እብዱ ዮሐና
....................ምዕራፍ ስምንት(12)
. የቤተ-ክርስቲያኑ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ባለበት በዚህ ሰዓት ዮሐና በእነዚህ አሳዛኝና ስቃይን የሚፈጥሩ ሀሳቦች አእምሮው ተወጥሮ ነበር:: በዚህ ተቃራኒ ህይወት በሚስተዋልበት ቦታ ትንፋሽ አጥሮት ደረቱ በስቃይ እንዳይተረተር ስጋት እንደያዘው ሁሉ፣ እጆቹን አጣምሮ ደረቱን ተጫነው:: ዳግም እነዚያ የመጨረሻ ደሀ የሆኑትን፣ ልባቸው የደረቀውንና ምድር ውስጥ መጠለያ የሚፈልጉትን ምስኪኖች ተመለከታቸው፡፡
ዳግም በመወለድ አዲስ እውነተኛ ግዛት ማግኘት የሚፈልጉ እጅግ በጣም የተቸገሩ መንፈሳዊ ተጓዦችን መስለው ታዩት፡፡
በዚህ መልኩ የምርቃቱ ሥነ-ስርዓት ተጠናቅቆ የተሰበሰበው ህዝብ ወደየመጣበት ሊበተን ሲል፣ ዮሐና በተጨቆኑት ድሆች ስም ንግግር እንዲያደርግ ታላቅ ሀይል (መንፈስ) ሲገፋፋው ታወቀው፡፡
እናም ይህ የሚገፋው ታላቅ ኃይል ከሰማይና ከምድር ፊት እንደቆመ ሰባኪ ወደ ፊት አንደረደረው፡፡ ወደ መድረኩ ጥግ ወጥቶ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ወረወራቸውና እጆቹን ከፍ አድርጐ በማንሳት ወደ ሰማይ አመለከተ፡፡
ህዝቡ ሲሰበስብለት፣ ትኩረት እንዲሰጡ በሚያስገድድ ብርቱ ድምፅ ጮኸ ብሎ መናገር ጀመረ:- ........
«አቤቱ ከፍ ብሎ በሚታየው ደማቅ ብርሃን ተከበህ በዙፋንህ የተቀመጥከው የናዝሬቱ ሰው - ኢየሱስ ሆይ! እነሆ ካለህበት የሰማዩ ሰማያዊ ጉልላት ባሻገር ቁልቁል ወደዚህች ምድር ተመልከት፡፡ ፍጡሮችዋን ትናንትና እንደ ካባ ለብሰሃቸው ነበር፡፡ አቤቱ በህይወትህ ደም እንዲለመልሙ የዘራሃቸውን አበቦች የጢሻው አሜኬላዎች እንዴት ቀንጥለው እንደገደሏቸው ተመልከት! . . .
«አቤቱ መልካሙ እረኛ! በደረትህ ታቅፈው የነበረው ደካማ ጠቦት አሁን በተኩላዎች ተነጣጥሎ ተበልቷል፡፡ ንፁህ ደምህን ምድሪቱ መጣዋለች፡፡ ትኩስ ዕንባህ በሰዎች ልቦና ውስጥ ደርቋል፡፡ በእግሮችህ የቀደስከው ይህ መሬት የሀያላን እግሮች ደካሞችን የሚጨፈልቁበት፣ የጨቋኞች እጆች ደግሞ የደካሞችን ህይወት የሚያጠወልጉበት ጦር ሜዳ ሆኗል
ጥሪ ምንም.....
«አቤቱ! ችግረኞች ከጨለማው ውስጥ ሆነው አቤቱ ይላሉ፡፡ በስምህ ዙፋን ላይ ተቀምጠው ያንተን ቃል የሚሰብኩት ሰዎች ግን ጥሪያቸውን ነገሬ - አላሉትም:: እስካሁን የድሆች ዋይታና የለቅሶ አልተሰማቸውም፡፡ የመንፈስ አባት እንዲሆኑ የሳክካቸው ሰዎች በእጆችህ ያቀፍከውንና የባረክከውን የበግ ግልገል ዘነጣጥለው ለመዋጥ የሚራወጡ ተኩላዎች ሆኗል.....
«አቤቱ! ከአምላክ ልብ ዘንድ ይዘኸው የመጣኸው የህይወት ቃል በነዚያ መጻህፍት ገፆች ውስጥ ብቻ ተሸሽጐ የሚቀር ፍሬ-የለሽ ሆኗል፡፡ እናም በእሱ ቦታ አስፈሪ የፍርሃትና የስጋት ጩኸት ተተክቷል .....
..........ይቀጥላል............
👍👍👍👍👍👍👍👍
https://t.me/Asresee