👉የመካነ ኢየሱስ/እስቴ - ስማዳ መንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው
💫በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን'ን ከደቡብ ወሎ ዞን ጋር የሚያገናኘው የመካነ ኢየሱስ/እስቴ - ስማዳ መንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
🚧50.4 ኪ/ሜ የሚሸፍነው የመንገድ ፕሮጀክቱ፣ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።
🏷አሁን ላይ የ47 ኪሎሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ተሠርቷል።
▶️በቀሪው የፕሮጀክቱ ክፍል ማለትም ወገዳ ከተማ ላይ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውኃ ማፋሰሻ፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ። በተጨማሪም የአምስት ድልድዮች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።
⏺የመንገድ ግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም አሁን ላይ 90.9 በመቶ የደረሰ ሲኾን፣ ቀሪ ሥራዎችን በዚህ ዓመት ለማጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።
▶️በፕሮጀክቱ የከተማ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለፕሮጀክቱ መቋረጥ ምክንያት የነበረ ቢኾንም፤ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከየአካባቢው የመስተዳድር አካላት ጋር ባደረገው ጥረት ግንባታውን ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል።
💫ግንባታውን ዓለም አቀፉ 'ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ' እያከናወነ ይገኛል።
🔰ለግንባታው የሚውለው 1.9 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በፌደራል መንግሥት ነው።
💫'ፕሮሚናንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ' ግንባታውን የመቆጣጠርና የማማከር ሥራ እየሠራ ይገኛል።
🚧የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀድሞ ከእስቴ ወደ ስማዳ ለመጓዝ ይወስድ የነበረውን 3 ሰዓት የጉዞ ጊዜ በግማሽ ያሳጥረዋል።
Via ERA
@etconp