ADDIS INSIDER - ETH


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና የተረጋገጡ እና አዝናኝ የሆኑ መረጃዎች የሚቀርቡበት ነው!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡

አባታቸው ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእ ኃረያ ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በአንድ ወቅት ታዳጊው ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለስብከተ ወንጌል እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡

ወላጆቻቸው ካረፉ በኋላም ንብረታቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ሲወርዱ ገመዱ ቢበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን አጥምቀዋል፤ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገዳም አስቦ ዋሻ በዙሪያቸው ስምንት ጦሮች ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት በማሰብ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት አንድ እግራቸው ተሰብራል፡፡

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ለምነዋል፡፡ ከዚህ ዓለም ድካም በሚያርፉበት ነሐሴ 24 ቀንም ጌታችን ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጥቶ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ሁሉ ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉና ከበረከታቸው እንድንሳተፍ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
 




ኢራን አሜሪካ መስፈርቶቿን እስክትሟላ ድረስ የሆርሙዝ መስመር  ተዘግቶ እንደሚቆይ ገለጸች
 
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህር መስመሩን  መልሶ መክፈት ዋነኛ ግቡ እንደሆነ ሲናገር፣ አሜሪካ በበኩሏ ትኩረቷን በኒውክሌር ድርድሩ ላይ ማድረጓን ቀጥላለች።
 
የኢራን የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሞሐመድ ባገር ቃሊባፍ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ የቴህራንን የሰባት ቀን ዕቅድ እስካልተቀበለች ድረስ የሆርሙዝ መስመር ተዘግቶ ይቆያል። 

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው፣ ቴህራን ወታደራዊ ዝግጁነቷን እንደጠበቀች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሔ ለማግኘት እየሰራች መሆኑን አረጋግጠዋል፤ አሜሪካ ተጨማሪ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ ግን ከቀድሞው በላይ "የበለጠ ዝግጁ" መሆኗን አስረድተዋል።
 
በየካቲት ወር አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ያካሄዱትን ጥቃት ተከተሎ፣ ከዓለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት አንድ አምስተኛው የሚጓጓዝበት ይህ የባህር ወስጥ ከሰባት ወራት በላይ መደበኛ እንቅስቃሴው ተስተጉሏል። 

በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ወገኖች የባህር መስመሩን መክፈት ቅድሚያ ይሰጥ ወይስ የኒውክሌር ድርድሩ በሚለው ነጥብ ላይ አለመግባባት ውስጥ ይገኛሉ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
 
የኢራን ዋና ተደራዳሪና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ የውሃ መንገዱን መልሶ ለመክፈት የቀረበውን የቴህራንን የሰባት ቀን ዕቅድ እስክትቀበል ድረስ የሆርሙዝ መስመር እንደተዘጋ ይቆያል።
 
ከኢራን መንግሥት ጋር ቁርኝት ያለው የኑርኒውስ (Nournews) የዜና ወኪል ሞሐመድ ባገር ቃሊባፍን ጠቅሶ እሁድ እንደዘገበው፣ አሜሪካ ለኢራን ዲፕሎማሲያዊ ጥያቄ ምላሽ ከሰጠች ከጥቂት ቀናት በኋላ በአደራዳሪዎች  በኩል "አንዳንድ የውሳኔ ሃሳቦችን" አቅርባለች።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


ዜና ዕረፍት!! የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
ምንጭ ድሬቲዩብ
ነፍስ ይማር!!




ኤርትራ ፀረ ድሮን መትከሉ ታወቀ

ኤርትራ በአክሱም እና አድዋ አካባቢ ፀረ ድሮን መትከሉ ታወቀ።

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የመካናይዝድ ጦሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጠጋ ይገኛል።

አሜሪካ ዛሬ ባወጣችው አስቸኳይ መግለጫ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ሁሉቱ ሀገራት በሰከነ መንገድ ጉዳዩን እንዲመለከቱ ጥሪ አቅርባለች።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


የቅዱስ ገብርኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን፤ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን🙏

“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡

አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡  

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የ2019 ዓ/ም የኢሬቻ 'ሆረ አርሰዴ' በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገልጿል።

#Irreechaa2019

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


ስልክ እና ኢንተርኔት መስራት ጀምሯል‼

ለቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት በመቀሌ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም መስራት መጀመሩ ተሰምቷል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ የሞባይል የስልክ ጥሪ ድምፅ እና የሞባይል ዳታ (ኢንተርኔት) አገልግሎት በአሁኑ ሰዓት መስራት ጀምሯል።

የአገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ የመመለስ አሁንም በስፋት እየተሰራ ነው ተብሏል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


በኢትዮጵያ እና እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረው “ድንበር ተሻጋሪ ውጥረት”፤ በመላ ቀጠናው ላይ “ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል” አሜሪካ ስጋቷን ገለጸች።

የአፍሪካ ቀንድ ሌላ ወታደራዊ ግጭት እና ሰብአዊ ቀውስ የመሸከም አቅም እንደሌለው የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳስቧል።

ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ትላንት ቅዳሜ መስከረም 23፤ 2019 ለሊት ባወጣው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሚቀሰቀስ ግጭት ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ ጥቅሞች ላይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር የምታደርገውን ትብብር “አደጋ ላይ ሊጥል” እንደሚችል ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት “ድንበር ተሻጋሪ” ሲል የጠራው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፤ ሁለቱ ሀገራት የጎረቤቶቻቸውን “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት” እንዲያከብሩ አሳስቧል።

ሀገራቱ ከግጭት ራሳቸውን “በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያቅቡ” እና በ2010 ዓ.ም በተፈራረሙት የሰላም ማዕቀፍ መሰረት “ወደ ውይይት እና ትብብር እንዲመለሱም” ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

“በውይይት የሚገኝ ሰላም ለዘላቂ ደህንነት፣ ለኢኮኖሚ እድገትና ለብልጽግና ብቸኛው መንገድ” መሆኑን መስሪያ ቤቱ በመግለጫው አስገንዝቧል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


በአድዋ ከተማ የሚገኙት ፓን አፍሪካን ሆቴል እና ሸዊት ሆቴል የድሮን ጥቃት ተፈፀመባቸው፡፡

በማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚያሳዩት፤ ጥቃቱ በእንዲህ መልኩ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


"አሜሪካን የሚያስደነግጡና እስካሁን በውጊያ ላይ ያላዋልናቸው የጦር መሳሪያዎች አሉን!" - ጄኔራል ሞስጣፋ ኢዛዲ

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኮር ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል ሞስጣፋ ኢዛዲ አገራቸው በምድር፣ በአቪዬሽን፣ በአየር መከላከያ እና በባህር ኃይል ዘርፎች አሜሪካን ሊያስደነግጡ የሚችሉ አዳዲስ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን ማልማቷን በይፋ አስታወቁ።

ኢራን አዲስ ጥቃት ከተፈጸመባት ለአሜሪካ የሚሆኑ አይገመቴ ወታደራዊ አቅሞች እንዳሏት ያስጠነቀቁት አዛዡ፣ ከነዚህ ስልቶች መካከል የተወሰኑት ቀደም ብለው ወደ ሥራ መግባታቸውንና ሌሎቹ ደግሞ ለወደፊት ግጭቶች ተዘጋጅተው የተቀመጡ መሆናቸውን አብራርተዋል።

አያይዘውም የአሜሪካ ኃይሎች የኢራንን የባሊስቲክ ሚሳኤል አቅም በመፍራት ከፋርስ ባሕረ ሰላጤና ከኦማን ባሕር ከ500 ኪሎሜትር በላይ ወደ ኋላ ማፈገፈጋቸውን ጠቁመዋል።

ይህ የከፍተኛ ወታደራዊ ማስጠንቀቂያ የተሰማው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሁን ቀደም አሜሪካ ከኢራን ጋር የሚኖራትን ፍልሚያ "በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በቅርቡ" እንደምትረታ ከተናገሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


አነጋጋሪው የጄኔራል ሙሁዚ ንግግር!!

ኡጋንዳ ጥያቄ ከቀረበላት ወደ ኢትዮጵያ ጦር ለመላክ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች‼️

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይነሩጋባ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር ተያይዞ መደበኛ ጥያቄ ካቀረበ ኡጋንዳ ወታደሮቿን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።

ጄኔራል ካይነሩጋባ በኤክስ (X) ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ኡጋንዳ ባለው ግጭት ወቅት ለኢትዮጵያውያን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው፣ በኢትዮጵያ አመራሮች በኩል ጥያቄ ከተቀረበ የኡጋንዳ ሕዝባዊ መከላከያ ሠራዊት (UPDF) እንደሚሰማራ ተናግረዋል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ታኅሣሥ 24 ቀን 1212 ዓ.ም ከካህኑ አባታቸው ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድና በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ተወለዱ፡፡ 

ወላጆቻቸውም ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ 

ቅዱስ ሚካኤልም ከአዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደተመረጡ፣ ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ያላቸውን ንብረት ዅሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው “አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተ ተውኹልህ” በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳምም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ከዚያ ሲወርዱ ገመዱ ገመዱ ሲበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በደብረ ሊባኖስ ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባትም በዙሪያቸው ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ለ22 ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት የአንድ እግራቸው አገዳ ተሰብራል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን የዐፅም ስባሪ አክብረው አኑረውታል፡፡ እግራቸው ከተሰበረ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ሌሊትና ቀን ጸንተው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ጥቂት ውኃ እንኳ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ እንደ ነበረ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የሚያርፉበት ቀን ሲቃረበ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጣ፡፡

በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው፣ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም “በሰው እጅ የማይለካውን ይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ” በማለት የጸጋ ልብስ አልብሷቸው፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ 24 ቀን በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ጌታችንም ነፍሳቸውንም በክብር ተቀብሏታል፡፡ የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
 
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
 




በትግራይ ክልል ከቀበሌ ጀምሮ አዳዲስ የአስተዳደር መዋቅር ይደራጃል - አብረሃም በላይ (ዶ/ር)
‎
‎አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፤ የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት እየሰራ ነው።
‎
‎በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤት ለማምጣት ሕዝቡ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት አዲስ መዋቅር እየተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።
‎
‎በአሁኑ ወቅት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ክልሉን ከሕገ-ወጥ ኃይሎች እያጸዳ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ይህንን ተከትሎም ከቀበሌ ጀምሮ አዳዲስ የአስተዳደር መዋቅሮች በሕዝቡ ተሳትፎ ይደራጃሉ ብለዋል።
‎
‎የአስተዳደር መዋቅሩን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


ለሻዕቢያ በእጥፍ ምላሽ ይሰጠዋል - አብርሃም በላይ‼️

በሰሞኑ ውጊያ የሻዕቢያ ሰራዊት መሳሪያ ይዞ፣ ግንባር ወስዶ፣ የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ከህወሓት ጋር አብሮ ተዋግቷል። 

በርካታ መሳሪያ ተማርኳል፣ የሞቱም አሉ።

ሻዕቢያ ለዚህ ተግባሩ በእጥፍ ምላሽ ይሰጠዋል፣ የአንድን ሀገር መንግስት ከባንዳ ጋር አብሮ መውጋት ምን ሊያስከትል እንደሚችል በምላሹ ያገኘዋል'ሲሉ ዶክተር አብርሃም በላይ ከመንግስት ሚዲያዎች በነበራቸው ቆይታ ላይ ተናግረዋል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH


የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል 

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡ 

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡ 

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል  ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132


የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921



Показано 20 последних публикаций.