Forward from: እውነታ TUBE
የዋይት ሀውስ ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት ያወጣውን መግለጫ ኢትዮጵያውያን እየተቃወሙ ነው
የዋይት ሀውስ ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ኢትዮጵያውያን እየተቃወሙ ነው፡፡
በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዋይት ሀውስ ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ በመቃወም ላይ ይገኛሉ።
የዋይት ሀውስ ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት በትናንትናው እለት በትዊተር ገጹ፥ “257 ሚሊየን የምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች የኢትዮጵያ ጠንካራ አመራርን ለማየት ይሻሉ፤ ይህም ማለት ፍትሃዊ ስምምነትን የሚጠይቅ ነው፤ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያሉ የቴክኒክ ጉዳዮች መፍትሄ አግኝተዋል፤ አሁን ደግሞ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት ላይ የሚደረስበት ጊዜ ሊሆን ይገባል” ፅሁፍ አውጥቷል።
መልእክቱም ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙርያ ስምምነት ላይ ሳይደርስ ሙሌት እንዳትጀምር የሚል እንድምታ ያለው ሆኖም ተገኝቷል።
ታዲያ ምክር ቤቱ በትናንትናው እለት የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ ሲሆን፥ ኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞዋቸውንም በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያውያኑ የዋይት ሀውስ ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ የሀገርን ሉዓላዊነት የሚጥስ መሆኑን በመግለፅ፤ “ምን ማድረግ እንዳለብን ማንም አይነግረንም፤ በድንበራችን ውስጥ ያለን ግድብ ውሃ ለመሙላት ማንንም አንጠይቅም” ብለዋል በሰጡት አስተያየት ።
100 በመቶ በኢትዮጵያውያን ወጪ የሚገነባን ግድብ ውሃ ሙሉ አትሙሉ ማለት የሚችል አካል የለም ያሉት ኢትዮጵያውያኑ፤ የግድቡ የመጀመሪያ ውሃ የመያዝ ሂደት ስምምነት ላይ ቢደረስም ባይደረሰም ግድባችን ይሞላል የሚል አስተያየት አስፍረዋል፤ በራሳችን ግድብ ለማንም ፈቃጅና ከልካይ ፍላጐት የምንተወው አይደለም በማለት።
ኢትዮጵያ ውሃውን በፍትሃዊነት ለመጠቀም ሲባል ከግብፅ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ በጣም ረጅም ርቀት መጓዛንም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በፍትሃዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ ይህን ያክል ርቀት የተጓዘችው በጋራ ጥቅም ስለምታምን መሆኑንም በመግለጽ፤ “ግብፅ በኢትዮጵያ በኩል የቀረበላትን ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ መፍትሄን እድንትቀበል ምከሯት” ያሉም አሉ።
ግብፅ በእረግጥ የቸገራት ውሃ ሳይሆን የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም መጉዳት መሆኑን የጠቀሱ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ በግብፅ ያለውን እምቅ የከርሰ ምድር ውሃ፣ አባካኝ የውሃ አጠቃቀም ባህል እና ሌሎች ማስረጃዎችን በማጣቀስ የሀገሪቱን ሴራ ያጋለጡም ኢትዮጵያውያን አሉ።
(Ebc)
ሰኔ 11/2012 ዓ.ም
--------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ