ሰዎች ለማፍቀር ይሞክራሉ፤ ለመፀለይ ይሞክራሉ፤ ለመመሰጥ ይሞክራሉ። ስለሚሞክሩም ማፍቀር አይችሉም፡፡ ለማፍቀር እየሞከራችሁ እንዴት ማፍቀር ትችላላችሁ?ለመፀለይ የምትሞክሩ ከሆነ መፀለይ አትችሉም፡፡ ምክንያቱም ሀይላችሁ በመሞከር ላይ ያልቃልና፡፡ ለመመሰጥ የሚሞክርስ እንዴት መመሰጥ ይችላል? እናንተ በመሞከር አባዜ ውስጥ ናችሁ፡፡ የዜን መምህር መሀረቡን ሲጥል ተማሪው እዚያ ነበር፡፡ መምህሩ ለተማሪው እንዲህ አለው፡- “ለማንሳት ሞክርና ስጠኝ፡፡ አለው!”
ተማሪውም ወዲያውኑ መሀረቡን ከመሬት በማንሳት ለመምህሩ ሰጠው፡፡ ሆኖም መምህሩ መሀረቡን በድጋሚ መሬት ላይ በመጣል ለተማሪው እንዲህ አለው፡- “ያልኩህ ለማንሳት ሞክር ነው! ይህም ድርጊት ለስድስት ጊዜያት ያህል ቀጠለ፡፡ ተማሪውም የመምህሩ ንግግርና ድርጊት እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ ምን ማለቱ ይሆን ብሎ አሰበ፡፡ ወዲያውኑ ግን አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት፡፡ “መምህሩ ያለው ለማንሳት ሞክር ነው!” እናስ “እንዴት መሞከር እችላለሁ? አነሳሁትም አላነሳሁትም እንዴት መሞከር እችላለሁ?” ብሎ አለ፡፡
መምህሩም እንዲህ አለ፡- “ለዚህ ነው ለሶስት አመታት ለመመሰጥ ስትሞክር የነበረው፡፡ ተመሰጥክ አልተመሰጥክ እንዴት አድርገህ መሞከር ትችላለህ?” መሞከር መሳሪያ ነው፡፡ መሞከር ሽወዳ ነው፡፡ አንድን ነገር ማድረግ ሳትፈልግ ስትቀር ትሞክራለህ፡፡ አንድን ነገር ማድረግ ስትፈልግ ግን ታደርገዋለህ፡፡
📓የመኖር ጥበብ
📚@Bemnet_Library