🛑
ከፊል ማስታወሻ እና ማሳሰቢያዎች!!
✅ነገ የዐረፋ ቀን በመሆኑ በዋነኝነት ሦስት ዋና ዋና ዒባዳዎች ይደረጋሉ።
1ኛው,
ጾም [የሁለት ዐመት ወንጀል ያስምራል።]
2ኛው,
ዱዐ [በየትኛውም ቀን ከሚደረገው በበለጠ ተቀባይነት አለው።]
3ኛው,
የተገደበው ተክቢራ [ከፈጅር ጀምሮ ከሁሉም ፈርድ ሰላቶች በኋላ ይደረጋል።]
❌በነገው ዕለት "የሴቶች ዐረፋ" በሚል የሚከበር በዓል ወይም "ለሞቱ ሰዎች" ተብሎ የሚታረድ እርድ የለም።
💫"ለሞቱ ሰዎች ሰደቃ" ተብሎ ከሆነ በዚህ ቀን የሚታረደው፦
መረጃ የሌለው ዒባዳ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም, ባለቤቱ ላይ ተመላሽ ይሆንበትና የወንጀል ተሸካሚ ይሆናል።
💫"ካልታረደ የሞቱ ሰዎች ተቆጥተው ንብረት ወይም ልጅ ላይ አደጋ ያደርሳሉ" በሚል ስጋት ከሆነ የሚታረደው፦
በአላህ ላይ ማጋራት ስለሆነ ባለቤቱ ከእስልምና የሚያስወጣ ተግባር ይሆናል።
✅የዒድ ቀን ከንጋት ጀምሮ ያማረ ልብስ በመልበስ ልጆችና ሴቶች ጨምሮ ሁሉም ወደ ዒድ መስገጃ መውጣት አለበት።
❌ሴቶች ወደ ዒድ መስገጃ ሲወጡ ወደ ፊትና ተጣሪ ከሆኑ ክፉ አለባበሶች መራቅ እና ከሽቶ መቆጠብ አለባቸው።
❌ወደ ዒድ መስገጃ በሚደረገው ጉዞ ወንዶች እና ሴቶች መሃል ንክኪ በሚፈጥር መልኩ መገፋፋት መኖር የለበትም።
❌ሴቶች ወደ ዒድ መስገጃ ሲሄዱም ይሁን መስገጃ ቦታው ላይ ሆነው ድምፃቸው ለወንዶች በሚሰማ መልኩ ተክቢራ ማድረግ የለባቸውም።
✅የዒድ ቀን: የዒድ ሰላት እስከ ሚሰገድ ድረስ መጾም የተወደደ ሱና ነው።
💫ከተቻለ እንደተሰገደ ኡዱሒያው ይታረድና በእሱ ስጋ ይፈጠራል።
✅ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ከመጓጓዣ ይልቅ በእግር መሄዱ የተወደደ ሱና ነው።
✅የዒድ ሰላት ተሰግዶ ሲመጣ የተኬደበት መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ መመለስ የተወደደ ሱና ነው።
✅የዒድ ሰላት ከተሰገደ በኋላ በጊዜ ቶሎ ብሎ ኡዱሕያ ማረድ የተወደደ ሱና ነው።
💫ከዒድ ቀጣይ ባሉ ሦሥት ቀናቶች የዒዱ ቀን ጨምሮ በአራቱ ቀናት ኡዱሒያ ቢታረድ ያብቃቃል።
✅ከዒድ ቀጥሎ ባሉ ሦሥቱ ቀናቶች አይጾምም: ይበላል, ይጠጣል አላህም በብዛት ይወሳባቸዋል።
✅ኡዱሒያው ሲታረድ አባወራው በራሱ እጅ ቢያርደው የተወደደ ነው።
✅ማረድ ባይችል ወይም ባይፈልግ: ቢያንስ ሲታረድ ቆሞ ማየት እና እቦታው ላይ መገኘት አለበት።
✅ከታረደው እርድ በቲንሹም ቢሆን እንኳ ለምስኪኖች ወይም ለደሀዎች ሰደቃ መሰጠት አለበት።
❌ከታረደው የኡዱሒያ ስጋ መሸጥ አይፈቀድም።
💫የሚያዘጋጀው ተቀጣሪ ባለሙያ ቢሆንም ለእሱ ከኪስ መክፈል እንጅ ከእርዱ ቆዳ ወይንም ሌላ ነገር ሰጥቶ ማመቻቸት አይፈቀድም።
✅ኡዱሒያ ለማረድ ከመጣሉ በፊት ማረጃ ቢላው በደንብ መሞረድ እና እንስሳው ሳይሰቃይ መታረድ አለበት።
❌እንስሳው ለእርድ ከቀረበ በኋላ ሰው ተሰብስቦ የሚደረግ ዱዐም ይሁን የሚጫጨስ እጣን የለም።
✅አራጁ ልክ ሲያርድ "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" ማለት አለበት።
💫"ቢስሚላህ" ረስቶ ካረደው: ትልቅዬ ሰንጋ ቢሆን እንኳ በክት ነው መብላት አይፈቀድም።
💫"አላሁ አክበር" ግን በተወዳጅነት ነው የሚባለው: ቢረሳው ምንም ችግር የለበትም።
✅በመጨረሻም: ሙስሊሞች እርስ በእርሳቸው ሲገናኙ………
🤝ዒድ ሙባረክ!!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!!
በመባባል ተጨባብጠው ደስታቸውን ማንፀባረቅ አለባቸው!!
ከወዲሁ
✋ዒድ ሙባረክ!!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሕ አል_አዕማል!!
🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante
👆
👇
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio