Forward from: TIKVAH-MAGAZINE
መድኃኒት የተላመደ የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ተከስቷል?
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህ ወቅት ካነሱት ጉዳዮች አንዱ መመድኃኒት የተላመዱ የወባ ትንኞችን ይመለከታል። ዶ/ር መቅደስ ይህን አስመልክቶ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ስር ባሉ ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም በዩኒቨርስቲዎችና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ጥናት እየተከናወነ ሆኑን አንስተዋል።
በዚህም "መድኃኒት መለማመድ የሚባለው ሙሉ ለሙሉ አለ አለ የምንልበት ደረጃ ላይ አይደለም።" ሲሉ አንስተዋል። ለዚህም አመላካች ያሉትን ጉዳይ ሲያነሱ፦
ከዚህ ቀደም ባሉ ዓመታተ ያለው የበሽታ ተጋላጭነት ቁጥር እንዲሁም ሆስፒታል ገብቶ የመተኛት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ሆስፒታል ተኝቶ የመታከም ቁጥሩ ዝቅ ማለቱን አንስተዋል።
ይህም ዜጎች በበሽታው ተይዘው ወደ ሆስፒታል በሚሄዱበት ወቅት መድኃኒት ሲያገኙ የመሻል ነማገገም አዝማሚያው ከፍተኛ መሆኑን ነው የጠቀሱት።
ዶ/ር መቅደስ አክለውም፥ ጥናቶች ግን አሁንም መካሄዳቸውን እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት።
ከዚህ በተጨማሪም፥ በ2017 በጀት ዓመት በተሰራው የንቅናቄ ሥራ ጋር ተያይዞ 8 ሚሊዮን የሚሆን የመድኃኒት እንዲሁም 6 ሚሊዮን የሚሆኑ የፈጣን መመርመሪያ ኪቶች ሥርጭት መደረጉን ጠቁመዋል።
ከአጎበር ሥርጭት ጋር ተያይዞም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከነበረው 19.7 ሚሊዮን የሚሆን የአጎበር ሥርጭት ተጨማሪ በዚህ በጀት ዓመት 2.2 ሚሊዮን የሚሆን አጎበር መሰራጨቱን ጠቅሰዋል።
ከ 2 ሚሊዮን በሚሆን ቤቶች ላይ ቀድሞ በተሰራ የቅኝት ሥራ የአጎበር የመጠቀም ልምዱ ከ50 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም ባለፉት ወራት በተሰራ ሥራ ይህን ወደ 70 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።
ከህገወጥ የመድኃኒት ቁጥጥር ጋር ተያይዞም 450 ኩንታል መድኃኒት በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት 9 ኩንታል የሚሆነው ከመንግሥት ቤት የወጣ መድኃኒት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ 75 በመቶ የሚሆነው አከባቢ ለወባ ምቹ ነው የተባለ ሲሆን 70 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍልም በእነዚሁ አከባቢ የሚኖር ነው።
@TikvahethMagazine