Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት በባሏ ላይ ከባድ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!
—————
➡️ ሀሰኑል በስሪይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:-
“መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ አንድ ሰው ዘንድ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ይህን ጊዜ ከሱ መግዛቱን ተውኩት። ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ። ከዚያም ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ፣ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለርሱም እንዲህ አልኩት:- ያ ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርክበት ሁኔታ አሁን ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።
እንዲህ በማለት መለሰ:-
1⃣ ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምትመለከት፣ ብዙም ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከጊዜ በኋላ ሞተች።
2⃣ ከሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ "እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን።" ትለኛለች።
[ምንጭ:- አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል-ዒልም 5/251]
↪️ ጥያቄ ለእህቶቼ፣ ለመሆኑ እናንተ ከየትኛዋ ሴት ናችሁ ከመጀመሪያዋ ወይስ ከሁለተኛዋ???
መልሱን… ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ ቆም ብላችሁ በማሰብ ለራሳችሁ መልሱት!።
ከመጀመሪያዋ የሆናችሁ አላህን (ተባረከወተዓላ) ፈርታችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ሁለተኛዋ ተመለሱ!!
ከሁለተኛዋ የሆናችሁ ሸይጧን ድንበር እንዳያሳልፋችሁ ነፍሳችሁን ዝቅ እንድትልና ከጌታዋ ከጃይ እንድትሆን አድርጓት!። አላህ ፅናት እንዲሰጣችሁም የዘውትር ዱዓችሁ ይሁን!! ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነውና‼
ባል ሆይ! ለቤተሰብህ ሀራም አታብላ!! የሚስትህንና ልጆችህን ሰውነተ በሀራም አትገንባ!!
የትውልዱ መበላሸት አንዱ ምክንያት ሰውነት በሀራም መገንባቱ ነው!!
ሚስት ሆይ! ባልሽ ከነ ልጆችሽ ሀራም እንዳያበላሽ አደራ በይው!! በሀላሉ አምጣ እንጂ ትንሹም ይበቃል ብለሽ በትንሹም ተብቃቂ!!
ተቅዋ (አላህን መፍራት) ማለት በትንሹ መብቃቃትና ለቀጣዩ አለም መዘጋጀት ማለት ነውና!! አንገብግበሽ አንቺንም ልጆችሽንም ሀራም እንዲያበላችሁ አታድርጊው!!
✍ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa