛ) #ወረዳ_9 #ሰሚት_አደባባይ
1ኛ. ቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ቦሌ ሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. ቦሌ ሰሚት ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
4ኛ. በሻሌ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም
#፷፫ኛ) #ወረዳ_12 #ቡልቡላ
1ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ወቅዱ አማኑኤል
3ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም
#፷፬ኛ) #ወረዳ_9 #ጎሮ_ሰፈር_ባሕረ_ጥምቀት
1ኛ. ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብኤል
2ኛ. ኤረር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ
3ኛ. ኤረር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል
#፷፭ኛ) #ወረዳ_13 #አያት_አደባባይ_ #4_ኪሎ_ሰፈር
1ኛ. አያት መ/ሕ/መድኀኔ ዓለም
#፷፮ኛ) #ወረዳ_13 #መሪ_አያት
1ኛ. መሪ ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2ኛ. አያት ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
3ኛ. መሪ ቅዱስ ፋኑኤል
4ኛ. መሪ ቅድስት ሥላሴ
#፷፯ኛ) #በሻሌ
1ኛ. ቦሌ በሻሌ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ እስጢፋኖስ
2ኛ. የቃጥላ ደብረ ፀሐይ ቅድሰት ማርያም
#፷፰ኛ) #ወቄ_አካባቢ
1ኛ. ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤል
#፷፱ኛ) #አያት_ጨፌ
1ኛ. አያት ጨፌ ደብረ ኢያሪኮ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
#፸ኛ) #ወረዳ_11 #ለሚ_ኮንዶሚኒየም
1ኛ. ቦሌ ሰሚት ቅዱስ ሩፋኤልና ኤዎስጣቴዎስ
#፸፩ኛ) #ወረዳ_11 #አራብሳ
1ኛ. አራብሳ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ዋሻው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፸፪ኛ) #ለሚ
1ኛ. ቦሌ ለሚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. ቦሌ ለሚ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፸፫ኛ) #አያት_ኮንዶሚኒየም
1ኛ. አያት ጨፌ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. አያት ፈለገ ሕይወት ቅዱስ ዮሐንስ
#፸፬ኛ) #ቦሌ_ቡኒ
1ኛ. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
#፸፮ኛ) #ሪፈንቲ
1ኛ. ሪፈንቲ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ቦሌ ሰሚት መካነ ሕያዋን ዋሻው ቅዱስ ገብርኤል

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5


(‹‹የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትን ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡›› ኢያሱ ፫፥፫)

#ጥምቀትን_በአዲስ_አበባ__በየትኛው_ጥምቀተ_ባሕር_ያከብራሉ_፤
#በአዲስ_አበባ_በ10ሩም #ክፍለ_ከተሞች_የሚገኙ
#76ት #የጥምቀተ_ባሕር_ቦታዎችና_ወደ_ጥምቀተ_ባሕሩ_የሚወርዱትን_179 #ገዳማትና_አድባራት_እነሆ_ጽፈንላችኋል፡፡
(እኛ በአ.አ. ከሚገኙ 76ት ጥምቀት ባሕር መካከል፤ ብዙ ታቦታት የሚወርዱበትን የጃንሜዳን ፎቶ ለጥፈንላችኋል፤ እናንተም በየአካባቢያችሁ ያሉትን በ‹ኮሜንት› መጻፊያ ላይ ለጥፉልን፡፡)
      #share
፠ ፠ ፠ #በአራዳና_ጉለሌ_ክፍለ_ከተማ_ (7ት ጥምቀተ ባሕር)
#፩ኛ) #በጃንሆይ_ሜዳ_ (በጃንሜዳ)፤ /በአዲስ አበባ ትልቁና የ12 አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት የሚያድሩበት)
1ኛ. መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤
2ኛ. ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፤
3ኛ. መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤
4ኛ. መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ.፤
5ኛ. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.፤ (የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ታቦተ ወደ ጥምቀተ ባሕር ስለማይወጣ ሕዝቡና ሰ/ት/ቤቱ አብሮ ነው የሚያከብረው)
6ኛ. መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም
7ኛ. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.፤
8ኛ. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (አብሮም ቅዱስ ሚካኤል ይወርዳል)፤
9ኛ. ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ.ክ.፤
10ኛ. ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ.ክ.፤
11ኛ. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤
12ኛ.  ፈለገ ሰላም ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡተ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ (ቀበና 18 ፓርክ አጠገብ)፡፡
#፪ኛ) #እንጦጦ_ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ
1ኛ. እንጦጦ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ ቤ.ክ.
2ኛ. እንጦጦ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም
#፫ኛ) #ሽሮ_ሜዳ_ወረዳ_01 ፥ #ቀበሌ_02_
1ኛ. ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ
#፬ኛ) #አዲሱ_ገበያ_
1ኛ. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
2ኛ. መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ተክለሃይማኖት
3ኛ. ድል በር መድኃኔዓለም
#፭ኛ) #ወረዳ_3ና_4 (19 ቀበሌ)
1ኛ. መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም
#፮ኛ) #ሸጎሌ_መንገድ_
1ኛ. ጉለሌ(ሸጎሌ) ቅድስት ኪዳነ ምሕረት

#፯ኛ) #ወረዳ_7_ቀበሌ_15(ቤልኤር፤ ኳስ ሜዳ)
1ኛ. ቀበና ምሥራቀ ፀሐይ መድኀኔ ዓለም

፠ ፠ ፠ #በየካ_ክፍለ_ከተማ_ (14ት ጥምቀተ ባሕር)
#፰ኛ) #ወረዳ_8(22 አካባቢ፤ ባልደራስ አጠገብ)
1ኛ. የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል
3ኛ. ቀበና ቤዛዊተ ዓለም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
#፱ኛ) #ወንድይራድ_ትምህርት_ቤት_አካባቢ_(ኮተቤ)
1ኛ. ኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ኮተቤ (ኋላ ሲ.ኤም.ሲ.) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል
3ኛ. መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
4ኛ. ሲ.ኤም.ሲ. አቡነ ተክለ ሃይማኖት
5ኛ. ደብረ አራራት ቅዱስ አማኑኤል
6ኛ. ሀገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ
7ኛ. ኮተቤ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፲ኛ) #ዋሻ_ተክለ_ሃይማኖት_ጠበል_ቦታ
1ኛ. ዋሻ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. አንቆርጫ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል
#፲፩ኛ) #በግ_ተራ
1ኛ. ኮተቤ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
#፲፪ኛ) #ላምበረት_ቤተ_ክርስቲያኑ_አካባቢ
1ኛ. ላምበረት ደብረ ፀሐይ አቡነ አረጋዊ
#፲፫ኛ) #ጉራራ_አካባቢ
1ኛ. ጉራራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፲፬ኛ) #ወረዳ_10 #ከጉራራ_ከፍ_ብሎ_ፖሊስ_ሴንተር_አጠገብ
1ኛ. ደብረ መድሐኒት ዳንሴ መድኀኔዓለም
2ኛ. ምሥራቀ ፀሐይ ዳንሴ ቅዱስ ሚካኤል
#፲፬ኛ) #ሎቄ_ቤተ_ክርስቲያን_አካባቢ
1ኛ. ሎቄ መ.ጸ. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፲፭ኛ) #ኬንያ_ኤምባሲ_ጀርባ_(በግ ተራ)
1ኛ. ደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም
#፲፮ኛ) #መሪ_አደባባይ
1ኛ. መሪ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ
2ኛ. መሪ ደብረ ታቦር ቅዱስ ፋኑኤል
#፲፯ኛ) #አባዶና_ካራ_አሎ_አርሴማ_ጠበል_አካባቢ_(ገበያው መሐል)
1ኛ. ካራ አሎ ደብረ ቀርሜሎስ መድኀኔ ዓለምና አቡነ ገሪማ
2ኛ. ካራ አሎ ቅድስት ሥላሴ
3ኛ. አባዶ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
4ኛ. ኮተቤ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፲፰ኛ) #አባዶ_አካባቢ
1ኛ. አባዶ ገ/አ/ ቅዱስ ሚካኤል
#፲፱ኛ) #አያት_አካባቢ
1ኛ. ጣፎ መ/ብ/ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. አያት ደ/ክ ቅድስት ማርያም
#፳ኛ) #አባዶ_ኮንዶሚንየም
1ኛ. አባዶ ጽርሐ አርያም ቅድስት ማርያም
2ኛ) ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሩፋኤል
3ኛ) ደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ
4ኛ) ደብረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም
5ኛ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
6ኛ. ቅዱስ ሚካኤልና ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
7ኛ. ኢያሪኮ ቅዱስ ገብርኤል
፠ ፠ ፠ #ልደታ_አዲስ_ከተማና_ቂርቆስ_ክፍላተ_ከተማ_ (5ት ጥምቀተ ባሕር)
#፳፩ኛ) #ቂርቆስ_አካባቢ
1ኛ. ደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ
#፳፪ኛ) #ኦሎምፒያ_ቦሌ_ማተሚያ_ቤት_አካባቢ
1ኛ. ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ
2ኛ. ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ
#፳፫ኛ) #ልደታ_ክፍለ_ከተማ_ሜትሮሎጂ_ጀርባ
1ኛ. ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. ጎላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ቅዱስ ሚካኤል
#፳፬ኛ) #ሳር_ቤት_ኮንዶሚንየም
1ኛ. ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም
#፳፭ኛ) #ቄራ_አካባቢ
1ኛ. አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
፠ ፠ ፠ #ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ_(9ኝ ጥምቀተ ባሕር)
#፳፮ኛ) #መድኀኔ_ዓለም_ከፍተኛ_መሠናዶ_ትምህርት_ቤት_(ራስ ኀይሉ ሜዳ)
1ኛ. መርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል
2ኛ. ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል
3ኛ. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል
4ኛ. ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
5ኛ. ጠሮ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ
#፳፯ኛ) #ሳንሱሲ_መናፈሻ_አጠገብ
1ኛ. አስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. አስኮ ደብረ መንክራት ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4ኛ. ፍኖተ ሎዛ ብርጭቆ ማርያም
#፳፰ኛ) #ወረዳ_15_(አርሴማ ጠበል /አወልያ ትምህርት ቤት ጋር/)
1ኛ. ቃሎ ተራራ አቡነ ሀብተ ማርያም
#፳፱ኛ) #ገዳመ_ኢየሱስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅጽር_ግቢ_ውስጥ
1ኛ. ደብረ ቀራንዮ መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ
3ኛ. ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ
4ኛ. ወይብላ ደብረ ጽዮን ማርያም
5ኛ. ፊሊዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
6ኛ. መርካቶ ደብረ ገሊላ አማኑኤል
7ኛ. ገዳመ ኢየሱስ
#፴ኛ) #ወረዳ_5_ #ጻድቃኔ_አካባቢ_ታቦት_ማደርያ
1ኛ. ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ
2ኛ. ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ


ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ✝
                         
Size 48.2MB
Length 1:03:34

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5









20 last posts shown.