Forward from: GOFERE
ጎፈሬ 🤝 የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን
የአምስት ዓመታት ስትራቴጂካዊ ስምምነት በመፈፀም የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል አጋር የሆነው ጎፈሬ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ያለውን እግርኳሳዊ መነቃቃት ለመደገፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል።
እግርኳስ የገባቸው አመራሮች የሚገኙበት ፌዴሬሽኑ የከፍተኛ ዲቪዚዮን ውድድራቸውን እጅግ በደማቅ ሁኔታ እያገባደዱ ሲሆን ለአሸናፊዎች እና ኮከቦች የሚበረከቱ ሽልማቶችን ተቋማችን ጎፈሬ በዛሬው ዕለት ስፍራው ድረስ በመጓዝ አስረክቧል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮሚሽነር ዓለሙ መገራ ዋንጫዎቹን እና ሜዳሊያዎቹን ከጎፈሬ መስራች እና ባለቤት አቶ ሳሙኤል መኮንን ከተረከቡ በኋላ የውድድር ዓመቱ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ አብሯቸው ለነበረው ጎፈሬ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በ16 ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የነበረው የ2017 ዓ.ም የድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ውድድር በቀጣዩ ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 23 በደማቅ ሥነ-ስርዓት እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
@goferesportswear