“ ሮድሪ ለፔሬዝ ቡድን ቢጫወት ወዲያው ባሎን ዶር ይጠየቅ ነበር “ አሌክሳንደር ሴፈሪን
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን የባሎን ዶር ሽልማት ለሮድሪ በመሰጠቱ የቀረበው ቅሬታ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል።
“ የስፖርታዊ ጨዋነት ህግ ባሎን ዶር ከጀመረ ጀምሮ ተተግብሯል “ ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ ሮድሪ በስፖርታዊ ጨዋነት እና በቁጥራዊ መመዘኛዎች ቪንሰስን በልጦታል ይገባዋልም “ ብለዋል።
የማድሪድ ቅሬታ “ እኛ በፈለግነው ካልሆነ “ ከሚል የመጣ ነው የሚሉት ሴፈሪን " ቪንሰስ በየጨዋታው ከዳኛ ፣ ከተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ጋር ያደርግ የነበረውን ተመልሰው መመልከት አለባቸው " ብለዋል።
“ ባሎን ዶር ያሸነፈው ሮድሪ በሰባ ሁለት ጨዋታዎች ያልተሸነፈ ከቪንሰስ በላይ የግብ አድል የፈጠረ እና አስራ ሁለት ጎል ያስቆጠረ ነው።“ አሌክሳንደር ሴፈሪን
“ በተጨማሪ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ እና የውድድሩ ምርጥ ተጨዋች ነው ፕርሚየር ሊግም አሸንፏል " ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።
“ ሮድሪ ለፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ቡድን ቢጫወት ወዲያው ባሎን ዶር ይጠየቅ ነበር “ ያሉት ፕሬዚዳንቱ አክለውም እግርኳስ ከምንም በላይ ስነምግባር እና መከባበር ነው ብለዋል።
@ETHIO_MANCHESTER_CITY@ETHIO_MANCHESTER_CITY