በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ዐብይ ጾም-------------------------------
@Ethiopian_Orthodox-------------------------------
ጾም ማለት "ተወ"፣ "ታቀበ" ፣"ታረመ" ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። ፍቺውም ምግብ መተው ፤መከልከል፤ መጠበቅ ማለት ነው።
ጾም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል፤ መወ'ሰን ማለት ነው። ወይም ሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት ነው። ጾም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ።
✳️ ጾም በብሉይ ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው።
ነብያት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር። (ዘፀ 30÷34-28)
✳️ በኃጢአት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። (ዮሐ 2÷7-10)
✳️ በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ ሥጋዌው የሥራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።
✳️ ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግራል።(ማቴ 17÷21)
✳️ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙት ሐዋርያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው ትዕዛዝ የሚቀበሉበት በጾም እና በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር።(ሐዋ 13÷2)
✳️ ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነበር። (ሐዋ 13÷3)
ጾምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ጾም ማለት ጥሉላት ማባልዕት ፈፅሞ መተው ሰውነትንም ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ "ይቅር በለኝ" በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበረከክ ምሕረት ለአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
ፆም ነፍስን ቁስልን የምትፈውስ፣ ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ የወንጌል ስራ መጀመሪያ ፣ የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል የንፅህና ጌጣቸው ፤የንፅህና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፤ የእንባ መናኛ መፍለቂያ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት።
ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገሥታት፣ ካህናት በፆምና በጸሎት ፅመድ ሆነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልም እንዲጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን ፈፅሞላቸዋል።
በሀዲስ ኪዳን ጾም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው።// ማቴ 5÷6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ሰጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ጾም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው። ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች ~~~ ስለዚህም የሚፆም ሰው በፈቃደ ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል።
በእምነት ሆኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን ምስጢር ለማየት ከዓለማዊነት ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል። በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል። ከዓለም አይደለምና //ዮሐ 15÷19//
🔰ዐብይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው።
አብይ ጾም የተለያዩ ስሞች አሉት:
፩.
ዐብይ ጾም: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐብይ እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ //መዝ 47÷1 መዝ 146÷5//
ዐብይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆን ለማሳወቅ ነው። ይህ ጾም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መጾሙና ከሌሎች አፅዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የጾመው ጾምም በመሆኑ ነው።
፪.
ሁዳዴ ጾም: ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው።፣ /አሞ 7÷1 //
፫.
በዓተ ጾም : ፆም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓል ማለት ነው
፬.
ጾመ አርቦ: ጌታችነ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉ 40// አርባ ቀን ስለሆነ ነው //ማቴ 4÷1
፭.
ጾመ ኢየሱስ : ጾሞ ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፣
፮.
ጾመ ሙሴ : ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ "ዕዝል ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት" እያለ በጾመ ድጓ ስለ ዘመረ ነው።
🌿ዐብይ ጾም ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው። //ማቴ 4÷1
ምእመናንም ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል።
🌿ዐብይ ጾም
ስምንት ሳምንታት //55 ቀኖች // አሉት። 7//ሰባት ቅዳሜ 8//ስምንት እሁድ ይገኛሉ። አስራ አምስት ቀን 55//ማለት ነው። ከጥሉላት እንጂ ከእህል ወኃ ስለማይጾሙ የጾሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል።
የዐብይ ጾም ሶስት ክፍሎች ፩. ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል)፦ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ያረሰ ያለው 7 ቀን ነው።
፪. የጌታ ጾም፦ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው አርባ ቀን ነው።
፫. ሕማማት፦ ይህ ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጡበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው።
ይህም ፯+፵+፰=፶፭(7+40+8=55)ቀን ይሆናል።
የዐብይ ጾም ሳምንታት 8 ሲሆኑ:
፩. ዘወረደ
፪. ቅድስት
፫. ምኲራብ
፬. መጻጉዕ
፭. ደብረ ዘይት
፮. ገብርሔር
፯. ኒቆዲሞስ እና
፰. ሆሣዕና ናቸው።
ጾሙን ጾመን ድኅነት የምናገኝበት የበረከት እንዲሁም ቤተክርሰቲያናችንንና ሐገራችንን ከመዓት የምንታደግበት ያድርግልን! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox@Ethiopian_Orthodox