እብዱ ዮሐና
....................ምዕራፍ ስምንት(11)
ታላላቅ ሰዎች - ለክብራቸው በሚመጥኑ ቃላት፣ በመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች፤ እንደዚሁም በዝማሬዎች እያወደሱ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተቀበሏቸው፡፡
አዲሱ ቤተ-ክርስቲያን ከተሰራበት ቦታ ሲደርሱም፣ በወርቅ የተሸለመ የቀሳውስት ካባ ተደረበላቸው፤ በጌጣጌጦች የተንቆጠቆጠ አክሊልም በራሳቸው ላይ ተደፋላቸው፡፡ ከዚያም ድንቅ የእጅ ሙያ ጥበብ የተገለፁበት በውድ የከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ ቆልማማ ዘንግ ተሰጣቸውና ቀሳውስቱን ከኋላ አስከትለው በአንድ ላይ እያዜሙና እየዘመሩ ቤተ-ክርስቲያኑን ዞሩት፡፡ ከሁሉም አቅጣጫዎች መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን ጢስና አየሩ ላይ የሚዋልል ጥርዥ፣ ብርዥ የሚል ነበልባል ያላቸው በርካታ ጧፎች የያዙ ዲያቆናት አጅበዋቸው ይታያሉ፡፡
በዚያ ሰዐት ዮሐና ከእረኞቹና ከአፈር ገፊዎቹ መሀል ቆሞ ሀዘን ባጠላባቸው ዓይኖቹ ይህንን ደማቅ ትዕይንት በአንክሮ ይመለከታል፡፡ በአንድ ወገን ከሀር የተሰሩ ካባዎችን፣ የወርቅ እጣን ማጤሻዎችን፣ በጌጣጌጦች የተሽቆጠቆጠ አክሊልንና በውድ የከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ ዘንግን፤ በሌላ ወገን ደግሞ ለዚህ በዓል ደስታና የምርቃት ሥነ-ስርዓት እገዛ ለማድረግ ከትናንሽ መንደሮችና ሰፈሮች የመጡትን በከፋ ድህነት ተዘፍቀው የሚኖሩት ደሀና ምስኪን ሰዎችን ሲያይ - ጥልቅ የሀዘን ስሜት አድሮበት በምሬት በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ በአንደኛው ወገን በከፋይና በሀር ልብሶች ውስጥ ያለው ምቾትና ስልጣን፤ በሌላኛው ወገን ደግሞ በተቀዳደደ ብጭቅጫቂ ቡትቶች ውስጥ ያለው ችጋርና መከራ ወለል ብለው ታዩት፡፡
እነዚያ በዓርማና ሜዳሊያ አሸብርቀው ራቅ ብለው የቆሙት ሀብታም «አስተዳዳሪዎች» ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የሚፀልዩት ሰሀብትና ለስልጣናቸው ሲሆን፣ ደስ የሚሰኙትም በዚያ ከንቱ ክብራቸው ነው፡፡ እነዚህ ዝቅ ብለው ቆመው ደረታቸውን እየደቁ ጠልቆ ከሚገኘው የተሰበረ ልባቸው የሚወጣ እውነተኛ ፀሎት የሚፀልዩት ጐስቆላ፤ ትሁትና በድህነት የሚማቅቁ የመንደሯ ነዋሪዎች ግን ደስ የሚሰኙት በትንሳኤ ውስጥ ባለው ዘላለማዊ ህይወታቸው ነው፡፡
የአስተዳዳሪዎቹና የመሪዎቹ ስልጣን በአረንጓዴ ለምለም ቅጠሎች እንደተሞላው ረዥም ዛፍ ሲሆን፣ የህዝቡ ህይወት ግን መርከባ በማዕበል ተመትታ በሞት አፋፍ ላይ እንደደረስ ካፒቴን ነው፡፡ እናም መቅዘፊያዋ ተሰብሮባት፣ ሸራዋ - በንፋስ ተቀድዶባት፣ በተቆጣው የባህሩ ውሃና በአስፈሪው አውሎ ነፋስ ብቅ፣ ስጥም እንደምትል መርከብ በፍርሃት ሰጥ ለጥ ብለው የሚገዙ ታዛዥ ጭሰኞች ናቸው::
ለመሆኑ ከከፋ የጭቆና አገዛዝና ከጭፍን ታዛዥነት የትኛው ይሆን የሚቀድመው? የትኛው ነው የቱን የወለደው? የጭቆና አገዛዝ በታችኛው መሬት ላይ ካልሆነ በስተቀር የማያድግ ጠንካራ ዛፍ ይሆን? ወይስ ጭፍን ታዛዥነት ከእሾሆች በስተቀር ምንም የማይበቅልበት ምድረ-በዳ ሆኖ ይሆን?
..........ይቀጥላል..........
👍👍👍👍👍👍👍👍
https://t.me/Asresee