👉ከመንግሥት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ባሻገር ተቋራጮች በራሳቸው ደካማ የሆነ የውል አስተዳደር (Contract Administration) ትግበራ እንዳላቸውም ተጠቅሷል።
ሳሙኤል (ኢንጂነር)፣ ‹‹ለምሳሌ የዋጋ ማስተካከያ ይፈቀድልን በሚል ገንዘብ ሚኒስቴር ሲጠየቅ፣ ‹ማን ከለከላችሁ?› የሚል ጥያቄ ሲያነሳ፣ የከለከለን አማካሪው በልዩ ሁኔታ (Special Condition) በማስፈረም መሆኑን ሲገልጹ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደዚህ ያለ ውል ማን ፈርሙ አላችሁ? ብሎናል። የእኛንም ችግር ራሳችን መውሰድ መቻል አለብን። ግን ፍፁም የተከለከለ አይደለም። በፊት የ12 ወር ተባለ አሁን የ18 ወር ሆነ፣ ከዚያ ውጪ ግን ሙሉ ለሙሉ ይህ ፕሮጀክት ይህንን አያካትትም ብሎ መከልከልን ያመጣው በደካማ ውል አስተዳደር ትግበራችን ችግር ነው፤›› ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የግንባታ ጥሬ ዕቃ ከውጭ አገሮች ለማስመጣት፣ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ከ40 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን ያህል ገንዘብ የሚያወጡ ቢሆንም፣ ግዥ ለመፈጸም የሚዋዋሉት አገር ውስጥ ካለ አስመጪ ድርጅት ጋር በመሆኑ፣ ዕቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገባበት ጊዜ ፍጥነት አስተማማኝ አለመሆኑን ጥናቶቹን ያቀረቡት ባለሙያዎች አስረድተዋል።
Via ሪፖርተር
@etconp