ተዓምር አይደለም?
~ ~ ~ ~ ~
ሲሸቀጥ ሲነገድ ፍቅር ጉልት ዋለ
በራሱ ቀይ ደም እንጨት ላይ ተሳለ፡፡
ተዘባበቱበት፡፡
ያን ሁሉ ዓለንጋ መቻሉን ረሱ
"እስቲ ይውረድ" አሉ ከመስቀል በራሱ::
እስቲ ተዓምር አድርግ ይሉታል በዓለም
በታናሽ መገረፍ ተዓምር አይደለም?
"እስቲ ድንቅን አድርግ" ይላሉ -
..... አይፈሩምና ጡር
ተዓምር አይደለም?....
......መቸንከር በፍጡር?
ልፍስፍስ ነው አሉት
ደካማ ነው አሉት
ወከባ ነው አሉት...
.... አይችልም ማስገረም
እናትን እያዩ መመታት....
......በራሱ ተዓምር አይደለም?
ተዘባበቱበት::...........
እንደራቆተ ዋለ ባደባባይ
ምድርን ያለበሰ በደመና ሰማይ፡፡
ከንፈር ስንት ገባ? ተጠምቶ አደረ
ውኃ ለሁለት ከፍሎ እንዳላሻገረ፡፡
ማቀፍ ስንት ገባ?
መሳም ስንት ገባ?
ዋጋው ተወደደ ወይስ ቀዘቀዘ
ዓለምን የያዘ
በዓለም ተያዘ፡፡
ተዓምር አይደለም?
ኤልያስ ሽታኹን
.......... @Meklite21 💚💛❤
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉት👇👇👇
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee
~ ~ ~ ~ ~
ሲሸቀጥ ሲነገድ ፍቅር ጉልት ዋለ
በራሱ ቀይ ደም እንጨት ላይ ተሳለ፡፡
ተዘባበቱበት፡፡
ያን ሁሉ ዓለንጋ መቻሉን ረሱ
"እስቲ ይውረድ" አሉ ከመስቀል በራሱ::
እስቲ ተዓምር አድርግ ይሉታል በዓለም
በታናሽ መገረፍ ተዓምር አይደለም?
"እስቲ ድንቅን አድርግ" ይላሉ -
..... አይፈሩምና ጡር
ተዓምር አይደለም?....
......መቸንከር በፍጡር?
ልፍስፍስ ነው አሉት
ደካማ ነው አሉት
ወከባ ነው አሉት...
.... አይችልም ማስገረም
እናትን እያዩ መመታት....
......በራሱ ተዓምር አይደለም?
ተዘባበቱበት::...........
እንደራቆተ ዋለ ባደባባይ
ምድርን ያለበሰ በደመና ሰማይ፡፡
ከንፈር ስንት ገባ? ተጠምቶ አደረ
ውኃ ለሁለት ከፍሎ እንዳላሻገረ፡፡
ማቀፍ ስንት ገባ?
መሳም ስንት ገባ?
ዋጋው ተወደደ ወይስ ቀዘቀዘ
ዓለምን የያዘ
በዓለም ተያዘ፡፡
ተዓምር አይደለም?
ኤልያስ ሽታኹን
.......... @Meklite21 💚💛❤
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉት👇👇👇
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee