Фильтр публикаций


Репост из: ATC NEWS
#EntranceExam #2017

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች #በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡ በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

👉ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-

1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣

2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።


[የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት]


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


በ20 ለተገረማቹህ ወገንታት እና ህዝብታት

፨ፍሬሽ ማን እያለሁ

👉 ሻይ 1ብር
👉ምግብ 10-15ብር
👉ነጭ ወረቀት የብር ሶስት አራት
👉 ሰላም ባስ 250ብር


ግቢ ውስጥ የኔ ትልቁ ወጪ ሻይ ነበር። ቡና አልጠጣም።ካርድ አልሞላም።


አንደኛ እና ሁለተኛ ዓመት ላይ ምንም ዓይነት ገቢ አልነበረኝም።

ኑሮም በጣም መጦዝ የጀመረው ከኮቪድ በኋላ ነበር ✌️


ባንክ ቤት ተሰልፌ 20ብር ያወጣሁ ሰው ነኝ 😊

#ግቢ




🚍 Help Improve Public Transport in Ethiopia! 🚍
We are developing Derash, a mobile app to solve public transport challenges like:
✅ Long wait times
✅ Overcrowding & safety concerns
✅ No real-time bus tracking
✅ Lack of cashless payment options

💡 Your opinion matters! Take this quick 2-minute survey and help shape the future of public transport.

📣  click the link to participate!

👇👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeW9_gPyh8KfgqN0DDQ1UgIr9lxRL8Thra-oi7k6K60GE5-TQ/viewform?usp=preview

Thank you for your support! 🙌


Management Exit Exam Full Day Schedule.xlsx
308.8Кб
Management Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Tuesday February 04, 2025 (ጥር 27/2017 ዓ.ም)

9.8k 5 50 14 10

Accounting Exit Exam Full Day Schedule.xlsx
301.5Кб
Accounting Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Monday February 03, 2025 (ጥር 26/2017 ዓ.ም)


Репост из: ATC NEWS
ዛሬ ምሽት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አነስተኛ የእሳት አደጋ አጋጥሞ የነበረ ሲሆን እሳቱ በአሁኑ ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋሉን የግቢው ተማሪዎች ነግረውናል።

ከእሳት አደጋው ጋር በተያያዘ ከቤተ-መፃህፍ ለመውጣት በነበረ ጥድፊያ ቀላል ጉዳት ያስተናገዱ ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን የግቢው ተማሪዎች ጨምረው ነግረውናል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


🧐




ይሄ ቲክቶክ ብዙ ልጆችን ማሰብ እንዳይችሉ አድርጓል።

እባካቹህ በምን እንደምትቀልዱ አርቃቹህ አስቡ‼️

ነገ እነዚህ ልጆች ይቅርታ እያሉ ቢነፋረቁም ይቅርታ ላያስጥላቸው የሚችል ከባድ ጥፋት ነው የፈፀሙት😢


Репост из: ATC NEWS
#Update

ማሳሰቢያ - ሁለት ቀን ብቻ ቀረው!

የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ( የ12 ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ስለሆነም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ ካላችሁ በነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን።

⚡️ያልተመዘገበ አይፈተንም❗️


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


ዩትዩብ ላይ የጥሪ ማስታወቂያዎችን ስታዩ ቪድዮው የተለቀቀበትን ቀን ተመልከቱ 🙏


Репост из: ATC NEWS
#EntranceExam #2017

የ2017 ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ 8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን ይሆናል።

👉እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጀ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጐ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ይሆናል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


Wollo University Mid Exam schedule


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


አዲሱ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሜኑ


አዲሱ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሜኑ


Репост из: ATC NEWS
#Update #MealMenu

ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል‼️

ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ያስተላለፈው የተማሪዎች የምግብ ሜኑ መግለጫ 👇

(ሚንስትር ዴኤታው)

[የምግብ ሜኑውን ከምስሉ ይመልከቱ]

Click

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ለዘንድሮ ፍሬሽማን ናቹራል ተማሪዎች ብቻ 👂

@muedu

Показано 20 последних публикаций.