Forward from: ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን(You tube-Misiker media ምስክር ሚዲያ)
ዜ ማ ቃ ል LYRICS
@muzicalword
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እንዴት_ይህን_የመሰለ_ታሪካዊ_ሙዚቃ_ተጻፈ
(የጂጂ የቀድሞ ማኔጀርና ጓደኛዋ እንዲሁም ቤዝ ጊታሪስት
ቶማሥ ጎበና Thomas Gobena (Tommy T) ጋር
ካደረግኩት ቆይታ የቆነጠርኩት ነው።)
እኔ፦ "ቶሚ፤ አድዋ ይገርመኛል። ሲሰራ ታስታውሳለህ??"
ቶማሥ፦ "ታስታውሳለህ?? እንዲያውም ይገርመኛል፤
ልንገርህ። ፕሮፌሠር ሀይሌ ገሪማ አድዋ የተሠኘውን
ፊልማቸውን በአሜሪካ እንደነገ ሊያስመርቁ እንደዛሬ የኔን ባንድ
ተከራዩ። Instrument ብቻ ነበር ልንጫወት የታሰበው።
ከዚያ ፕሮፌሠር ሀይሌ መጡና "እስቲ፤ የፊልሙን ምርቃት
የሚከፍት ዘፋኝም ፈልግ። ብቻ ሴት ኢትዮጵያዊት ትሁን" አሉኝ።
እሺ ብዬ ማንን እንደምጋብዝ እያሰብኩ ቤቴ ሄድኩና ከጓደኞቼ
ጋር ልምምድ ጀመርን።
ማታ 2 ሰዓት ተኩል ገደማ ጂጂ ሁለት ሺፍት ሥራዋን ጨርሳ
ወደ ቤቷ ልትሄድ ስትል ጎራ አለች።
"አንቺ፤ ፕሮፌሠር ሀይሌ ዘፋኝ ይፈልጋሉ። ለምን አንቺ
አትሠሪም?!" አልኳት።
"መጣሁ!" ብላ እየሮጠች ወጣች። 4 ሠዓት ሲል መጣች።
"አዲስ ሙዚቃ ሠርቻለሁ። እናጥናው።" አለች።
"አንቺ ልጅ አብደሻል እንዴ?! አይሆንም!" አልኳት።
እኔ፦ ለምን???!
ቶማሥ፦ እንዴ ፕሮፌሠር ሀይሌ እኮ ናቸው። በጣም ነው
የምንፈራቸው። የማይሆን ሥራ ይዘን ገብተን አበላሽተን
ቢገሉንስ??
ከዚያ "ዝምብለሽ "እማማ ኢትዮጵያ" የሚለውን ዝፈኝ እንጂ
አይሆንም" አልኳት። ተስማማች። በማግስቱ ጠዋት መድረክ
ላይ ወጥተን ልትዘፍን ስትል በምልክት "ፀጥ በሉ!" አለችን።
በጣም ብዙ ህዝብ ነበር። ትላልቅ እንግዶች ከፊት ነበሩ። እኛ
መጫወት አቆምን።
"አድዋ"ን ያለ ሙዚቃ በድምጿ ብቻ መዝፈን ጀመረች።
"የሠው ልጅ ክቡር..........." ስትል ክው አልኩ።
ሰምተነው አናውቅም። በ 1 ሰዓት ተኩል የተደረሠ ዘፈን ነው።
ከዚያ ከሀይሌ ጋር የተቀመጡ ነጭ ምሁራን እንባቸውን
ያወርዱታል። ቋንቋው አይገባቸውም። ጂጂ ራሷ ደንግጣ
እየዘፈነች ወደኔ ዞራ "ምንድነው?!" የሚል አስተያየት አየችኝ።
በምልክት "ቀጥይ!" አልኳት። ስትጨርስ ቤቱ በእግሩ ቆመ።
ፕሮፌሠር መጡና "እቺን ጉደኛ መተዋወቅ እፈልጋለሁ" ብለው
ተዋወቋት። ያልመጣ ሠው አልነበረም። ከነሱ መሀል የ 7
ግራሚ አሸናፊዋና የ Bob Marley ልጅ ሚስት Lauren Hill
ነበረች። እሷም ከትላልቅ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሮች ጋር አገናኘቻት።
ከአመታት በኋላ አልበም ሆኖ ወጣ። ይሄ ነው ታሪኩ።"
ለሌሎች ማስነበቦን ያስታውሱ
👇more n more👇
🦁 @muzicalword 🦁
🦁 @muzicalword 🦁
🦁 @muzicalword 🦁
@muzicalword
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እንዴት_ይህን_የመሰለ_ታሪካዊ_ሙዚቃ_ተጻፈ
(የጂጂ የቀድሞ ማኔጀርና ጓደኛዋ እንዲሁም ቤዝ ጊታሪስት
ቶማሥ ጎበና Thomas Gobena (Tommy T) ጋር
ካደረግኩት ቆይታ የቆነጠርኩት ነው።)
እኔ፦ "ቶሚ፤ አድዋ ይገርመኛል። ሲሰራ ታስታውሳለህ??"
ቶማሥ፦ "ታስታውሳለህ?? እንዲያውም ይገርመኛል፤
ልንገርህ። ፕሮፌሠር ሀይሌ ገሪማ አድዋ የተሠኘውን
ፊልማቸውን በአሜሪካ እንደነገ ሊያስመርቁ እንደዛሬ የኔን ባንድ
ተከራዩ። Instrument ብቻ ነበር ልንጫወት የታሰበው።
ከዚያ ፕሮፌሠር ሀይሌ መጡና "እስቲ፤ የፊልሙን ምርቃት
የሚከፍት ዘፋኝም ፈልግ። ብቻ ሴት ኢትዮጵያዊት ትሁን" አሉኝ።
እሺ ብዬ ማንን እንደምጋብዝ እያሰብኩ ቤቴ ሄድኩና ከጓደኞቼ
ጋር ልምምድ ጀመርን።
ማታ 2 ሰዓት ተኩል ገደማ ጂጂ ሁለት ሺፍት ሥራዋን ጨርሳ
ወደ ቤቷ ልትሄድ ስትል ጎራ አለች።
"አንቺ፤ ፕሮፌሠር ሀይሌ ዘፋኝ ይፈልጋሉ። ለምን አንቺ
አትሠሪም?!" አልኳት።
"መጣሁ!" ብላ እየሮጠች ወጣች። 4 ሠዓት ሲል መጣች።
"አዲስ ሙዚቃ ሠርቻለሁ። እናጥናው።" አለች።
"አንቺ ልጅ አብደሻል እንዴ?! አይሆንም!" አልኳት።
እኔ፦ ለምን???!
ቶማሥ፦ እንዴ ፕሮፌሠር ሀይሌ እኮ ናቸው። በጣም ነው
የምንፈራቸው። የማይሆን ሥራ ይዘን ገብተን አበላሽተን
ቢገሉንስ??
ከዚያ "ዝምብለሽ "እማማ ኢትዮጵያ" የሚለውን ዝፈኝ እንጂ
አይሆንም" አልኳት። ተስማማች። በማግስቱ ጠዋት መድረክ
ላይ ወጥተን ልትዘፍን ስትል በምልክት "ፀጥ በሉ!" አለችን።
በጣም ብዙ ህዝብ ነበር። ትላልቅ እንግዶች ከፊት ነበሩ። እኛ
መጫወት አቆምን።
"አድዋ"ን ያለ ሙዚቃ በድምጿ ብቻ መዝፈን ጀመረች።
"የሠው ልጅ ክቡር..........." ስትል ክው አልኩ።
ሰምተነው አናውቅም። በ 1 ሰዓት ተኩል የተደረሠ ዘፈን ነው።
ከዚያ ከሀይሌ ጋር የተቀመጡ ነጭ ምሁራን እንባቸውን
ያወርዱታል። ቋንቋው አይገባቸውም። ጂጂ ራሷ ደንግጣ
እየዘፈነች ወደኔ ዞራ "ምንድነው?!" የሚል አስተያየት አየችኝ።
በምልክት "ቀጥይ!" አልኳት። ስትጨርስ ቤቱ በእግሩ ቆመ።
ፕሮፌሠር መጡና "እቺን ጉደኛ መተዋወቅ እፈልጋለሁ" ብለው
ተዋወቋት። ያልመጣ ሠው አልነበረም። ከነሱ መሀል የ 7
ግራሚ አሸናፊዋና የ Bob Marley ልጅ ሚስት Lauren Hill
ነበረች። እሷም ከትላልቅ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሮች ጋር አገናኘቻት።
ከአመታት በኋላ አልበም ሆኖ ወጣ። ይሄ ነው ታሪኩ።"
ለሌሎች ማስነበቦን ያስታውሱ
👇more n more👇
🦁 @muzicalword 🦁
🦁 @muzicalword 🦁
🦁 @muzicalword 🦁