አንተ ፀጥተኛ ባህር ከሆንክና ከተጫዋች ፏፏቴ ጋር እራት ብትበላ ጥሩ ምሸት ታሳልፋላችሁ። “ወሬ እንዴት ነው የምጀምረው?” ብለህ ማሰብ አይጠበቅብህም። እንደውም ባጠቃላይ ማሰብ አይጠበቅብህም። ማድረግ ያለብህ በየመሀሉ ራስህን እየወዘወዝክ “አሀ” ማለት ነው። እሷ ምሽቱን ትሞላውና ወደ ቤትህ ስትሄድ “ምን አይነት ምርጥ ሰው ናት?” ትላለህ። በተቃራኒው አንተ ተጫዋች ፏፏቴ ከሆንክና የፍቅር ቀጠሮ ላይ ከፀጥተኛ ባህር ጋር ካሳለፍክ በተመሳሳይ ጥሩ ምሽት ይሆናል። አንተ ለሰአታት ስትጫወት እሷ ታደምጥሀለች፡፡ እናም ወደ ቤትህ ስትሄድ “ምን አይነት ምርጥ ሰው ናት” ትላለህ። መሳሳባችሁ አይቀርም።
ነገር ግን በትዳር አምስት አመት ከቆያችሁ በኋላ ተጫዋቹ ፏፏቴ ከእንቅልፉ ተነስቶ “አምስት ዓመት በትዳር አብረን ቆይተናል ግን በደንብ አላውቃትም,,, ሊል ይችላል። ፀጥተኛዋ ባህር በበኩሏ “በደንብ አውቄዋለሁ አንዳንዴ ዝም ቢል ጥሩ ነው።” ብላ ልታስብ ትችላለች። ጥሩው ዜና ፀጥተኛ ባህሮች ተጫዋች መሆን፤ ተጫዋች ፏፏቴዎች ደግሞ ዝም ማለትን መማር መቻላቸው ነው ስብእናችን ተፅእኖ ያሳድርብናል እንጂ ሙሉ ለሙሉ አይቆጣጠረንም፡፡
📓ዘላቂ የፍቅር ሚስጥር
📚@Bemnet_Library