“ቀድመውኝ አይደለም፤ ዘግይቼም አይደለም። ቀድሜያቸውም አይደለም፤ ወይም እነሱ
ዘግይተው።
… ትክክለኛው ሰዐት ላይ ነኝ።” በል!
:
ምናልባት አንዱ በ20 ዓመቱ ያገባ ይሆናል፤ ለመውለድ አስር አመታትን ይወስዳል።
አንዱ በ30 ዓመቱ ያገባል፤ በዓመቱ ይወልዳል።
አንዷ በ22 ዓመቷ ታገባለች፤ ጥሩ ባል አይደለም።
ሌላኛዋ በ34 ዓመቷ ታገባለች፤ ደስተኛ ትዳርንም ትመራለች።
ከፊሉ በ22 ዓመቱ ይመረቃል፤ ስራ ለማግኘት 5 ዓመታት ይፈጅበታል። ከፊሉ በ27 ዓመቱ
ይመረቃል፤ ከመውጣቱ ስራን ያገኛል።
ሌላው በ25 ዓመቱ የድርጅት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፤ በ40 ዓመቱ ይሞታል።
ሌላኛው በ50 ዓመቱ የድርጅት አስኪያጅ ይሆናል፤ በ90 ዓመቱ ይሞታል።
:
…
ጊዜህን ብቻ ተከተል።
የቀደሙህ ወይም የዘገየህ አድርገው ይስሉሀል።
አንተ ከማንም አልተቀደምክም፤ ከማንም አልዘገየህም። ፈጣሪ በፈቀደልህ ጊዜ ብቻ
እየሄድክ ነው። ይህንን እወቅ።
የአዕምሮ ረፍትና እርጋታህን ይዘህ ኑር።
:
ጊዜ
በፈጣሪ እጅ ያለ መንገድ ነው። እንደፈለገ ያስኬደዋል። የፈለገውን ላንተ በፈለገልህ
ሰዓት ያደርግልሀል።
«ነገሩም ሁሉ በእርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።».....
ተመስገን🙏🙏🙏..........
@Meklite21 💚💛❤
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉት👇👇👇
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee