ከዚህም ከዚያም SCAM


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Quotes


⚠️ Warning: Many users reported this account as a scam or a fake account. Please be careful, especially if it asks you for money.

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Quotes
Statistics
Posts filter


Forward from: 👸🏻PRINCESS HANAN👸🏻
ሀላል ዘውጅ ምትፈልጉ ብቻ ይቀላቀሉ በአላህ ፍቃድ እናገናኛቹዋለን🤵👰

t.me/halalzewaj


#እምነትህ_ይኑራቹ
ሕይወት እምብዛም እንደታቀደው በትክክል አይሄድም፡፡ብዙውን ጊዜ ሕይወት እኛ ለመጓዝ ወዳሰብንበት መንገድ ሳይሆን ፍጹም በተለየ አቅጣጫ ይወስደናል።...
#ምንም ቢከሰት ግን ... እምነት ይኑራቹ!
አሁን ላይ ባይሳካም፣ በስተመጨረሻ ይሳካል የሚል እምነት!.....
#እምነት ማለት አንድ ነገር እንደሚከሰት ምልክቶች ባይኖረን እንኳ እሱ(ፈጣሪ) ካለው ግን ይሳካልናል ብሎ ማመን ነው።
#እምነት ማለት ሕልመኛነታቹን ማንም ባያምንምበትም እንኳ በእራሳቹ ማመን ነው።
#እምነት ማለት በሕይወታቹ ከባድ አውሎ ነፋስ መካከል ተቀምጣቹ ነገር ግን ዓይኖቻችሁን ጨፍናቹ ፀሐያማ እና የተረጋጋውን ሰማይ በጭንቅላታቹ መሳል መቻል ነው።በዙሪያቹ ካሉ ከሚረብሿቹ አውሎ ነፋሶች ይልቅ እየመጡ ያሉትን ጥሩ ቀናቶችን Feel ማድረግ ከቻላቹ..#ያ እምነት ነው!
#አንዳንዴ ማየት ለምትፈልጉት ህልም ብላቹ ሁሉንም ነገር አደጋ ላይ ትጥሉት ይሆናል...ነገር ግን እዚያ መድረስ የምትፈልጉት ሕልማቹ ላይ ለመድረስ ምንም አይነት መስዋእትነት ቢያስከፍላቹም በሕልማቹ ውስጥ እምነት ይኑራቹ ፡፡ምንም አይነት ጊዜ ቢወስድባቹም
: “በመጨረሻም እንደሚሳካ እምነት አለኝ” ብላቹ ለራሳቹ ንገሩ።
#እምነት የመንገዱን ሙሉውን ማየት ባትችሉም እንኳን በሕይወታቹ ላይ የመጀመሪያውን እርምጃ መራመድ መቻል ነው ፡፡የተቀረውን መንገድ ማመን ከቻላቹ በእራሱ ጊዜ እና ሰዓቱ ይገለፅላቹሀል...ነገር ግን ወደፊት መጓዛቹን ከቀጠላቹ ነው!
#እምነት ማለት መድረስ የምትፈልጉት ቦታ ላይ ለመድረስ በመሐል ላይ የሚከሰቱ ፍጹም ያልሆነበት ሁኔታዎችን እና አስቸጋሪ ጊዝያት ላይ ቢሆን እንኳ በእምነት ወደዚያ ቦታ መውጣት እና መከሰት መቻል ነው።#ነገር ግን የምትፈልጉት ቦታ ላይ ለመድረስ በመሐል የሚከሰቱት ሁኔታዎች ፍጹም እና የተስተካከሉ እስኪሆኑ ድረስ የምትጠብቁ ከሆነ ምናልባት ለዘላለም ያስጠብቃቹ ይሆናል!
#እምነትህ_ይኑራቹ
ኹሉድ ኑሪ


በሕይወታቹ ውስጥ ያሉ ሰዎች ከእርስዎ ጋር የመጨረሻ ቀን ይኖራቸዋል።ግን መቼ እንደሚሆን እንኳን አታውቁም ፡፡
እነሱ ለእናንተ ብቁ ከሆኑ አብሮነታቹ እስካለ ድረስ ተደሰቱ፣ብቁ ካልሆኑ ግን በቻላቹት ጊዜ ከሕይወታቹ ቁረጧቸው።
ፍቅርን አሳድዶ ወይም አስገድዶ ለመቀበል አትሞክሩ፡፡ፈጣሪው ባለው በትክክለኛው ጊዜ እውነተኛ ፍቅር በሕይወታቹ ላይ ይከሰታል እስከዛው ግን እናንተ በራሳችሁ ላይ በማተኮር እና ህልሞቻቹን በማሳደድ ጊዜያችሁን አሳልፉ ፡፡ያኔ ፍቅር እራሱ ፈልጎ ሲያገኛችሁ እና በአጋጣሚ በሕይወታችሁ ላይ ሲከሰት ያንን ሰው ፈጣሪ ሆን ብሎ ለማገናኘት እንደፈለገ ይገባቹሀል ፡:
"መጥፎውን ፖም🍎 ካልቀመሳቹ ጥሩውን ፖም🍏 በጭራሽ ማድነቅ አችሉም" so what i am tryinn to say is ህይወትን ጣዕም ለመረዳት የህይወትን ጣፋጩንም መራራውንም ጎን መቅመስ ይኖርባቹአል‼️✌️😊


....ሁለት ገፅታ....
(ክፍል ስምንት- የመጨረሻ ክፍል)
(በኹሉድ ኑሪ)
ምንም ማድረግስላልቻሉ ዝም አሉኝ ዶክተሩ ንግግሩን ቀጠለ"የታማሚዎ symptom በጣም ከባድ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነው የሚያሳየው ለምንድነው እዚህ stage ላይ እስክትደርስ የጠበቃቿት" ብሎ ተቆጣንና የኛን መልስ ሳይጠብቅ ንግግሩን ቀጠለ "አሁን ባደረግንላት የChest X Ray አና የደም ምርመራ እህታቹ የCongestive heart failure(CFH) ተጠቂ ናት CFH ማለት ወደልብ ልክ እንደበፊቱ ደም በደምብ መውጣት የማይችልበት ስር የሰደደ ሁኔታ ነው በተጨማሪም ይኀ በሽታ የልብ ፍላጎትን ለማርካት እንደ ፓምፕ ሆኖ የሚያገለግለው part በቂ እንዳይሆን አድርጎ የሚጎዳ በሽታ ነው። ይሄ በሽታ የሚመጣው በተለያየ ምክንያት ቢሆንም most of the time የሚከሰተው ከበቤተሰብ ዘር የቀጠለ ወይ በከፍተኛ ደምግፊት አልያ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የአልኮል እና በሲጋራ ሱሰኝነት ነው እህታቹ ያላት የ6ወር ጊዜ ነው ስለዚህ በአፋጣኝ ሚያስፈልገውን ነገር ጨርሳቹ ወደ ውጭ ሄዳ የልብ ንቅለ ተከላ ማድረግ አለባት processኡን ለመጨረስ እንዲረዳቹ እኔ ከዚህ ማስረጃ እፅፍላቹአለው"አለን። ሁላችንም ቅስማችን ተሰባብሯል ሆኖም የፊርዶውስን ሕይወት ከአላህ ጋር ለማዳን ያለን አማራጭ መጠንከርና መፍጠን ነው።ለነጅዋ እዚህ የተፈጠረውን ስንነግራት እሷ ጋር ሄዳ እንድትታከም ነገሮችን ማመቻቸት ጀመረች። ፊርዲ ትንሽ እንድታገግም ብለው እዛው አስተኟት እኔና የፊርዲ እናት ፊርዲን እየተመላለስን ስንከባከባት ኢምራንና ዓሊ ደግሞ ጉዳዩን ለማስጨረሽ ላይ እታች መሯሯጥ ጀመሩ።ከብዙ ልፋት እና ድካም በኋላ የፊርዲ process አለቀ።ዓሊ እኔ መውለጃዬ ስለተቃረበ ኢምራን እዚ አብሮኝ መሆን አለበት በሎ ስላሰበ ከፊርዲ ጋር እሱ እንደሚሄድ ነገረን።
ፊርዲናፍቃናለች፣ጨዋታዋ፣ሳቋ፣እብደቷ፣ምክሯሁሉም ነገሯ ናፍቆናል።አሁን ፊርዲ አታወራም እሷ ጋር ከሄድን የምንሰማው የልብ ምት መከታተያውን የማሽኑን ድምፅ ብቻ ነው።ፊርዲ ከብዙ ጥንካሬዎቿ በኋላ ተሸነፈች ያኔ መኖርን ሳትፈልግ ብዙ መጥፎ ነገሮችን ስታደርግ ምንም ያልሆነችው እንዴት አሁን በሕይወቷ ተስፋን ስታገኝ፣ነገን ለማየት ስትጓጓ፣ነገን ለመለወጥ ስትተጋ እንደዚህ አይነት ነገር ተፈጠረ ብዬ አማርር እና መልሼ ደግም የአላህ እርዳታ ቅርብ እንደሆነ፣አላህ የፈለገውን እንደሚያደርግ፣ በሕመሟም ወንጀሎቿን እያበሰላት እንዳለ አስብ እና ወደራሴ እመለሳለው።የዓሊ እና የፊርዲ መሄጂያ ተቃረበ ይዘውት የሚሄዱት እቃዎችን እያዘጋጀው እያለ ሆዴን ቁርጠት እና ጀርባዬን በጣም አመመኝ ይኼ ስሜት የምጥ ሊሆን ይችላል ብዬ ስላሰብኩኝ አጠገቤ ያለውን ስልክ አንስቼ ኢምራን ጋር ደውዬ የዓሊን መኪና ይዞ እንዲመጣ ነግሬው መጣ። መኪና ውስጥ ሊያስገባኝ ሲል የሽርት ውሃ ፈሰሰኝ ሁለታችንም ስንደነባበር የፊርዲ እናት መጥተው አረጋግተውን አብረውን ሄዱ።ፊርዲ የተኛችበት ሆስፒታል ስንደርስ ነርሶቹ በዊልቸር እየገፉ ወደ መውለጃ ክፍል ይዘውኝ ገቡ። የፊርዲን እናት ኢምራን ወደ ቤት ልኳት ዓሊ እና ፊርዲ ማታ ሰለሚበሩ እቃውን እንድታስተካክል ነገራት።ዓሊ እዛው ፊርዲ ጋር ስለነበር ኢምራን ደወለለት።ኢምራንና ዓሊ አንዴ እኔ ጋር አንዴ ፊርዲ ጋር በጭንቀት እየተመላለሱ መጠበቅ ጀመሩ።
እኔ በዶክተርና ነርሶች ተከብቤ አይዞሽ ግፊ ይሉኛል የሰውነቴ አጥንቶች አንድ በአንድ እየተነቃቀሉ ነበር የመሰለኝ በጣም አሞኛል በዛጭንቀት ሆኜ ግን ለፊርዲ ነበር ዱዓ ማደርገው"የዓረብ እሷ ብዙ ተፈትናለች፣እሷ ብዙ ተሰቃይታለች በቃሽ በላት ለሷ የመጣውን ለኔ አድርገው" እያልኩኝ አለቅሳለው እኔ ምጥ ላይ ብዙ ስለቆየው እነ ዓሊን ሳልሰናበታቸው ሄዱ ከ 6 ሰዓት ስቃይ ቀኋላ ሴት ልጄን ወደዚ ዓለም ቀላቀልኳት አልሃምዱሊላህ ሁፍፍፍ አልኩ ወዲያሁኑ ኢምራን ልጁን ከዶክተሮቹ ተቀብሎ አዛን አለባት ቀይ ቆንጂዬ ናት ኢምራን አቅፏት በደስታ አንዴ እኔን አንዴ እሷን ይስማል።በድካም እንደዛልኩ "ዓሊስ" አልኩት የበረራ ሰዓት ደርሶባቸው እንደሄዱ ነገረኝ አለቀስኩኝ የአላህ መጥፎ ነገራቸውን እንዳታሳየኝ ብዬ ለመንኩት ። ኢምራን "እሺ እናትየው የልጅሽን ስም ማን እንዲሆን አሰብሽ"ብሎ ፈገግ ብሎ አየኝ እኔም "ፊርዶውስ"አልኩት ኢምራን ደስ አለውና "ዑሙ ፊርዶውስ"ብሎ ግንባሬን ሳመኝ።
......ከ አንድ አመት በኋላ
የጠዋት ፀሃይዋ ድምቅ ብላለች ከሌላው ጊዜ ይበልጥ ሰላም የሰፈነባትና ውብ ሆናለች ኢምራን ጊቢ ውስጥ"ቀስ በይ ፊርዲ ዳዴ ዳዴ"እያለ ከቆንጅዬ ልጃችን ጋር ጊቢውን ይዞራሉ። "አንቺ ሰብሪን ተንቀሳቀሺ እንጂ እንግዶች ሊመጡኮ ነው እናንተ ቀስ በሉ እንዳትወድቁ"እያለች ከቤት እየተሯሯጡ ያሉትን ልጆችዋን ትቆጣቸዋለች ነጅዋ ነበረች። እሺ ብያት ወደ ቤት ገብቼ ለሰርግ የተከፈተውን መንዙማ እስከመጨረሻው ድምፅ ሰጠሁትና ከነጅዋ ባል ጋር ዲኮሩን ማስተካከል ጀመርኩ። ዛሬ ፊርዲን እና የዓሊን መልስ ጠርተናቸዋል አልሃምዱሊላህ የሃሳቤ ሁሉም ተሳካልኝ ሁሉም ነገር ሞላልኝ ከአላህ ጋር ምንም የማያልፍ መከራ በሳቅ የማይተካ ለቅሶ በደስታ የማይተካ ሐዘን የለም አላህ ሁሉን አዋቂ ነው "በእርግጥም ከሀዘን በኋላ ምቾት አለ"ለነገ የተዘጋጀልንን ውብ ነገር ለማየትና የለፋንባቸውን ነገሮች ውጤት ለማየት ብቸኛው መፍትሔ ዛሬ ላይ ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ምክንያቱም ተስፋ የቆረጠ ሰው የ አንድ ሰኮንድ እድሜ እንኳ የለውም።ለዛሬ ደስታ ብለን የዛሬን ችግር ለመሸሽ ና ለመደበቅብለን ነገአችንን አናበላሽ።
............ተፈፀመ.............


....ሁለት ገፅታ....(ክፍል ሰባት)
(በኹሉድ ኑሪ)
እኔ እና ፊርዲ እምቢ ብንልም ከረጅም ውትወታቸው በኋላ ተስማማን የምንሄድበት ቦታም ከኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች አንዷ ወደሆነችው በስተምሥራቅ ወደምትገኘው ወደ ውቢቷ የፍቅር ሀገር ሀረር እንዲሆን ወስነን መንገድ ጀመርን ከረጅም ሰዓት ጉዞ በኋላ ወደ የብሄር ብሄረሰቦች መገኛ የዐማራ ፣ የኦሮሞ ፣ የሐረሪ ፣ የጉራጌና የሶማሌ እና የበርካታ ጎሳዎች ቤታችን ብለው ወደሚጠሯት በሕብረ ቀለም ወዳሸበረቀችው ውቢቷ ከተማ በሰላም ደረስን።ኢምራን ሀረር በደምብ አድርጎ ያውቃት ስለነበር ሁሉንም ቦታ ያውቅ ነበር።እዛ እንደደረስን በ ረውዳ ዋበር በሚባል ባህላዊው የሐረሪ እንግዳ ማረፊያ አረፍን በሀረሪ ለአራት በቆየንባቸው አራት ቀናቶች የሀረርን ሱስ የሚያሲዝ ቡና እየጠጣን፣የተለያዩ ሃላዋዎችን እያጣጣምን፣በሐረር የጎዳናዎች ላይ በምናያቸው ምርጥ ምርጥ ነገሮችን በ ፎቶግራፍ አንስተን ለታሪክ እያስቀመጥን፣ በአሮጌዋ ከተማ መሃል ላይ በሚገኝ ቆንጆ የህንድ ነጋዴ ቤት ውስጥ የሚገኘውን አርተር ሪምቡድ የሚባለውን ሙዚየም፣የራስ ተፈሪ ቤት ሸሪፍ ተብሎ የሚጠራው ኃይለ ሥላሴ (ራስ ተፈሪ) የጫጉላ ሽርሽራቸው ያደረጉበትን ሀረር ከተማ ሙዚየም፣ግድግዳው በቀስተ ዳመና ቀለም የጌጠውን ሐረር ጁጎልን፣በባቢሌ የሚገኘውን የሶማሊያዎች የግመል መሸጫንና በተለያዩ ስሞች የሚጠሩ የሃረር ገበያዎችን እስኪበቃን ጎበኘናቸው በስተመጨረሻም የሐረር የዱር ጅቦችን መግበን ምርጥ አይረሴ ጊዝያቶችን አሳልፈን ወደቤታችን መጣን።
ፊርዲ በጣም ደስተኛ ሆናለች እሷ ብቻ ሳትሆን ሁላችንም ነን ደስተኞች የሆነዉ አንድ ቀን እሁድ ጠዋት ላይ እኔ እና ዓሊ ቁርስ እየበላን የቤታችን በር ተንኳኳ በሩን ለመክፈት እኔ ነበር የሄድኩት ፊርዲ እና ኢምራን ነበሩ "እንዴ አሰላሙ አሌይኩም ወራኽመቱላሂ ሰዎች በሰላም ነው?" አልኳቸው
"እእ ወአለይኩም ሰለም ወራኽመቱላህ"አሉኝ በአንድ ላይ ፊርዲም"ምንድ ነው ቤታችን በፈለግነው ሰዓት መምጣት አንችልም እንዴ" አለችኝ እና ሁለታችንን ጥላን ወደውስጥ ገባች እኔም ተከትያት ልገባ ስል ኢምራን "ሰቡሪ አንዴ ላናግርሽ?" ብሎ አንገቱን በእፍረት አጎነበሰ ግራ እየገባኝ ዞርኩኝ እና"ወዬ ኢምሩ ምነው ችግር አለ እንዴ?"አልኩት"ኧረ ምንም የለም አንዴ ብቻሽን ማወራሽ ጉዳይ ነበረኝ እእ ይኸውልሽ ሰብሪኔ እእ ምን ነበር ሁፍፍ" ሲል አሳቀኝ"እንዴ ኢምሩ ምንድነው እስኪ ተረጋግተክ ንገረኝ"አልኩት "እሺ ምን መሰለሽ ሰቡሪ እእ እኔ አንቺን ማግባት እፈልጋለሁ ማለት አፈቅርሻለሁ እእ እና ማለት አለ አደል በስርዓቱ ዓሊን ጠይቄ አንቺን ሃላሌ ማድረግ እፈልጋለሁ ማለት እሱ ከማወቁ በፊት ፍቃደኝነትሽን ልወቀው ብዬ ነው"አለኝ አላውቅም ድንጋጤ ይሁን ደስታ ለረጅም ሰዓት ደንዝዤ ቀረው "ማለት ተንበርክኬ ምናምን መጠየቅ እችል ነበር ግን ያው በሸሪዓው መንገድ በስርዓቱ ልጠይቅ ብዬ ነው ማለት መብትሽ ነው ምንም ብትወስኚ እኔ አላዝንብሽም" አለኝ እኔም ከፈዘዝኩበት ብንን አልኩና በደስታ እንደምስማማ ነገርኩት በጣም ደስተኛ ሆነ ግን ከዛ በፊት ለጋብቻው እኔ ወንድሜን ማማከር እንዳለብኝ ነገርኩት በጣም ደስ ብሎኛል ነገር ግን ከዓሊ በፊት ማግባቴ እና ብቻውን ጥዬው ልወጣ እንደሆነ ሳስብ ውስጤ ተረበሸ።ሁለታችንም ተከታትለን ገባን ዓሊ ኢምራንን ተነስቶ ሰላም ብሎት ቁጭ አለ።ፊርዲ ፊት ፊታችንን መልስ ፍለጋ ታያለች ወድያሁኑ እሷ እንደሰማች ገባኝ ኢምራን ጠቀሳትና ፈገግ አለ እኔንም ስታየኝ ጭንቅላቴን በአወንታ ስነቀንቀው መልሱ ምን እንደሆነ አወቀች በጣም ደስ አላት በቃ ቡና ላፍላ እኔ ብላ ፍንጥር ብላ ተነሳች ዓሊ"እንዴ ይቺ ልጅ ዛሬ ምንሆና ነው ምትቁነጠነጠው እናንተ እስክትመጡ እኮ ስንቴ ቁጭ ብድግ እንደሰራችብኝ" ብሎ በግርምት ሲያያት እኔ እና ኢምራን ተያይተን ሳቅን የዛን ቀንን ስንጫወት አምሽተን ፊርዲ እና ኢምሩ ወደቤታቸው ሄዱ።ዓሊ ሊተኛ ሊገባ ሲል ማናግረው ነገር እንዳለ ነገርኩት ሊሰማኝ ቁጭ ሲል እየፈራው እየተንተባተብኩኝ እኔ እና ኢምራን ያወራነውን ነገርኩት እሱም በጣም ደስተኛ እንደሆነ ነገረኝ ነገር ግን "ከእናትና አባትሽ ማስታወሻ ከሆነው ቤት ወጥተሽ የኪራይ እንድትኖሪ ስለማልፈልግ ትልቁን መኝታ ቤት እለቅላቹአለው ከእዛ እኔ አንቺ ክፍል እተኛለሁ"አለኝ በአንዴ ሸክሜ ሲቀል ታየኝ ተነስቼ አቀፍኩት እሱም "እህቴ ለካ አድገሽልኛል"ብሎ አቀፈኝ ለኢምራን ዓሊ መስማማቱን እና ያቀረበውን ሃሳብ ነገርኩት መጀመሪያ ላይ ትንሽ ቢያንገራግርም በመጨረሻም ተስማማ።
በስርዓቱ ሽማግሌ ልኮ እኔን እንዲሰጠው ጠየቀ ዓሊም ከ ሁለተኛ ቀጠሮ በኋላ እሺታውን ገለፆ የሰርጉን ቀን ቆረጡ።ሰርጌ 1 ሳምንት ሲቀረው ነጅዋ ከልጆቿ እና ከባለቤቷ ጋር መጣች ደስታዬ እጥፍ ድርብ ሆነ ስለ ፊርዲ እና ኢምራንን ሁሉንም ነገር አጫውታት ስለነበር አዲስ አሎኑባትም።ከሳምንት በኋላ ሰርጉ ተደግሶ ኢምራንን የግሌ አደረግኩት አልሃምዱሊላህ ሁሉ ሃሳቤ ተሳካልኝ ነገር ግን የፊርዲ እና የዓሊ ነገር ያሳስበኝ ነበር ሁለቱን ብድራቸው ጭንቀቴ ይቀልልኝ ነበር።ጊዜ ሄደ ነጅዋም የእረፍት ቀኗን ጨርሳ የልጆቿ ትምህርት ሊጀመር ስለነበር ወደ ሀገሯ ተመለሰች።ከወራቶች በኋላ ፊርዲ የራሷን የልብስ መሸጫ ሱቅ ከፍታ አብረን እዛው መዋል ጀመርን በትርፍ ሰዓታችን ደግሞ ልጇቹን ቁርአን ማስቀራታችንን ቀጠልን አንድቀን በጣም አሞኝ ከፊርዲ ጋር ሐኪም ቤት ስንሄድ የ2ወር ነብሰጡር መሆኔን ነገሩኝ እኔ እና ፊርዶስ በጣም ተደሰትን ቤት ሄደን ለነዓሊ እና ኢምራን ነግረናቸው ቤት ውስጥ ከቆንጆ እራት ጋር የደስታችንኝ ቀን አከበርን።
ጊዜያቶች እየሄዱ ወራቶች እየተተኩ መጡ የእኔም መውለጃ እየተቃረበ መጣ። ፊርዲ ግን ልክ አደለችም ከቀን ወደቀን ብዙ የእመም አይነቶችን ማስተናገድ ጀመረች ሆስፒታል ብንሄድም አንዴ ጨጓራ አንዴ ኩላሊት እያሉ የመድኃኒት መዓት ማቃም ጀመሩ።ከጊዜ ወደጊዜ ግን የፊርዲ የሕመም ስሜቶች እየጨመሩ የአልጋ ቁራኛ አደረጋት።ፊርዲ በኃይለኛው ያሥላታል፣አተነፋፈሷ እየተለየ ፣ ሰውነቷ እያበጠ ፣የምግብ ፍላጎቷ እየጠፋ ፣በየጊዜው እያቅለሸለሻት ፣የልብ ምቷ በከፍተኛ እየጨመረ ደረቷ ላይ በጣም እያመማት እና በነገሮች ግራ መጋባት ወይም የተሳሳተ ነገሮችን እያሰበች መጣች ፡፡ ሁላችንም ግራ ተጋባን እኔ ኢምራንና ዓሊ ቤታችንን ጥለን ከእናቷ ጋር ፊርዲን ማስታመም ቀጠልን።ዓሊ በወጣበት ከጓደኞቹ አንድ ታዋቂ እና ጎበዝ ዶ/ር እንዳለ ሰምቶ በዛው ሆስፒታሉ ሄዶ አናግሯቸው ባስቸኳይ እንዲያመጣት ነግረውት ወደ ቤት መጥቶ የፊርዶስን እናት ቤት እንዲቀመጡ አሳምነናቸው ለሦስት ይዘናት ሄድን።ወደውስጥ አስገብተው የመጀመሪያ እርዳ ሰጥተዋት በዛውም መረመሯት ዶ/ሩ የፊርዲ ውጤት ያስደነገጠው ይመስላል ።ሦስታችንንም ቢሮው አስጠራን ፊቱ ተለዋውጧል እና የፊርዶስ ምኗ እንደሆንን ካጣራ በኋላ እኔ ነብሰጡር ስለሆንኩኝ ውጪ እንድቆይ ቢነግሩኝም እምቢ አልኳቸው...........ይቀጥላል


......ሁለት ገፅታ....(ክፍል ስድስት)
(በኹሉድ ኑሪ)

በሩን የከፈተው ኢምራን ነበር ልክ እንዳየን የፊርዲ እግር ላይ ወድቆ እያለቀሰ ባደረገው አስነዋሪ ነገር ከልቡ እንደተፀፀተ፣በራሱ እንዳፈረ እና የሷን ይቅርታ ለማግኘት ምንም እንደሚያደርግ ነግሮ ይቅርታዋን ተማፀነ ፊርዲ ቢከብዳትም ተፀፅቶ እና ተሰምቶት ጥፋቱንም አውቆ ይቅርታ ስለጠየቃት በእጇ አነሳችው "አብሽር ይቅርታ አድርጌልሃለሁ"ብላ ዓይኗ ላይ የቀረረውን እንባ ጠረገችና ፈገግ አለች።ኢምራን ወንዳወንድ ነገር ነው ደንደን ያለ ሰውነትና ቁመና ያለው፣የቀይ ዳማ ሆኖ አፍንጫው ሰልከክ ያለ፣ ቅንድቡ በዛ ብሎ ጥቁር ያለ ነው አብሶ ከጆሮው ጫፍ እስከ ከናፈሩ ግጥም ብሎ የሚታየው ፂሙ ግርማ ሞገስን ሰጥቶታል ፣አይኖቹ አነስ ያሉ ሆነው የብሌኑ ቀለም የየትኛዋንም ሴት ልብ የሚሰርቅ ነው። ፈዝዤ እያየሁት እያለ ፊርዲ ወደ እኔ ዞረችና "ኢምራን ይባላል" አለችኝ።እኔም ደንገጥ ብዬ "ኦ ሰብሪን"አልኩት እና ወደ ውስጥ ገባን የፊርዲ እናት ከተቀመጠችበት ተነስታ ስትቀበለን ፊርዲ ተንደርድራ ሄዳ አቀፈቻት ሁለቱም ተላቀሱ ኢምራን ሄዶ ሁለቱንም አረጋጋቸው የፊርዲ እናት እኔንም ተዋወቁኝ በመቀጠልም ፊርዲ እስካሁን ያጋጠማትን ለ እናቷ ነገረቻት ከኢምራኑ ታሪክ ውጪ። ነገር ግን እናቷ ስለ ኢምራን ሁሉንም እንደሰማች እና የሷን ይቅርታ ፍለጋ የዛኔ አይታው ከቤት የወጣች ቀን ከመጣ እስካሁን እንዳልሄደ ነገረቻት።ፊርዲ ስለሷ ያለውን ሁሉን ነገር ከነገረቻት ወዲህ በእናቷ እና በአባቷ ጉዳይ በአጠቃላይ ስለደበቋት ነገሮች ማወቅ እንደምትፈልግ ነገረቻት የፊርዲ እናት ትንሽ ካቅማማች በኋላ ታሪኩን እንዲህ ብላ ጀመረችው "ፊርዶውስ እኔ እና አባትሽ ተጋብተን ረጅም ጊዜ ብንቆይም ልጅ እምቢ ይለናል ሁለታችንም በጣም ነበር የልጅ ፍላጎት የነበረን አባትሽ የወንድ ልጅ ጉጉት ነበረው እኔ ደግሞ የሴት ልጅ።ለዛ ብለን ሆስፒታል ስንሄድ ችግሩ ከእኔ እንደሆነ ይነገረናል በዛ ምክንያት በጣም አዘንን አባትሽ ሌላ አግብቶ ሀሳቡን እንዲያሳካ ብወተውተውም በፍጹም አሻፈረኝ አለ።ይሄን ችግራችንን የሚያውቀው የአባትሽ ወንድም የኢምራን አባት ብቻ ነበር።በዛን ስዓት እሱ እና ሚስቱ ከኢምራን ጋር በኪራይ ቤት ውስጥ ነበር ይኖሩ የነበረው። የአባትሽ ወንድም የሆነ ቀን ለእኛ አሳቢ መስሎ አንድ ሃሳብ ይዞልን መጣ እሱም በሚቀጥለው የሚወልዱትን ልጅ ለእኛ እንደሚሰጡንና እኛ ደግሞ በምላሹ 5 ሚሊዮን ብር እንድንሰጠው ጠየቀን።አባትሽ ወዲያው ነበር የተስማማው እኔ ግን ምንም አልተስማማሁም ነበር። ከ አመት በኋላ አንቺ ተወለድሽ እኛም አንቺን ስንቀበል እሱም ብሩን ወሰደ።ልጅ እያለሽ ውስጤ ቢከብደኝም ተንከባክቤ አሳደግኩሽ እያደግሽ ስትመጪ ግን ከእኔ እሱን መቅረብ ጀመርሽ ሁሌም ቢሆን እቀና ነበር።ከዓመታቶች በኋላ የአባትሽ ወንድም ከእኛ አጠገብ ያለውን ቤት ገዛው እና እዛ ገቡ። ሁሌ እየመጣ ገንዘብ ከአባትሽ መቀበል ስራ አደረገው ከእኔ ጋርም በሱ ምክንያት ሁሌ እንጨቃጨቅ ነበረ ጊዜው ሲሄድ አንቺም እያደግሽ የአባትሽ ወንድም ማስፈራርያም እያደገ መጣ ጭራሽ ወይ ንብረቶቹን ወይ አንቺን እንዲመርጥ አስገደደው።አባትሽ ግን አንቺን መረጠ ፎቁን ወሰደበት ከዛ መኪናውን ከዛ በመጨረሻም ቤቱን ወሰደበት እኔ ተው እያልኩት እኔን ሳያማክር ሁሉንም ነገር በራሱ መወሰኑ አበሳጨኝ እና ጥዬው ወጥቼ ክፍለ ሃገር ያሉት ዘመዶቼ ጋር ሄድኩኝ ግን ሁሌም ስለእናንተ እጠይቅ ነበር።በመጨረሻም አባትሽን መታመም ስሰማ እሱን ለማሳከምን ያለኝን ወርቆች ሽጬ የቀን ስራ ገብቼ መኪናዬን ሽጬ ብሩን አሞላልቼ ስመጣ አላህ ፈለገው ሆነና ከእኔ ቀድሞ ወሰደው።ኢምራንም በእኛ እና በቤተሰቦቹ መሐከል የተፈጠረውን ባያውቅም ቤቱን ወስደው ከአዚያ እንዳስወጡን ሲያውቅ ቤቱን ጥሎላቸው ጠፋ አሁን እነሱ ንብረቶቹን እንዳለ ሽጠው በአሜሪካን ተደላድለው እየኖሩ ነው" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ፊርዲ እና ኢምራን ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ግራ በተጋባ አስተያየት ተያዩና መለስ ብለው አዩዋት ከዛ ፊረዲ"እናቴ ምን እያልሽኝ ነው ኢምራን ወንድሜ ነው?" ብላ አፈጠጠችባት እናቷም ጭንቅላቷን በአወንታ ነቀነቀችላት ፊርዲም ኢምራንም እኔም የሰማነውን ማመን አቃተን ኢምራን ከተቀመጠበት ተንደርድሮ መጥቶ በቁጭት ፊርዲን አቅፏት አብረው ድምፅ አውጥተው ማልቀስ ጀመሩ ላረጋጋቸው ብሞክርም አልቻልኩም ከእራሳቸው አልፈው እኔንም አስለቀሱኝ ከረጅም ሰዓት ለቅሶ በኋላ ሁሉም አፉ ተባብለው ፊርዲ እና ኢምራን ሊሸኙኝ ተያይዘን ወጣን ፊርዲ አስቆመችኝ እና እንዲህ አለችኝ "ሰብሪን አንቺ ከአላህ ለእኔ የተላክሽ ስጦታዬ ነሽ አላህ እንዳረሳኝ በተግባር አንቺን ልኮ አሳይቶኛል ለሁሉም ነገርምክንያቷ አንቺ ነሽ ለምስጋና ቃላት ያጥረኛል ብቻ ምንም አትሁኚብኝ" ብላ ጭምቅ አድርጋኝ አለቀሰች እኔም ምንም ሳልላት አቀፍኳት።አልሃምዱሊላህ አሁን እነፊርዲ ቤት ሰላም ሰፍኗል ሃሣቤ ሞልቶልኛል ከእነሱ ጋር ተሰነባብቼ እቤቴ ገባው ዓሊ ሲመጣ የተፈጠረውን ነገር በሙሉ አጫወትኩት ዓሊ ለፊርዲ ከልብ አዘነላት ከዛን ጊዜ ጀምሮ የኔ እና የፊርዲ ግንኙነት ጠነከረ ከእኛ አልፈን ኢምራንና ዓሊም ጓደኛሞች ሆኑ ኢምራን ስራ ዓሊ ጋር ገባ መኖሪያውን ደግሞ እነ ፊርዲ ጋር አደረገው።ፊርዲ ሱሶቿን ለማቆም ብትቸገርም በአላህ እርዳታ እና በእኛ እገዛ ከሱስ ነፃ ሆነች።ፊርዲ ሰላት ሰግደን ከጨረስን በኋላ ሁሌም ጌታዋን ምህረት ትጠይቃለች ሁሌም ወንጀሎቿን ይቅር እንዲላት ተንሰቅስቃ አልቅሳ ትጠይቀዋለች።ፊርዲ ከጊዚያቶች በኋላ ገላ የቀቀረቻትን የድሮዋን ገፅታዋን ዳግመኛ ተላበሰቻት ጅልባቧንም መልሳ አደረገችው አቅራቢያችን ባለው መስጂድ ውስጥም እኔ እና እሷ በፍቃደኝነት ሴት ህፃናቶችን ቁርዓን ማስቀራት እናፊርዲ ከራሷ ሕይወት ተሞክሮ ተነስታ ዳዕዋ ማድረግና ልጆችን ወደ ትክክለኛው መንገድ ማቅናት ጀመርን።አንድ ቀን ዓሊ እና ኢምራን ከከተማ እንድንወጣ ጠየቁን....ይቀጥላል


.....ሁለት ገፅታ....(ክፍል አምስት)
(በኹሉድ ኑሪ)
ያሬድን ከአንዷ ሴት ጓደኛችን ጋር እርቃናቸውን ተኝተው ደረስኩባቸው።የማየውን ማመን አቃተኝ ኬኩን በቁም ስለቀው ሁለቱም ደንገጥ ብለው ተነስተው አዩኝ እና መደነባበር ጀመሩ ምንም ሳልተነፍስ ፊቴን አዙሬ ስሄድ ያሬድ ልብሱን ደርቦ ከኋላዬ መጥቶ ያዘኝ ዞሬ በጥፊ ብዬው እጄን አስለቀኩትና ወደ እናቴ ቤት ሄድኩኝ ቀጥታ መኝታ ቤት ገብቼ ዘጋሁትና ኮመዲና ውስጥ ያሉትን መድኃኒቶች በሙሉ ቃምኳቸው ኻዲማችን ሁኔታዬ ስላላማራት እናቴን ጠርታ ተከትላኝ ነበርና በሩ ቢያንኳኩ አልከፈት ሲላቸው ሰብረውት ገቡ። እኔ ወድቄ አረፋ ስደፍቅ አገኙኝ ተሸካክመው ሆስፒታል ወሰደው አሳከሙኝ።ከዛን ጊዜ በኋላ በተደጋጋሚ ራሴን ለማጥፋት ሞከርኩ አልተሳካልኝም፣ በተናደድኩኝ ቁጥር ይሄው እጄን ጠባሳዎችን እንዳየሽው ነው ሁሌ እተለትለዋለው፣ጊዜው ሄዶ ከያሬድ ጋር ከተለያየን ዓመታት ቢያልፉም እኔ ግን ውሎዬን በሌላ ጫትና መጠጥ ቤት ቀይሬ ሁሌ እየሰከርኩኝ ቤቴ ለአዳር ብቻ መምጣት ጀመርኩኝ በተከታታይ እንደዚህ ሳደርግ እጄ ላይያለው ብር እየተመናመነብኝ መጣ።ግድ ስለሆነብኝ ቀን ቤቴ እየተኛው ሊመሻሽ ሲል እዚህ ቦታ መጥቼ ሱሴን ለማስታገስ ሲጋራዬን አጭሼ ባለችኝ ትንሽ ገንዘብ እያበቃቃው መጠጣት ቀጠልኩኝ በስተመጨረሻም እጄ ላይ ያለው ብር አለቀብኝ ።ከዛሬ ሦስት ቀን በፊት በጠዋት ተነስቼ እናቴን ብር እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት እሷ ግን አልሰጥም አለችኝ ከእናቴ ጋር በዚህ ምክንያት ብዙ ተጨቃጭቅንና ትቻት ወጣው እጄ ላይ ምንም ስለሌለ እና የምሔድበት ቦታ ስላልነበር ቀጥታ ኢምራን ጋር ነበር የሄድኩት። ለእሱ ከእናቴ ጋር ምን እንደተፈጠረ ነግሬው እና ለአንድ ቀን ብቻ እሱ ጋር ማደር እንደምችል ጠየቅኩት እሱም "በደስታ ነዋ" ብሎ መለሰልኝ እና "እንደውም ዛሬ አብረን ነው ዱዓ ምናደርገው" ብሎኝ ወጥቶ ጫት ይዞ መጣ።የኢምራን ለውጥ አስገረመኝ ጫትና እንደሚጠቅም የዛን ቀን ነበረ ያወቅኩት።የዛን እለት ሁለታችንም እየቃምን እና እያጨስን አመሸን እና ሰዓቱን ስናየው በጣም ሄዷል ነገ የሚሄድበት ስላለ መተኛት እንዳለብን ነገረኝ።እኔም እሺ ብዬ የቃምንበትን አነሳስቼ ጥጌን ይዤ ተሸፋፍኜ ተኛው የሆነ ሰዓት ላይ ግን ኢምራን ቀሰቀሰኝ እና አብሮኝ መተኛት እንደሚፈልግ ነገረኝ በመጀመርያ እየቀለደ ነበር የመሰለኝ ነገር ግን እየቆየ ኢምራን በፍጹም የማላውቀው እስኪመስለኝ ሌላ ሰው እየሆነብኝ መጣ ከመጠየቅ አልፎ እየታገለኝ መጣ እኔም አይሆንም ብዬ ስታገለው ይኸው እንደምታይው እንደዚህ አድርጎ ደበደበኝ እና ከቤቱ ውሻ አድርጎ በዛ ለሊት አባረረኝ።ግራ ገባኝ መሔጂያ አጣሁኝ አንድ ጥግ ላይ ፌስታል ለብሼ ተጠቅልዬ አደርኩ።ማይነጋ የለ ነግቶልኝ ወደቤቴ ሄድኩኝ እና ክፍሌ ገብቼ ቀኑን ሙሉ ኀይለኛ እንቅልፍ ተኛው።የሆነ ሰዓት ላይ ስነቃ የሰዎች ድምፅ ተሰማኝ ማን እንደሆነ ለማየት ወደ ሳሎን ስሄድ ኢምራን እና እናቴ ቁጭ ብለው እዬተሳሳቁ ነው።በጣም ተናደድኩ ውስጤ አረረ "ፍርዲ" ብሎ ሰላም ሊለኝ ሲነሳ ተመልሼ ወደ መኝታ ገብቼ ጃኬቴን ደርቤ ወጣው እና እግሬ ወዳመራኝ ሄድኩ ግን መሄጅያ እንደሌለኝ ሳውቅ ተመለስኩ በቃ በሁሉም ነገር ተዳከምኩ መኖር ሰለቸኝ ደከመኝ ካለሁበት ስሜት መውጣት ከበደኝ ተስፋ ቆረጥኩ ለሕይወቴ መፍትሔ ሞት ብቻ እንደሆነ ተሰማኝ ካለሁበት ደቂቃ ሽራፏን በዚ ዓለም ላይ ማሳለፍ አልፈለኩም አልቅሼ እንዳይወጣልኝ የዓይኔ የእንባ ከረጢት ደርቆአል ወደ ሱቅ ሄጄ እጄ ላይ ባለው ብር ምላጭ ገዛሁና እዚው በራቹ ጋር መጥቼ ሕይወቴን ለማቆም የደም ስሬን ቆረጥኩት ግን በድጋሚ እናንተ አዳናቹኝ ይሄውልሽ ሰብሪን የኔ ሕይወት ድቅድቅ ጨለማ ነው አላህ እኔን ረስቶኛል የምኖርበት ምንም ምክንያት አልታየኝም ተስፋ ሚባል ነገር እኔ ጋር የለም ታውቂያለሽ ብዙ ጊዜ ወደ አላህ ለመመለስ እፈልግና የአብዛኞቹን የወጣት ሙስሊሞችን ነገር ሳይ ከሩቅ እሸሻለው ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ሁሉም ይንቅሻል፣ይጠቋቆሙብሻል፣ቀርቦ ዳዕዋ እንደማድረግ ከሩቅ ያንጓጥጡብሻል፣የጀሀነብ መሆንሽን ቀድመው ወስነው ይነግሩሻል እና አንቺ በየት በኩል ትለወጫለሽ? ብዙ ጊዜ መንፈሴን ለማረጋጋትና ከአላህ ጋር ለማውራት ሂጃብና ቀሚስ አድርጌ ስገባ ወይ በቀሚሴ ጥበት ወይ ደግሞ የድሮ ስለሆኑ ትንሽ ያጥረኛል እናም ወይ በእጥረቱ ይጠቋቆሙብኛል በፌዝ መልክ አድርገው አላህ ተቀልብሶ ይስጥሽ ተብለው ተሳስቀው ይሄዳሉ ግማሾቹ አንቺ ሙስሊም ነሽ እንዴ ብለው አፌዘውብኝ ይሄዳሉ በቃ ከመስጂድ ከነጭራሹ ሸሸውኛ። እንግዲህ ሰብሪን የኔ ሕይወት ይሄን ይመስላል ስላዳመጥሽኝ አመሰግናለሁ" ብላ በእንባ የራሰው ፊቷ ስጠራርገው ወደ እሷ ዞሬ አቅፍኳትና ለረጅም ሰዓት አብረን ተላቀስን።በፍርዲ ቦታው እራሴን አሰብኩት ከባድ ነው በጣም ከባድ እኔ ሳስበው እንደዚህ የከበደኝ እሷ የምትኖረው እንዴት ትሁን? በቃ ሁላችንም መፅሐፍ ነን በውስጣችን ማብቂያ የሌለው የኑሮ መሰናክል፣ደስታ፣ሐዘንና፣የፌሽታ፣ለቅሶ የተቀላቀለበት ሙሉ የየራሳችን ታሪክ ያለበት መፅሐፍ ለዛ ነው አንድን መጽሐፍ በሽፋኑ አትፍረዱ ሚባለው የሰው ልጅንም ቀርበን ሳናይ ከላይ በሚታየው ገፅታ ብቻ መፍረድ ከባድ ነው።የሰው ልጅ ለሰው መድኃኒቱም መሆን ይችላል ማጥፊያ መርዙም መሆን ይችላል።
ለፍርዲ ትንሽም ቢሆን ተስፋ መስጠትልቅ እንዳለብኝ አሰብኩኝና እንዲህ አልኳት "ፍርዲ ወላሂ አንቺ ጠንካራ እሴት ነሽ እኔ አንቺን የምንመክርበት ወኔው የለኝም ግን ልልሽ የምፈልገው ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ አላህ አንቺን በጣም ይወድሻል ለዛም ነው ብዙ እድሎችን የሰጠሽ ብዙ ጊዜ እራስሽን ለማጥፋት ሞክረሽ አልተሳካልሽም አደል ለምን? ምክንያቱም እራሳቸውን ያጠፉ ሰዋች በአኼራ ከባድ ቅጣት ስለሚጠብቃቸው ምክንያቱም አላህ የሰጠሽን ሩሕ አንቺ በፍላጐትሽ ለመቋጨት ስበብያውን ስለፈጠርሽ ነው። ከያሬድ ጋር የተፈጠረው ነገር አላህ ለሁሉም ነገር ምክንያት አለው በአላህ ዘንድ የፍቅር ግንኙነት የተጠላም የማይፈቀድም ነገር ነው አደል ስለዚህ አንቺ እና እሱ እንድትለያዩ ወሰነ።ሌላው ደግሞ ከኢምራን ጋር የተፈጠረው አንቺ እና እሱ ብቻ ናቹ አደል ቤት ውስጥ ብትጮሂ ሰው አይሰማሽም ቢሰማም ወዳ ገብታ ነው ከሚል ማሕበረሰብ ጋር ነው ምንኖረው እንግዲህ አስቢው በዛን ሰዓት አንቺን መድፈር ይችል ነበር እኮ ግን አላህ ስላላለው ከቤት ደብድቦሽ ብቻ አሶጣሽ ከዛም መንገድ ላይ አደለም ለሴት ለወንድ ከባድ በሆነበት ወቅት አላህ ጠብቆሽ ቤትሽ አስገባሽ አየሽ አላህ ለሁሉም ነገር ምክንያት አለው ያልኩሽ ለዚህ ነው ምክንያቱም ላንቺ የመረጠልሽም ኸይርሽም ቤትሽ ብትኖሪ ነው ስለዚህ አላህ ውጪ የመኖር መንገዱን እንዳለ ዘጋብሽ በቃ እኮ አባትሽንም አላህ ጀነተል ፊርዶስን ይወፍቃቸው እና ኸይር ነገር እንደሰሩ ነው የሞቱት ሱብኃነክ ለዛው ያማረ አሟሟት ሸኻዳ ይዘው እስቲግፋር አድርገው ሁሉንም አፉ ብለው አደል ይኼን ሞት ስንቱ እንደሚመኘው ብታቂ እኛ የአላህ ነን ወደ እሱም ተመላሾች ነን ፍርዲ ወላሂ አላህ የሚወደውን ነው ሚፈትነው ሕይወትሽ አላበቃለትም ይሄ ገና መጀመርያው ነው ደግሞ አላህ በቁርዓኑ "ሰብረኞችን አብስሯቸው"ብሎ አደል ከአሁን ጀምረን ከአላህ እርዳታ የድሮዋን ፍርዲ ያንን ገፅታሽን ደግመን እንገነባታለን ጥርት ያለ ተውበትም እናደርጋለን እእእ ትስማሚያለሽ" ብዬ ፈገግ ብዬ ሳያት ጭንቅላቷን በአወንታ ነቀነቀችው "እሺ በይ ተነሽ አሁን እጅሽን ሳይነካው ቀስብለን ገላችንን ከመታጠብ እንጀምራለን ልብሶች እኔ ጋ


.......ሁለት ገፅታ....(ክፍል አራት)
(በኹሉድ ኑሪ)

"እሺ ከልጅነቴ ልጀምርልሽ እኔ የቤቱ ብቸኛ ልጅ ነኝ ተወልጄ 17 አመት እስኪሞላኝ ድረስ እንኖር የነበረው ሳር ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነበር ። ቤታችን ቤተመንግስት ነበር የሚመስለው በሰፈሩ የታወቅን ሃብታሞች ነበርን ። አባቴ በጣም ጎበዝ፣ታታሪ፣የሰው ሐቅ የማይነካ በሰዋች ና በስራ ባልደረባዎች ዘንድ ትልቅ ክብርና ፍቅር ያለው ሰው ነበር ። የሚገርምሽ አባቴ እንደ አንዳንድ ስግብግብ ሃብታሞች ራስ ወዳድ እና ከአላህ መንገድ የወጣ አነበረም እኔ እና እሱ መሐል ደግሞ የተለየ ፍቅር እና ከእናቴ የበለጠ ግንኙነት ነበረን ከእናቴ ጋር ግን ብዙም የጠበቀ ቅርበት አነበረንም ም/ም ደግሞ ከአባቴ ጋር ምክንያቱን ባላውቅም ሁሌ ቀን እና ማታ ስትጨቃጨቀው ሁሌም ስትጮህበት ነበር የማየው ለእኔም እንደ እናት አትቀርበኝም ነበር።እኔ ከአባቴ ውጪ እንደወንድም የምቀርበው አብረን ያደግነውን ኢምራንን ነበር ኢምራን ከኛ ቤት አጠገብ ይኖሩ የነበሩ የአባቴ ወንድም (የአጎቴ) ልጅ ነበር ከእኔ በ 2ዓመት ይበልጣል ። ኢምራን ሁሌም አብሮኝ ነበር ሚሆነው ለሱ የተለየ የወንድምነት ፍቅር ነበረኝ እሱም እንደዛው።አባቴ ከ10ዓመቴ በኋላ የግል ዑስታዝ ቀጠረልኝ ሁሌም ከ ቀለም ትምህርት ይበልጥ ወደ ዲን ትምህርት እንዳተኩር ነበር ግፊት ሚያደርግብኝ እኔም እሱ ነበር ፍላጎቴ እናም በ 13 አመቴ ነበር ኻፊዘል ቁርዐን የሆንኩት (ቁርዓኑን በቃሌ የያዝኩት) በ 17 ዓመቴ ደሞ የተለያዩ ኪታቦችን እና የቁርዓን ሙሉ ትርጉሞችን በቃሌ መሸምደድ ቻልኩኝ ያለ ማንም ግፊት በራሴ ፍላጎት ጅልባብ ለበስኩኝ። አባቴ እና እኔ ደስተኛ ብንሆንም እናቴ ግን የቀለም ትምህርቴ ላይ ትኩረት አለመስጠቴ ሁሌም ያበሳጫትና ከአባቴ ጋር ያጨቃጭቃት ነበር።አንድ ቀን አይቻቸው ማላውቃቸው ሰዎች ወደ ቤታችን መጥተው ለአባቴ እና ለእናቴ የሆነ ወረቀት ሰጥተዋቸው ሄዱ ወረቀቱን ሲቀበሉ አባቴ ምንም አልመሰለውም ነበር እናቴ ግን በድንጋጤ እጇ ተንቀጠቀጠ አባቴ ላይ በሃይለኛው መጮህ ጀመረች እንድትረጋጋ በቀስታ ቢነግራትም ምንም መረጋጋት አልቻለችም ምን እንደተፈጠረ ብጠይቃቸውም ምንም መልስ ሊሰጡኝ አልቻሉም በመጨረሻም እናቴ ጥላን ወደ ቤት ገብታ ሻንጣዋን ማዘጋጀት ጀመረች አባቴ ተከትሏት ገብቶ ተረጋግተው ቁጭ ብለው እንዲያወሩ ቢጠይቃትም ጆሮ ዳባ ብላ ሻንጣዋን እየጎተተች ወጣች እኔ እና አባቴ እየተከተልን ተማፀናት አባቴ እግሯ ላይ ወድቆ ሲለምናት ገፍትራው ጥላን ሄደች። አባቴ አሳዘነኝ ውስጤ በጣም ተሰበረ ተንበርክኬ ቤታችን ውስጥ የገባውን ሴጣን አላህ እንዲያወጣልን ዱዓ አደረኩኝ እናቴን እንዲመልስልኝ ተደፍቼ አለቀስኩኝ አባቴ ተነስቶ መጣ እና አቀፈኝ አንገቱ ውስጥ ተወሽቄ አለቀስኩ አባቴም እራሴን እንዳጠነክር እና ጎበዝ እንድሆን ሁሌም በአላህ ተስፋ እንዳልቆርጥ ነገረኝ ምን እንደተፈጠረ ስጠይቀው ከትንሽ ቀን በኋላ ይሄን ቤት ትተን እዚህ ሰፈር አከራይተነው የነበረው ማለት አሁን የምንኖርበት ቤት እንደምንሄድ ወደፊት ሁሉንም ነገር እንደምደርስበት ነገረኝ። ከትንሽ ቀናት በኋላ ቤቱን ለቀን እዚህ መጣን እናቴ ከሄደች በኋላ በቀን በቀን ይመጡ የነበሩት አጎቴ እና ኢምራን ድራሻቸው ጠፋ ስለ እናቴም ስለ እነሱም አንድም ነገር ሰምቼ አላውቅም ነበር አባቴም እሷ ጥላን ከሄደች ጀምሮ ምንም ጤንነት ተሰምቶት አያውቅም ሁሌም እራሴን ያመኛል ይለናል ብዙ ጊዜም ያዞረው ነበር።ከአንድ ዓመት በኋላ አባቴ የአልጋ ቁራኛ ሆነ እኔና አብራን ወደዚህ የመጣችው ኻዲማችን እሱን ለማሳከም ሆስፒታል ስንወስደው ዶክተሮቹ የአባቴ በሽታ የጭንቅላት ዕጢ እንደሆነና ባፋጣኝ ውጪ ሄዶ መታከም እንዳለበት ነገሩን ለሱም ብዙ ብር ተጠየቅን ነገር ግን ያሉንን ገንዘብ ማግኘት አልቻልንም ምክንያቱም ያለን ሙሉ ሃብት ተመናምኗል ያለንን ሁሉንም ነገሮች ሸጥን ሆኖም ዶክተሮቹ ያሉንን ገንዘብ ግማሹን እንኳ ማግኘት አልቻልንም አባቴ የሚያውቃቸው ለክፉ ቀን ለደረሰላቸው ሰዎች ሄጄ እያለቀስኩ ብለምናቸውም አብዛኛዎቹ ፊታቸውን አዞሩብኝ አንዳንዶቹ ግን ከ 2000 ብር በላይ ሊሰጡኝ አልቻሉም በመጨረሻም ወደ አጎቴ ጋር ሄድኩኝ እሱ ግን የለም አስብሎ ከውጪ መለሱኝ እናቴን ፍለጋም ብዙ ኳተንኩ ሆኖም ላገኛት አልቻልኩም የማረገው ግራ ገባኝ ያለንበት ቤት እንዲሸጥ ለአባቴ ብናማክረውም"በፍፁም ከሸጣችሁት አፉ አልላቹም" አለን አባቴን በገንዘብ ምክንያት ላጣው መሆኑ አንገበገበኝ ምነው ስቃዬን አበዛከው ብዬ ፈጣሪዬን አማረርኩ። አንድ ቀን ከአባቴ አጠገብ ቁጭ ብዬ ሳለው አንዲት ሴት ወደቤታችን ዘው ብላ ገባችና "አሰላሙ አለይኩም"አለች ድምጿ አዲስአልሆነብኝም እኔም አባቴም "ወአለይኪ ሰላም" ብለን ቀና ስንል እናቴ ናት በጣም ደነገጥኩኝ ወድያሁኑ አባቴን ሳየው በደስታ ፊቱ ፈክቷል "አልሃምዱሊላህ መጣሽልኝ ብሎ "ቀና ለማለት ሲሞክር ሮጣ ሄዳ አቀፈችው እና ማልቀስ ጀመረች እኔ ቆሜ እንባዬን እያፈሰስኩ አየዋቸው ከረጅም ደይቃ በኋላ አባቴ ነይ አለኝና አፉ እንድንባባል ጠየቀኝ በጣም ገረመኝ የት እንደሰነበተች እንኳን ሳይጠይቃት ስቆ ተቀበላት እኔም እሱን ላለማስከፋት እሺ ብዬ አቀፍኳት ግን ውስጤ ቂም ቋጥሮባታል ።አባቴ ያለበትን ነገር እንደሰማችና ነገሁኑ እንደምናሳክመው እየነገረችን አባቴ ማጣጣር ጀመረ ተደናግጠን ከበብነው "አባዬ አባዬ" ብለው አልሰማ አለኝ "ሁሉንም አፉ ብያለው አፉ በሉኝ ፍርዶውስን አደራ አደራ" ብሎ ሸኻዳ እየያዘ ሩኹ ወጣ። ሃዘኑ በጣም ጎዳኝ እናቴ የገደለችው እስኪመስለኝ ለዓይን አስጠላችኝ።ለቅሶ ላይ ብዙ ባለሀብቶች ተገኙ እነሱ ባለቀሱ ቁጥር እኔ በግርምት ስስቅ "ምፅ ይህች ልጅ ጭንቅላቷ ተነካ" እያሉ ይጠቋቆሙ ነበር።አጎት ተብዬ ግን በራችንን ረግጦት አያውቅም ነበር።ቀናቶች በሄዱ ቁጥር ቤታችንን የሞላው ሰው እየቀነሰ መጥቶ የሰፈር ሰዎች ብቻ ቀሩ ለምን እንደሆ ባላውቅም ሁሉም ይጠቋቆሙብኝ ነበር አንድ ቀን መንገድ ላይ እየሄድኩኝ ኢምራንን አገኘሁት "እንዴ ፍርዲ" ብሎ መጥቶ ተጠመጠመብኝ እኔም ከእላዬ ላይ ገፍትሬ እስካሁን የት እንደነበር ስጠይቀው ከቤት ተጣልቶ የራሱን ቤት ተከራይቶ እንደሚኖር ነገረኝ እና ቤቱን ካላሳየሁሽ አትሄጂም ብሎ ያዘኝ እኔም ተስማምቼ አብሬው ሄድኩኝ። ቤቱ ደስ ይላል ባለ ሁለት ክፍል ናት ነገር ግን ዝብርቅርቁ ወጥቷል "ምን ሆነክ ነው ምንድነው ሚመስለው ቤትክ ብዬ"ጅልባቤን አውልቄ ሳፀዳ በግርምት አየኝ እና"ፍርዲ ትልቅ ልጅ ሆንሻ እስካሁን ቤት መሆንሽ ይገርማል እኔ እኮ ቤተሰቦችሽ እንዳልሆኑ ካወቅሽ በኋላ አብረሻቸው ምትኖሪ አልመሰለኝም ነበር"ሲለኝ ሰውነቴን ነዘረኝ "ምንድነው ምቀባጥረው"ብዬ አፈጠጥኩበት "ምነው በሱ ምክንያት አደል እንዴ የተጣሉት እናትና አባትሽ አለኝ" ጅልባቤን እዛው ትቼው እየሮጥኩ ሄድኩ።ቤት ስገባ እናቴ ከሰፈር ሴቶች ጋር ነበረች ጎትቼ መኝታ ክፍል አስገባዎት እና "እናንተ አባትና እናቴ አደላችሁም?አዎ ወይ አይ በይኝ "ብዬ አፈጠጥኩባት በጣም ደነገጠች "ፍርዲ ምን መሰለሽ"ስትለኝ "ምንም አታስረጂኝ አዎ ወይ አይ በይ" ብዬ ጮህኩኝ ሁሉም ሰምቶ ወደኛ መጡ እናቴም "አዎ" አለችኝ በሩን በርግጄ ስወጣ እናቴ ከኋላ ተከትላ ስትይዘኝ ገፍትርያት ወጣው ሁሉ ነገር አስጠላኝ ሂጃቤን ጣልኩት በቲሸርት እና በሱሪ ብቻ ሆኜ እግሬ ወዳመራኝ ሄድኩ እምባዬ የለም በቃ ውስጤ ሲደማ ተሰማኝ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ፈጣሪዬን ጠላቴ አደረኩት።አካባቢው ላይ የነበረው ግሮሰሪ ገባው እና ሰዎ


ሁለት ገፅታ (ክፍል ሦስት)
(በኹሉድ ኑሪ)

....ሁለታችንም ሮጠን ወደዚያው ሄድን። ስንቀርብ የወደቀችው ሴት መሆኗን አወቅን ስለጨለመ ግን ማንነቷን መለየት ባንችልም እኔ ግን ፍርዲ ትሆናለች ብዬ ነበር የገመትኩት እጇ በደም ተለውሷል አንስተናት ወደ Hospital ሄድን የገመትኩት ልክ ነበር ልጅቷ ፍርዶውስ ናት ፊቷ በላልዟል ዶከተሮች ተቀብለውን ወደውስጥ አስገቧት እኔ እና ዓሊም ገንዘብ ለመክፈልና ካርድ ለማውጣት ሄድን ካርድ መዝጋቢዋ "የpatientዋን ስም"ስትለኝ "ፍርዶውስ" አልኳት እና ማልቀስ ጀመርኩ ዓሊም እሷ እንደሆነች ሲያውቅ በጣም ደነገጠ እንድረጋጋ ተቆጥቶ ተናገረኝ።የካርዱን ጣጣ እንደጨረስን ወደ ፍርዲ ስንሄድ ዶክተሩ ቢሮው አስጠራንና "ፍርዶውስ እራሷን ለማጥፋት ምን እንዳነሳሳት ጠየቀን" ሆኖም መልሳችን "አናውቅም"ነበር እሱም ፍርደውስ የእጅ ደምስሯን ቆርጣው ቢሆንም በጊዜ ይዘናት ስለመጣን ሕይወቷን መታደግ እንደቻልንና የዚህ አይነት ነገር ዳግመኛ እንዳይፈጠር ወደpsychiatry ይዘናት መሄድ እንዳለብን እና ሲነጋ ይዘናት መሄድ እንደምንችል ነገረን።እኔ እና ዓሊ እዛው አድረን ሲነጋ ፍርዲን ወደ እኛ ቤት ይዘናት ሄድን ይኼ ሁሉ ሲሆን እሷ አንድም ቃል ከአፏ አልወጣም ስንወስዳት መሄድ፣ስናስቀምጣት መቀመጥ ነበር ስራዋ።እኔ እና ዓሊ ግራ እንደተጋባን ፍርዲም ሳታናግረን መሽቶ ነጋ ዓሊ ጥሎኝ መሄድ ባይፈልግም መሄዱ ግድ ስለሆነበት ወደስራው ሄደ እኔ ግን ይሄን አጋጣሚ ፍርዲን ለማነጋገር ምቹ ስለሆነልኝ ወዳለችበት ክፍል አቀናው ወደ ክፍሏ በተጠጋው ቁጥር ስቅ ስቅ የሚል ድምፅ ይሰማኛል በጣም ደንግጬ ሮጬ በሩን ስከፍተው ደንግጣ ጋደም ካለችበት አልጋ ብድግ አለች እና እንባዋን በሁለት እጇ ጠረገችው። "ውይ አፉ በይኝ እኔ ኮ ድምፅ ስሰማ ምን ሆና ነው ብዬ ሁፍፍ አልሃምዱሊላህ ደህና ነሽ አደል?" አልኳት ፈገግ ብላ ጭንቅላቷን በአወንታ ነቀነቀችልኝ በጣም ደስ እያለኝ"እሺ ምትፈልጊው ነገር አለ?" አልኳት ወድያውኑ ብድግ አለችና በእጄ የያዝኩትን ብር ጠቁማ እጇን ዘረጋችልኝ "ምን ብር ነው ለምንሽ ማለቴ የኔ ቆንጆ ተጎድተሻል እኮ መውጣት አችይም ቢያንስ ትንሽ ጉልበት ማግኘት አለብሽ" አልኳት ጭንቅላቷን ነቀነቀችው ቅር እያለኝ 50 ብር ስሰጣት ከእጄ ምንትፍ አድርጋ ጃኬቷን ደርባ ወጣች እኔ ቢያንስ ከኋላዋ መከተል እንዳለብኝ ተሰምቶኝ በሩን ቀስ ብዬ ዘጋግቼ ከኋላዋ ተከትያት ወጣውና ግራናቀኝ ሳይ ፍርዲ ዛፋ ጋር ቁጭ ብላ እያጨሰች ነው።ቀስ እያልኩኝ ወዳለችበት ተጠግቼ አጠገቧ ቁጭ አልኩኝ የዚህን ጊዜ ነበር ፍርዲ የመጀመሪያ ቃሏን ከአፏ ያወጣችው..የጠየቀችኝን ጥያቄዎች መልስ መስጠት አቃተኝ እውነትም ግን ሕይወት ምንድናት?፣እውነተኛ ደስታ ምንድን ነው?፣ እኔ ማን ነኝ?፣..እኔስ ምንድን ነኝ?፣..ለምን እዚህች ምድር ላይ መጣው?እነዚህን ጥያቄዎች ለራሴ እንድጠይቅ አደረገችኝ ጥያቄው ሲያዩት ቀላል ሲመልሱት ግን ከባድ ነው። ፍርዲ እጇ ላይ ያለውን ሲጋራ ሳብ ሳብ አደረገችና መናገሯን ቀጠለች "ይኼውልሽ አንድ ጥግ ላይ ብቻዬን ተቀምጫለው በልቤ ጮኼ እያለቀሰኩ ነው በዙሪያዬ ሁሉም ሰዎች አሉ ግን ጩኸቴን ለቅሶዬን ማንም የሰማው የለም አንዳንዶቹ በሽተኛ ነች ይሉኛል አንዳንዶቹ ዲዳ ናት ይሉኛል አንዳንዶቹ ዱርዬ ሰካራም ናት ይሉኛል
ግን ማንም በጭራሽ አይረዳኝም የሆነ አለ አደል መናገር ማስረዳት የማልችለው ስሜት አለ በሰውነቴ በእጄ ላይ ለሚፈጠሩት ጠባሳዎች ሀፍረት ይሰማኛል ነገር ግን በሌላ ቀን መልሼ አደርገዋለሁ ታውቂያለሽ እኔ ላስረዳው በማልችለው ነገር ተጎጂ ነኝ ግን እኔነቴን ማንም አያየውም የሆነ የተሰወረ ነገር አለ መሰለኝ እናም በቃ ህመሜን ማንም አያስተውልም እያንዳንዱ ሰው እኮ የማይናገረው የራሱ የሆኑ ችግሮችን ያልፋል እርስ በእርስ ደግ መሆን ቅን መሆን ያን ያህል ከባድ ነው እንዴ? በፊት ልጆች እያለን የሚያስጨንቀን እና የሚያሳዝነን ስሜቶችን ለማጠብ እንባዎቻችን ምቹ ነበሩ ፡፡ ስናድግ ግን የሆነ በጭራሽ በእንባ ሊታጠቡ የማይችሉ በጭራሽ መታጠብ ማይገባቸው የሚያሰቃዩ ትዝታዎች ፣በጣም የሚያሳዝዝኑ፣ የሚጎዱ፣ የሚሰብሩ፣ነገሮች እንዳሉ እንማራለን፡፡ ስለዚህ አንዳንዳንዶቻችን ማልቀስ ስንፈልግ እንስቃለን፣ማውራት እየፈለግን ዝም እንላለን፡፡ ዝም ብለን እየሳቅን ሁሉንም ህመምና ሀዘን እንቋቋማለን ሲበዛና ከአቅማችን በላይ ሲሆን ደሞ ራሳችንን ሱስ ውስጥ እንደብቃለን፡፡" ብላ ማልቀስ ጀመረች። ፍርዲ ልክ ናት ፍርዲ አዋቂ ናት ምትናገረው ነገር በሙሉ ልክ ነው ወላሂ በራሴ አዘንኩ፣ሰው መባሌ አስጠላኝ፣ አንገቴን አስደፋችኝ ከረጅም ዝምታ በኋላ የያዘችውን ያለቀ ሲጋራ ጥላ እጇን ጠራረገችና "ፍርዶውስ" አለችኝ ፈገግ ብዬ "ሰብሪን"አልኳት "ይቅርታ እንግዲህ ብሶቴን ተወጣውብሽ አንዳንዴ አዳማጭ ጆሮ ስታገኚ ገባሽ ደስ ይላል ብቻ አመሰግናለሁ ስላወቅኩሽ ደስ ብሎኛል"ብላ ፈገግ አለች"ፍርዲ እኔ አንቺን ከዚህ በላይ ማወቅ እፈልጋለው ስለራስሽ ብትነግሪኝ ደስ ይለኛል" ስላት "አየችኝ እና እርግጠኛ ነሽ ስለኔ መስማት ትፈልጊያለሽ" አለችኝ ውስጧ ላይ የተሰማት ደስታ ፊቷ ላይ ወጣ በጣም ብዙ ነገር መናገር እንደምትፈልግና እውነትም ጭንቀቷን ብሶቷን ሰምቶ ሸክሟን የሚያቀልላት ሰው እንደምትፈልግ ተረዳሁ "በደስታ ነዋ ለዛውም የምሰማሽ" ብዬ ፈገግ አልኩኝ.....ይቀጥላል

9 last posts shown.

2 177

subscribers
Channel statistics