#ከዜናዎቻችን| ከመስከረም ወር ጀምሮ ታስቦ ይከፈላል ተብሎ የነበረው የደሞዝ ጭማሪ አሁንም ለሌላ ግዜ መተላለፉ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- በርካታ የመንግስት ሰራተኞች የጥቅምት ወር ደሞዛቸው በድሮው ስኬል እንደተከፈላቸው የተናገሩ ሲሆን በመንግስት ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ በሚደረግ መልኩ ይከፈላል የተባለው ደሞዝ አሁንም የውሀ ሽታ እንደሆነባቸው ገልፀዋል።
መሠረት ሚድያ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምንጮቹ ባገኘው መረጃ ከታህሳስ ወር 2017 ዓ/ም ወዲህ አዲሱ የደሞዝ ስኬል ይፈፀማል ተብሎ አይጠበቅም።
"በኢትዮጵያ ያለ የመንግስት ሰራተኛን ደሞዝ ስኬል በዝቅተኛ የመንግስት መዋቅር ድረስ ወርዶ ማስተካከል የቀናት እና የሳምንት ግዜ ብቻ አይበቃውም" ያሉት ምንጫችን ስራው ቢያንስ ተጨማሪ ሁለት ወራትን ይጠይቃል ብለዋል።
ይሁንና በመንግስት በኩል ፍላጎቱ ካለ ስኬሉ ተሰርቶ ካለቀ በኋላ ክፍያው ወደኃላ ተመልሶ ከመስከረም ወር ጀምሮ ሆኖ እንዲከፈል ማስደረግ ይቻላል ብለዋል።
ይሁንና ይህ አማራጭ መንግስትን በቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያስወጣው ስለሆነ መንግስት ያደርገዋል ብለው እንደማይገምቱ ጨምረው ተናግረዋል።
ምንጭ:መሠረት ሚዲያ
@EEC1227