እህተ አልጋዋ ላይ ተቀምጣለች።አይኖቿ ቀልተዋል፤ፊቷ አብጧል፤ስታለቅስ እንደዋለች በግልፅ ይታያል።ውበቷ ደብዝዟል። «እንደምን አመሸሽ እህተ» ከማለት ሌላ በእናቷ ፊት ሌላ ቃል ሊወጣው አልቻለም።እንደናፍቆቱና አመጣጡ ማንም ፊት ሊስማት የቆረጠ መስሎት ነበር።ሆኖም ሀፍረትና ይሉኝታ ጉተቱትና እጅዋን እንኳን ሳይጨብጥ እጆቹን ወደ ኋላዌ እንደሸረበ ቆመ።ነገር ግን ብቻዋን የማግኘት ጸሎቱ ሳይቆይ ደረሰለት።እናቷ «በል እስቲ ትንሽ አጫውታት» ብለውት ቶሎ ቶሎ እየተነፈሱ ወጡ።
እህተ አንገቷን ደፍታ የለበሰችውን ጋቢ ጫፍ ታፍተለትላለች።እውስጧ ገብቶ የሚያሰቃያት አንዳች ሀሳብ ወይም ሀዘን ጭምር እንጂ ፤በሽታ ብቻ እንዳልሆነ ከተረዳ ቆይቷል።
እንደቆመ ብዙ ስለቆየ አንገቷን ሳታቀና «ተቀመጥ እንጂ» አለችው።አልጋዋ ጫፍ ተቀምጦ አገጯን ቀና በማድረግ ፊቷን አየ።
«እህተ»
«ወዬ» ትንፋሽ እንጂ ድምፅ አልመሰለውም።እንደ እናቷ ሁሉ የእሷም ድምፅ ደክሞ ነበር።የሲቃ ቅኝትም የቀሰቀሰ መሰለው...ሊያምን አልቻለም።ለሰባት ቀናት ባለመገናኘታቸው ከመናፈቁ በስተቀር የፈገግታ ምንጭነቷ ነጥፎ፤የሀዘን ጥላ አጥሎባት እስከሚያገኛት ድረስ የዘገየ አልመሰለውም።
"ምን ሆንሽብኝ?"
«ምንም»
ትኩር ብሎ አያት።ዘልቀው የሚመረምሩ የሚመስሉ አይኖቹን ትኩረት ልትቋቋመው አልቻለችም።አገጯን ከጣቶቹ ሹልክ አድርጋ እንደገና አቀረቀረች።የፀፀትና የቁጭት መንታ ስለት ውስጧን ይገዘግዛታል።የዋለችበት ለቅሶ እንደገና የሚያገረሽ ስለመሰላት ከንፈሯን ነክሳ ታገለች።እንዲወጣ የማትፈልገውን ምስጢሯን ልታጋልጠው እንደተቃረበች ስለታወቃት ራሷን አጠነከረች።በዚህ ሁኔታ ራሷን ማጋለጧ ፋይዳ አልነበረውም።መደበቅ መቻል አለባት።አለበለዚያ ፍቅሯን ታጣለች።ራሷን እንጂ ፍቅሯን ማጣት አትፈልግም.......
📓ርዕስ፦ሰንሰለት
✍️ደራሲ፦ፈቀደ ዩሀንስ
📚 @Bemnet_Library