👉የአቃቂ ድልድይ ግንባታ 40 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል
🚧በአቃቂ ክፍለ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘው የአቃቂ ወንዝ መሻገሪያ ድልድይ የግንባታ ስራ 40 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡
የድልድዩን ግንባታ ብሪጅ ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ ከ447 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ ደግሞ ስታዲያ አማካሪ ድርጅት እየተከታተለው ይገኛል፡፡
የግንባታ ስራው በዲዛይን ለውጥ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይጠናቀቅ ቆያቷል፡፡
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የተቋሙ አመራርና የሥራ መሪዎች ቡድን በግንባታ ሥፍራው በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን፣ የድልድዩ ግንባታ በፍጥነት በሚጠናቀቅበት ሁኔታም ላይ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
አሁን ላይ ከድልድዩ ግንባታ 2 ዋና ዋና ተሸካሚዎች እና 12 ምሰስዎች መካከል 50 በመቶ የሚሆነው ስራ በመገባደድ ላይ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የድልድዩን የላይኛውን ክፍል ፕሪካስት የማምረት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፤ ከቃሊቲ ቶታል በዜሮ ስምንት ወደ በአቃቂ ከተማ እና ወደ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ የሚደረገውን የትራፊክ ፍሰት የተቀላጠፈ በማድረግ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡
Via የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
@etconp