Forward from: AI-IKHILAS
“ሽርክ” የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮ
وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال : سمعت رسول الله ﷺ يقول : قال الله تعالى : "أنا أغنى الشركاء عن الشرك ، من عمل عملا أشرك فيه معي غيري تركته وشركه" رواه مسلم: ٢٩٨٥
አቡሁረይራ (ረዲየሏሁዓንሁ) ከረሱል ﷺ ሰምተው ባስተላለፉት “ሐዲስ አል'ቁድስ” አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“ከተጋሪዎች ሁሉ መጋራት የተብቃቃሁ ነኝ ፤ ከእኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እርሱን ከነማጋራቱ እተወዋለሁ፡፡” ሙስሊም: 2985
ይህ ሐዲስ ከዑለሞች ዘንድ “ሐዲሰ አል'ቁድስ” በመባል ይጠራል፡፡
ረሱል ﷺ አንድን ሐዲስ ወደ አላህ ካዛመዱት “ሐዲስ አል'ቁድስ” በመባል ይጠራል፡፡ ወደአላህ ካልተዛመደ ግን “ሐዲስ አን'ነበውይ” በመባል ይጠራል፡፡ (¹)
አላህ ሸሪካ የሌለው ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነው፡፡ አንድ ሰው በሚሰራው ስራ የአላህን እና የሰዎችን ውዴታ የሚሻ ከሆነ ስራው ተቀባይነት ያጣል፡፡ ግማሹን ተቀብሎ ግማሹን ይተወዋል አይባልም፡፡ ከሰዎች ውዳሴን ፈልጎ ሶደቃ ቢሶድቅ አላህ ከእርሱ አይቀበለውም፡፡ ከሰዎች ሙገሳን ፈልጎ ሶላት ቢሰግድ አላህ ከእርሱ አይቀበለውም፡፡ አላህ ከተጋሪዎች ማጋራት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡
አንድ ሰው ሶላቱን ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ “እከሌ ማሻ አላህ ይሰግዳል! ሶላትን ያበዛል!” የሚል የሰዎችን አድናቆት የሚፈልግ ከሆነ ሩኩኡን ሱጁዱን ቂያሙን መቀመጡን ሁሉ ቢያስረዝም አይኑ ከሱጁድ ቦታ ተተክሎ ቢቆይ ሶላቱን አላህ አይቀበለውም፡፡ አላህ ከዚህ ሰው ሶላት የተብቃቃ ነው፡፡
“እከሌ ለጋስና ቸር ነው፡፡ ሶደቃ ለምስኪኖች ይሶድቃል፡፡” መባልን ሽቶ ለምስኪኖች ገንዘብ የሚሰጥ እና ዘወትር የሚያበላ ቢሆን እንኳ ከአላህ ዘንድ ስራው ተቀባይነት አያገኝም፡፡
አንድ ሙኽሊስ (አምልኮቱን ለአላህ ብሎ የሚፈጽም ሰው) በዒባዳው አፈጻጸም ላይ ሪያዕ (ለይዩልኝ) ገባብኝ ብሎ ቀልቡን ቢሰማውና ከሰይጣን መሆኑን አውቆ ወዲያውኑ ቢከላከለው በአምልኮቱ ላይ የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ሰይጣን ሁልጊዜ ሙኽሊስ የሆኑ ሰዎችን ይፈታተናቸዋል፡፡ ስለዚህ ለሰይጣን ተገዥ መሆን ሳይሆን የሚያመጣውን ፈተና በጽናት መወጣት ነው የሚገባው፡፡ እርሱን በመስጋት ወይም ሪያእ (ለይዩልኝ) ይገባብኛል ብሎ በመስጋት ኢባዳውን ማቋረጥ የለበትም፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው በአቋማችን ላይ መጽናት ብቻ ነው፡፡ እኛ ከጠነከርን ሰይጣን በፍርሃት ወደኋላ ይሸሻል፡፡
﴿مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ﴾ الناس: ٤
“ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች (ሰይጣን) ክፋት (እጠበቃለሁ) በል፡፡” (ናስ: 4)
ሶላቱን ሙኽሊስ ሆኖ ጀምሮ ሪያዕ (ይዩልኝ) ገባበት ከዚያም ምንም ሳይከላከለው አምልኮቱን እስኪጨርስ በዚያው ቀጠለ ሶላቱ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ይበላሽበታል፡፡ ምክንያቱም ሶላት መጨረሻው ከተበላሸ የመጀመሪያውም ይበላሻል፡፡
በዒባዳችን ውስጥ ሪያዕን (ለይዩልኝ) ልንፈራ ይገባል፡፡ ሪያእን ፈርተን ደግሞ ዐዒባዳን ፍጹም መተው የለብንም፡፡ ሰይጣን ወደ ሰዎች ይመጣና “አትስገድ” “አትቅራ” ምክንያቱም ሪያዕ ይሆንብሃል፡፡” ይለዋል፡፡ “ሶላትህን በኹሹዕ (አላህን በመፍራት) አትስገድ ሪያዕ ይሆንብሃል፡፡” ይለዋል፡፡ ሰይጣን ይህን በማለቱ ከዒባዳ የሚዘናጉ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ የሰይጣን ተንኮል መሆኑን አውቀን በዒባዳችን ላይ መጽናት ነው የሚገባን፡፡ ለሰይጣን ቅንጣት ያክል በር መክፈት አይገባንም፡፡ ይልቁንም አላህን መፍራት መረጋጋት ለሶላታችን አንኳርና በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰይጣንን እየተከላከልን አላህ በሚፈልገው መንገድ ኢባዳችንን ከፈጸምን ምንም አይጎዳንም፡፡ ይህን ካደረግን ሰይጣን ወደኋላ ሸሽቶ የሚደበቅ አካል ነው፡፡ (²)
የሰው ልጅ በሐቂቃ ካየነው በሁለት ክስተቶች የተከበበ ነው፡-
1ኛ፡- ወደዒባዳ ከመግባቱ በፊት፤
ለምሳሌ፡- ሰይጣን ይመጣና “ሰዎች ስለሚያወድሱህ አትስራ” በማለት ከዒባዳ እንዲዳከም ያደርገዋል፡፡
2ኛ፡- ወደዒባዳው ከገባ በኋላ፤
ዒባዳ ውስጥ ከገባ በኋላ ሰይጣን እየወሰወሰ ዒባዳውን ሊያበላሽበት ይሞክራል፡፡ በዚህ ሰዓት በአላህ እየተጠበቀ ሰይጣንን መከላከልና ወደኋላ እንዲሸሽ ማድረግ ነው ያለበት፡፡
በዚህ ቦታ የሚከተለው ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
ዒባዳን ጨርሰን ካበቃን በኋላ ሰዎች ቢያወድሱንና ብንደሰት ዒባዳችን ሊበላሽ ይችላል?
መልሱ፡- ዒባዳችን ሊበላሽ አይችልም የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ዒባዳዋ በሰላማዊና በኢኽላስ ተፈጽማለች፡፡ እኛ ውዳሴን ሳንፈልግ ብንወደስ ይህ አላህ በዚህ በዱንያ ላይ ያደረገው የሙእሚኖች ፈጣን ብስራት ነው፡፡ አላህ እኛን ሳንፈልገው የውዳሴ ቦታ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ይህ ምንም ችግር የለውም፡፡ ሰዎች አወደሱት እርሱም ውዳሴያቸውን ሰማ “የመልካም ውዳሴ ቦታ ያደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው” ቢል ችግር የለውም፡፡ ዋናው ነገር ዒባዳችን ካበቃ በኋላ በፈጸምናት ዒባዳ ላይ ተነስተው ሰዎች ቢያወድሱን እና እኛ ብንደሰት በዒባዳችን ላይ የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ብቻ ግን ከውዳሴው ተነስተን በነፍሳችን በመደነቅ ሌሎች የአላህ ባሮችን ለመናቅ እና ዝቅ ለማድረግ ምክንያት ከሆነ ግን ይህ ስራችንን የሚያበላሽ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በልቦናው ምንም ትዝ ሳይለው ዒባዳውን በመልካም በመጨረሱ አላህ መልካም ስራ ገጠመኝ ብሎ አላህን አመሰገነ ተደሰተ ይህ ዒባዳውን ፍጹም አይጎዳውም፡፡
ይህን አስመልክቶ የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"من سرته حسنته وساءته سيئته فذلك مؤمن" الترمذي: ٢١٦٥، احمد: ١١٤
“መልካም ስራው ያስደሰተው መጥፎ ስራው ያስከፋው ይህ ሰው ሙእሚን ነው፡፡” ቲርሚዚይ: 2165, አህመድ: 114
አላህ ከትልቁም ከትንሹም ሽርክ ሁላችንን ይጠብቀን!
شرح رياض الصالحين لفضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله ٦/ ٣٤٠
==========================
(¹) ይህን አገላለፅ ዑለሞች የሚጠቁሙት በሁለቱ ሐዲሶች መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት እንጅ "ሐዲስ አንነበዊይ" ወህይ (ራዕይ) አይደለም ለማለት ታስቦበት አይደለም። ምክንያቱም ነብያችን ﷺ አላህ እንዳለው:–
﴿ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَى۞إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَى﴾ النجم: ٣-٤
"ከልብ ወለድም አይናገርም። እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራዕይ እንጅ ሌላ አይደለም።" አንነጅም: 3‐4
(²) ፉዶይል ብን ዒያድ (ዓለይሂረህመቱላህ) "ለሰዎች ሲባል ሥራን መተው ይህ ከሪያዕ (ከይዩልኝ) ነው።" ብለዋል። አል`አዝካር ሊነወዊይ ገፅ/19
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة